TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
«አፍሪቃ ለክፉ ቀን መዘጋጀት አለባት» - ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

«አፍሪቃ ለክፉ ቀን መዘጋጀት አለባት» ሲሉ የዓለም የጤና ድርጅት ዳሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም የኮሮና ወረርሽን በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ መሆኑን አስጠንቅቀዋል።

ዶክተር ቴድሮስ ትላንት በሰጡት መግለጫ «አፍሪቃ ንቂ» አህጉሬ ንቂ» ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተውም አሳስበዋል። 116 ታማሚዎች ላይ ተህዋሲውን ባረጋገጠችው ደቡብ አፍሪቃ ስድስት እድሜያቸው ከ 10 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ይገኙበታል።

ከ54ቱ የአፍሪቃ ሀገራት 30ዎቹ በተህዋሲው የተያዙ ሰዎች እንዳሉ ያረጋገጡ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ ጋምቢያ፣ ዛምቢያ እና ጅቡቲ እንዲሁ የመጀመሪያ ያሉትን ሰው አግኝተዋል።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Italy #Russia #COVID19

ሩስያ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝ በብርቱ እየተጠቃች ያለችውን ጣልያንን ለመደገፍ ሐኪሞችን እና የህክምና ቁሳቁስ እየላከች መሆኗን አስታውቃለች።

ሩስያ በወረርሽኙ ክፉኛ የተጠቃችዉን ጣልያንን ለመደገፍ በዘጠኝ የጭነት አውሮፕላኖች የሕክምና ባለሞያዎች እና ቁሳቁስ ወደስፍራው ለማጓጓዝ በችካሎቭስኪ ወታደራዊ ሰፈር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጻለች።

በተልዕኮው ስምንት (8) ተንቀሳቃሽ የሕክምና ቡድኖችን ጨምሮ የሕክምና ቁሳቁስ እና የጸረ ቫይረስ [COVID-19] ርጭት ተሽከርካሪዎች ያካተተ መሆኑን ተገልጿል።

#AFP #DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፊሊፒንስ ውስጥ 9 ዶክተሮች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው መሞታቸው ተሰምቷል። የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ ከፍተኛ ትግል እያደረጉ ያሉት የፊሊፒንስ የጤና ባለሞያዎች በቂ መከላከያ እያገኙ አይደለም ተብሏል። #StayHomeSaveLives @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ ከፊሊፒንስ በDW ፦

- የፊሊፒንስ ሕክምና ማህበር የ9ኙ ሐኪሞቹ ህልፈት የጤና ባለሞያዎች የቫይረሱን መከላከያ ቁሳቁስ እንደማይቀርብላቸው ማሳያ ነው ሲል ወቀሳውን አቅርቧል።

- በዋና ከተማዋ ማኒላ የሚገኙ ሶስት ትልልቅ ሆስፒታሎች በመሙላታቸው በቫይረሱ ታመው የሚመጡ ሰዎችን መቀበል አቁመዋል።

- በመቶዎች የሚቆጠሩ ሐኪሞች ለቫይረሱ ተጋላጭ በመሆናቸው እና በቫይረሱ ሊያዙ ይችላሉ በሚል ጥርጣሬ ለ14 ቀናት መለየታቸውንም ተነግሯል። ይህ ደግሞ ለደሃዋ ፊሊፒንስ በእንቅርት ላይ እንዳይሆንባት አስግቷል።

- በማኒላ ከሆስፒታሎች አቅም በላይ የሆኑትን ታማሚዎች ወደ ሌሎች ሆስፒታሎች ማድረስ ካልተቻለ የሃገሪቱ የሕክምና ስረዓት ውድቀት ሊያጋጥመው ይችላል ተብሏል።

#DW #REUTERS
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር ሀገር አቀፍ መረጃዎች፦

- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሥራ እንዲውል የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለግሰዋል።

- ሼህ ሁሴን አሊ አላሙዲ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝን ለመግታት የ120 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በተጨማሪ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ማኔጅመንት፣ አመራር እና ሠራተኞች ከ10 ሚልዮን ብር በላይ ለተመሳሳይ አላማ አበርክተዋል።

- የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ 14, 000 ሰራተኞቹን በጊዚያዊነት ከስራ አሰናብቷል። ሰራተኞቹ ከስራ የተሰናበቱት በአሜሪካና በአውሮፓ ገበያዎች የምርቶቹ ዋነኛ ተቀባይ የነበሩት ድርጅቶች በኮሮና ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው እየተቀዛቀዘ በመምጣቱ ነው።

- መከላከያ ሰራዊት ነገ በአዲስ አበባ የቫይረሱን ስርጭትን ለመግታት የሚያግዙ መልዕክቶችን የያዙ በራሪ ወረቀቶችን በሄሊኮፕተር ይበትናል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ በማርሽ ባንድ የታጀበ የማንቂያ ቅስቀሳ ያደርጋል፡፡

- አልማ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ መመደቡን አስታውቋል።

#DW #etv #EliasMeseret #fbc #ena
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከ7,600 በላይ ታራሚዎች እንዲፈቱ ተወስኗል!

የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ስርጭትን ለመከላከል በሚል ከ7,600 በላይ ታራሚዎችን በይቅርታ እንዲፈቱ ወስኗል።

ከእስር በይቅርታ እንዲፈቱ የተወሰነላቸው፦

- የሚያጠቡ እናቶች፣
- የአመክሮ ጊዜያቸው አንድ ዓመት የቀራቸው፣
- ቀላል ወንጀል ፈፅመው ጊዜያቸው አንድ ዐመት የቀራቸው፣
- የሌላ አገር እስረኛ ዜጎች ናቸው።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#RUSSIA

ሩሲያ በአንድ ቀን ብቻ 9,623 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ። አብዛኞቹ በዋና ከተማዋ #ሞስኮ የሚኖሩ ናቸው። ይህ ቁጥር ወረርሽኙ ሩሲያ ከደረሰ በኋላ ከተመዘገቡት ሁሉ ከፍተኛው ነው።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት 57 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በመላ አገሪቱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 1,222 ማሻቀቡን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ኮሚቴ አስታውቋል።

የሞስኮ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ሰርጌይ ሶብያኒን የከተማው ነዋሪዎች ራሳቸውን በመኖሪያ ቤታቸው ለይተው እንዲያቆዩ ተማፅነዋል።

በኮሮና ቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባው እጅግ የከፋ ደረጃ አለመድረሱን ገልጸዋል። ሁኔታው ከከፋ በሞስኮ ከተማ ለመንቀሳቀስ የሚሰጥ ፈቃድ ሊቀነስ እንደሚችልም ከንቲባው ገልጸዋል።

በሞስኮ ከተማ ነዋሪዎች ከመንግሥት ልዩ ፈቃድ ካላገኙ በቀር ከቤታቸው መውጣት የሚችሉት ዕቃ ለመሸመት፣ ውሾቻቸውን ለማንሸራሸር እና ቆሻሻ ለመጣል ብቻ ነው።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopi
አጫጭር መረጃዎች ፦

- ዋይት ሐውስ፤ የአሜሪካ መንግሥት ጤና አማካሪ የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ፋውቺ ምክር ቤት ቀርበው እንዳይመሰክሩ አግዷል። ዶክተር ፋውቺ፤ ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን የመከቱበት መንገድ ትክክል ነው ወይስ አይደለም በሚለው ላይ ነበር እንዲመሰክሩ የታሰበው - #BBC

- በትናንትናው ዕለት የሩሲያ የግንባታ ሚኒስትር ብላድሚር ያኩሼቭ በኮሮና ተይዘው በሆስፒታል ሕክምና መከታተል መጀመራቸውን አረጋግጠዋል። ምክትላቸው ዲሚትሪ ፎልኮቭም በኮሮና መያዛቸውን መስሪያ ቤታቸው አረጋግጧል - #DW

- በደቡብ ኮሪያ ባለፉት 24 ሰዓት 6 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ስድስቱም (6) ከውጭ የገቡ ናቸው።

- በኢራን ባለፉት 24 ሰዓት 802 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ ዛሬ ሪፖርት የተደረገው ኬዝ ከየካቲት 30 በኃላ የተመዘገበ ዝቅተኛው ቁጥር ነው።

- በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት የ276 ሰዎች ሞት ሲመዘገበ 2,588 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።

- በቻይና ባለፉት 24 ሰዓት 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙን ሪፖርት አድርጋለች። ዛሬ በሀገሪቱ ሞት ሳይመዘገብ አምስተኛ ቀኑን ይዟል።

- FDA ለኢቦላ በሽታ የሚውለውን ሬምዴሲቬር የተባለውን መድኃኒት ለአስቸኳይ ጊዜ የኮቪድ-19 ህክምና እንዲውል ፈቅዷል። ይህ ጸረ ቫይረስ የሆነው መድኃኒት በኮቪድ-19 በጽኑ ታመው ሆስፒታል የሚገኙ ሰዎችን ለማከም ይውላል። የአሜሪካ ምግብና መድኃኒት አስተዳደር ኮሚሽነር የሆኑት ስቴፈን ሃን 'ይህ የኮቪድ-19ን ለማከም ዕውቅና የተሰጠው የመጀመሪያው መድኃኒት ነው' ብለዋል - #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ሳቢያ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ዕርዳታ ጠባቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ የፋይናንስ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ መናገራቸው DW ዘግቧል።

ሚኒስትሩ እንዳሉት በዚህ ሳቢያ በአገሪቱ ዕርዳታ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በአጠቃላይ ወደ 30 ሚሊዮን ያሻቅባል።

መንግስት የኮሮና ወረሽኝን ለመከላከል ያቋቋመው የምኒስትሮች ኮሚቴ በትናንትናው ዕለት ባደረገው እና ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በመሩት ውይይት ለዚህ ብቻ ኢትዮጵያ 1.4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ገልጸዋል።

የኮሮና ወረርሽኝን ለመቋቋም ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት፣ ከአውሮፓ ኅብረት፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታኒያ እና ቻይና 2.1 ቢሊዮን ዶላር ዕገዛ መጠየቋን አቶ አሕመድ ተናግረዋል። ከዚህ ውስጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር በቅርቡ ለኢትዮጵያ ሊሰጥ እንደሚችል ጠቁመዋል።

በትናንትናው ዕለት የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ጫና ለመቋቋም የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ የ411 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ አጽድቋል። የዓለም ባንክ በበኩሉ 750 ሚሊዮን ዶላር የበጀት ድጋፍ ሊሰጥ እንደሚችል የፋይናንስ ሚኒስትሩ አስረድተዋል - #DW

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#CHINA

ቻይና የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መነሻን የሚመረምሩ ዓለም አቀፍ አጥኚዎችን አሁን ወደ ሀገርዋ እንደማትጋብዝ አስታውቃለች።

በጄኔቫ የቻይና አምባሳደር እንዳሉት ቻይና አጥኚዎቹን የምትጋብዘው ቻይና በኮሮና ቫይረስ ላይ ድል ከተቀዳጀች በኋላ ነው ብለዋል።

አምባሳደር ቼን ሹ ሀገራቸው አሁን ቅድሚያ የምትሰጠው ወረርሽኙን ማሸነፍ እና የቫይረሱን ጉዳይ ፖለቲካዊ ለማድረግ የሚሰነዘሩ ትርጉም የሌላቸው ውንጀላዎችን መቋቋም ላይ መሆኑን አስረድተዋል።

የዓለም የጤና ድርጅት በበኩሉ የቫይረሱን ምንጭ ለማጣራት በሚካሄደው ምርመራ ላይ ለመሳተፍ የቻይናን #ግብዣ እየተጠበቀ መሆኑን አስታውቋል።

ቻይና ግብዣውን መቼ ልታቀርብ እንደምትችል የተጠየቁት ሊቼን ሹ በአሁኑ ወቅት ቅድሚያ ሊሰጣቸው በሚችሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩሩ ተናግረው ፤ ይህን ለማድረግ ደግሞ ትክክለኛውን ድባብ እንፈልጋለን ብለዋል - #DW

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AtoAknawKawza

በደቡብ ክልል እስከ 12 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በኮቪድ - 19 ቫይረስ ሊጠቁ ይችላሉ ሲል የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ #አስጠንቅቋል

የቢሮው ሃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ እንዳሉት የከፋ የተጋላጭ ሁኔታ አመልካች እንደሚያሳየው አሁን በበሽታው ዙሪያ የሚያታየውን 'የጥንቃቄ ጉድለት' መቅረፍ ካልተቻለ በክልሉ 60 በመቶ የሚሆነው ነዋሪ በቫይረሱ ሊጠቃ ይችላል።

📹#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia