TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀሰተኛ ወሬዎችን ተጠንቀቁ‼️

በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ #ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለመረበሽ የሚደረጉ ማናቸውንም ዓይነት እንቅስቃሴዎችን በመለየት በጋራ እንደሚከላከሉ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አካላት ገለፁ፡፡

ተማሪዎቹም ተጨባጭ ባልሆኑና መሠረተቢስ #ሀሰተኛ ወሬዎች ተታለው ሳይደናገጡ ዋና ትኩረታቸው በትምህርታቸው ላይ ሊሆን እንደሚገባም የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ አሳስበዋል፡፡

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ እንደገለፁት የዩኒቨርሲቲውን ሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደትን #ለማደናቀፍና ለመረበሽ የሚፈልጉ አንዳንድ ሀይሎች ተማሪዎች ርስበርስ እንዲጋጩ ሆን ተብለው መሠረት የሌላቸው ሀሰተኛ ወሬዎችን በግቢው ውስጥ በመንዛት #ብጥብጥና ግጭት ለመፍጠር የተሞከረው ሙከራ አለመሳካቱን ገልፀው፣ ዩኒቨርሲቲው ያለውን መልካም ስምና ገፅታን በማበላሻትና ተማሪዎች ትምህርታቸውን ተረጋግቶ እንዳይከታተሉ ለማድርግ በውጭም ሆነ በውስጥ በሚሰሩ የጥፋት ሀይሎች ላይ የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው የተደረሰበትንም ውሳኔና እርምጃ በቀጣዩ ዩኒቨርሲቲው እንደሚያሳውቅ ተነግረዋል፡፡

ተማሪዎችም ከእውነት በራቁና በሚናፈሱ ወሬዎች ሳይደናገሩ ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያደርጉ እንዲሁም ወላጆችም ባልተጨበጠና ሀላፊነት በጎደላቸው ግለሰቦች በማህበራዊ ድህረ-ገጽ በሚሰራጩ መሰረት በሌላቸው ወሬዎች ሊረበሹ እንደማይገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ #ሲሳይ_ዮሐንስ እንደተናገረው ተማሪዎች እንዳይረጋጉ ሆን ተብሎ በሀሰት የሚነዙ ወሬዎች መኖራቸውን ጠቅሶ በአሁኑ ግዜ የመማር ማስተማሩ ተግባር ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ነው ሲል ተነግረዋል፡፡

ምንጭ፦ Hadiya zone Communication main process
@tsegabwolde @tikvahethiopia