TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በሱማሌ ክልል “ሔጎ” በሚል ስያሜ ይንቀሳቀስ የነበረው የወጣቶች ሕገ ወጥ ቡድን ከሞላ ጎደል #እንዲበተን ተደርጓል፡፡ ብዙዎቹ ሕገ ወጥ ሥራ ሲሰሩ የነበሩ የቡድኑ አባላት በቁጥር ሥር ውለዋል፤ ሰው #ሲገድሉ የነበሩ ጥቂት ቁልፍ አመራሮቹ ግን ተሰውረዋል ብለዋል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር #ሙስጠፋ_ዑመር ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን በሰጡት መግለጫ፡፡

via~wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

“አባ ቶርቤ” በሚል መጠሪያ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በድብቅ በመንቀሳቀስ ሰዎችን ሲገድሉና ሲያስገድሉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች #በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንዳስታወቀው፥ ብሄራዊ የመረጃ እና የደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በዛሬው እለት ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ “አባ ቶርቤ” (ባለሳምንት) በሚል መጠሪያ በመደራጀት ሰላማዊ ዜጎችን፣ የመንግስት ባለስልጣናት እና የፀጥታ ሀይሎችን #ሲገድሉ እና #ሲያስገድሉ ነበር በሚል ነው ተጠርረው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

የተጠርጣሪዎቹን ማንነትና ዝርዝር መረጃ እንደደረሰው ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia