TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update የዓለም ኤድስ ቀን የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 22 ቀን 2011 ዓ.ም በፌደራል ደረጃ በዱከም እንደሚከበር ተገልጿል። በዓሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን፥ አሁን ላይ እየታየ ያለውን #መዘናጋት በመስበር በየደረጃው የሚገኘው አመራርና አጠቃላይ ማህበረሰብ ቃሉን እንዲያድስ የሚደረግበት ነው ተብሏል።

©fbc
@tsegabwolse @tikvahethiopia
#WezeroLemlemBezabeh

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ማህበረሰቡ ላይ የሚስተዋለው መዘናጋት ለውጥ ካላመጣ ተጨማሪ የእንቅስቃሴ ክልከላዎችንና እገዳዎችን ለማድረግ እንደሚገደድ ገልጿል፡፡

የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ ከጅቡቲ ተመላሽ በሆኑና በድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ማቆያ በሚገኙ 574 ተመላሾች ላይ በተደረገ የናሙና ምርመራ ሶስቱ (3) ላይ ቫይረሱ ሊገኝ ችሏል ብለዋል፡፡

የበሮ ኃላፊዋ አክለውም ግለሰቦቹ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የሳቢያን ሆስፒታል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑንና በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው ከነርሱ ጋር ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በመለየትም ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የፈረንሳይ ሆስፒታል ተገቢውን ክትትል እንዲያገኙ መለየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ማህበረሰቡ በበሽታው ላይ ያለው #መዘናጋት ከቀን በቀን እየጨመረ ነው ያሉት ወይዘሮ ለምለም የበሽታውን ገዳይነት በመረዳት የተቀመጡ የአካላዊ ርቀት ፤ ንፅህናን ባግባቡ የመጠበቅ እንዲሁም ተያያዠ ህጎችን በማክበር ለራሱም ሆነ ለማህበረሰቡ ጤና ሊጠነቀቅ ይገባል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrGurmeessaaHinkoosaa

ህብረተሰቡ በኮሮና ስርጭት ላይ #መዘናጋት እንደሌለበት የጤና ባለሞያው ዶክተር ጉርሜሳ ሂንኮሳ አሳስበዋል። ዶክተር ጉርሜሳ ከOMN ጋር በነበራቸው ቆይታ የአሜሪካን ሁኔታ እንደማሳያ አስተዋል።

በአሜሪካ በ49 የመጀመሪያው ቀናት በበሽታድ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 987 እንደነበር አስታውሰው ከዚያ ቀጥሎ ባሉት 16 ቀናት ውስጥ ይህ ቁጥር ከ100,000 መብለጡን ገልፀዋል።

ይህ የሚያሳየው በሽታው በአንዴ መስፋፋት እንደሚችል ነው ያሉት ዶክተር ጉርሜሳ ህብረተሰቡ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ቁጥር አይቶ መዘናጋት የለበትም ብለዋል።

በተጨማሪም ህብረተሰቡ በጤና ባለሞያዎች የሚሰጠውን ምክር መከተል እና ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።

#DrGurmeessaaHinkoosaa #OMN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia