TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ህወሃት⬇️

5ኛ ቀኑን የያዘው የህውሃት ድርጅታዊ ጉባዔ በዛሬ ውሎው የተለያዩ #ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ድርጅታዊ ጉባዔው በዛሬው ውሎው የማእከላዊ ኮሜቴ አባላት ምርጫ ያካሄደ ሲሆን፥ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ቁጥርም ከ45 ወደ 55 ከፍ እንዲል ወስኗል።

በዚህም መሰረት 65 እጩዎች ለማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት የቀረቡ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ የ55 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ
ተካሂዷል።

ለማእከላዊ ኮሚቴ ከተመረጡት 55 ውስጥ 45ቱ ለኢህአዴግ ምክር ቤት አባልነት የሚቀርቡ ይሆናል።

ለማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት የተመረጡት ዝርዝርም በነገው እለት ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል። ድርጅታዊ ጉባዔው በዛሬ ውሎው 12 ነባር አመራሮችንም በክብር #አሰናብቷል

በዚህም መሰረት፦

1 አቶ አባይ ወልዱ
2 ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ
3 አቶ ገብረመስቀል ታረቀኝ
4 አቶ ሚካኤል አብረሃ
5 አቶ ጎበዛይ ወልደአረጋይ
6 አቶ ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ
7 አቶ ነጋ በረኸ
8 አቶ ተወልደብርሃን ተስፋዓለም
9 አቶ ማሞ ገብረእግዚአብሄር
10 አቶ ጎይቶም ይብራህ
11 አቶ ሀይሌ አሰፈሃ
12 አቶ ኪሮስ ቢተው ከድርጅቱ በክብር ተሰናብተዋል።

የህወሃት ድርጅታዊ ጉባዔ በነገ ውሎው የድርጅቱን ሊቀ መንበር እና ምክትል ሊቀመንበር #ምርጫን እንዲሁም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫን እንደሚያካሄድ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ምርጫ በማካሄድ በነገው እለት #ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦዴፓ🔝የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኦዲፒ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን እያካሄደ መሆኑን የፓርቲው የገጠር ፓለቲካ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል። ፓርቲው በስብሰባው ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን የሚያስችሉ #ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። እንዲሁም የህግ የበላይነትን ለማስከበር፣ የሀገር አንድነትን ለማስቀጠል እና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ይገመግማል ተብሏል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia