TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ነዳጅ

⛽️ " አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ሆነ ብለው የነዳጅ ዕጥረት ያጋጠመ ለማስመሰል መሞከራቸውን በክትትል ደርሼበተለሁ " - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን

⛽️ " ከአዲሱ የዲጂታል ስርዓት ጋር በተያያዘ የተሽከርካሪዎቻቸውን የነዳጅ ታንከር #በመሙላት፣ ግዥ የሚፈጸሙ አሽከርካሪዎች ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆኑ ነው " - የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር

የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ሆነ ብለው የነዳጅ ዕጥረት ያጋጠመ ለማስመሰል መሞከራቸውን በክትትል ደርሼበታለሁ አለ።

" በሀገር ውስጥ በቂ የነዳጅ አቅርቦት አለ " የሚለው ባለስልጣን መ/ቤቱ ይህ እየታወቀ የነዳጅ ዕጥረት ይከሰታል የሚሉ አዋኪ መልዕክቶች ሆነ ተብለው የሚነዙ መሆኑን ሕብረተሰቡ ይገንዘብ ሲል አሳስቧል፡፡

በቀጣይ በነዳጅ ማደያዎች ላይ የአገልግሎት አሰጣጥ መዘግየት እና ዕጥረት መፍጠርን የመሳሰሉ ችግሮች በሚፈጥሩ አካላት ላይ ክትትል በማድረግ አስተማሪ እርምጃ እወስዳለሁ ሲልም አስጠንቅቋል።

በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም የሚያስችል አካውንት ካለመክፈት ጋር የተያያዘ እንጅ የነዳጅ ዕጥረት አይደለም ሲል አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር ፥ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጠው ቃል ፤ ከአዲሱ የዲጂታል ስርዓት ጋር በተያያዘ የተሽከርካሪዎቻቸውን የነዳጅ ታንከር #በመሙላት፣ ግዥ የሚፈጸሙ አሽከርካሪዎች ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆኑ ነው ብሏል።

አሁንም ቢሆን ወደ ዲጂታል የግብይት ሥርዓቱ የማስገባቱ ሥራ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሊፈጠር የሚችለውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ ተጨማሪ የነዳጅ አቅርቦት ያስፈልጋል ብሏል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ፥
" አሁን የሚታየው መጨናነቅ የተወሰኑ ቀናት ሊቀጥል የሚችል ቢሆንም እንኳን መጨናነቁን ለማስቀረት የግድ መንግሥት በቂ ነዳጅ ወደ ከተማው እንዲገባ ማድረግ ይገባዋል " ያለ ሲሆን " ይህንን ካላደረገ ዕድሉን አግኝተው ነዳጅ የሚቀዱ ተገልጋዮች፣ ከፍላጎታቸው በላይ እየቀዱ የሚቀጥሉ ስለሚሆን የነዳጅ አቅርቦቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል " ብሏል።

@tikvahethiopia