TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
READY FOR LAUNCH? ለምጥቀት ዝግጁ?

#ETRSS1 #ESSS #ESSTI #Ethiopia #SpaceGeneration #SatelliteLaunch
#እውንሆነ

(Ethiopian Space Science Society)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ በመጪው ሰኔ ወር አጋማሽ የፀሃይ ግርዶሽ ይከሰታል! በኢትዮጵያ በመጪው ሰኔ ወር አጋማሽ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ እንደሚከሰት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል። ግርዶሹ ከምዕራብ እስከ ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ የሚታይ ሲሆን ክስተቱም ወለጋ፣ ከፊል ጎጃምና ጎንደር፣ በወሎ በተለይ ላሊበላ አካባቢ ቀኑ #የሚጨልም ይሆናል ተብሏል። በተቀረው የአገሪቱ ክፍል ደግሞ በዕለቱ…
የፀሐይ ግርዶሽ እና ጥንቃቄ!

የፀሐይ ግርዶሽን በዓይን በቀጥታ መመልከት ቋሚ ጉዳት በዓይን ላይ ያደርሳል። ግርዶሹን ለመመልከት ፦

1. ደረጃውን የጠበቀ የግርዶሽ መነፅር መጠቀም

2. ፒን ሆል ካሜራ ወይም በአነስተኛ ቀዳዳ ወደ ድፍን ካርቶን የሚገባውን ብርሃን የሚስለውን ስእል ጀርባ ለፀሐይ በማዞር መመልከት

3. ጨለማ ክፍል ውስጥ በቀዳዳ የሚገባውን የፀሐይ ብርሃን መሬት ወይም ግድግዳ ላይ የሚሰራውን ስእል መመልከት

4. በዛፎች ቅጠል አልፎ መሬት ላይ የሚያርፈውን የፀሐይ ስእል መመልከት

5. ለቴሌስኮፕም ሆነ ባይነኩላር የፀሐይ ብርሃን መጣኝ ደረጃውን የጠበቀ ፊልተር ግጥሞ መመልከት

6. ግርዶሹን የሚያሳዩ የቀጥታ ስርጭቶችን መመልከት

የፀሐይ መነፅር ፣ ፍሎፒ ዲስክ ፣ የፎቶ ፊልም ፣የራጅ ፊልም እና የመሳሰሉት ቁሶች መጠቀም በዓይን ላይ ጉዳት ያደርሳል - #ESSS

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሰኔ 14ቱ የጸሃይ ግርዶሽ!

ሙሉ ወይም ቶታል የጸሃይ ግርዶሽ በየ3 ዓመት ሁለት (2) ጊዜ ሲከሰት ፤ በአንድ ስፍራ ላይ በድጋሚ ለመከሰት እስከ 400 ዓመት ሊፈጅ ይችላል።

ከዚህ በኃላ በሀገራችን ብዙ ሰዎች የሚመለከቱት ከሰኔ 14ቱ ጋር ተመሳሳይ ግርዶሽ የሚከሰተው ከ54 ዓመት በኃላ ሲሆን ሐረር ፣ ጅግጅጋ ፣ ድሬዳዋ ፣ ደብረ ብርሃን እና ደብረ ማርቆስ እሳታማ ቀለበት ለመመልከት እድለኛ ስፍራዎች ይሆናሉ።

ማሳሰቢያ ፦ የጸሃይ ግርዶሽ በዓይን መመልከት ቋሚ ጉዳት በዓይን ላይ ያደርሳል ፤ ሶላር ኢክሊፕስ መነፅር በመጠቀም፣ በጨለማ ክፍል ውስጥ በቀዳዳ የሚገባ የጸሃይ ብርሃን የሚስለውን ቅርፅ በመመልከት ወይም ፒን ሆል ካሜራ በመስራት መመልከት ይቻላል - #ESSS

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot
የሰኔ 14ቱ ግርዶሽ- የትና መቼ በኢትዮጵያ ?

በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል ፀሐይ ከ60 - 80 ፐርሰነት ተሸፍና ከፊል ግርዶሽ ይታያል፡፡ ከ80 ፐርሰነት በላይ ያለውን ዋናውን ግርዶሽ ግን ከምዕራብ ኢትዮጵያ አንሥቶ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ በሚገኝ ስፍራ ጎልቶ ይታያል፡፡

ክስተቱ ወለጋ አካባቢ ጀምሮ ከፊል ጎጃምን ፣ ከፊል ጎንደርን አልፎ ወደ ወሎ ላሊበላን አቋርጦ ይሄዳል፡፡ በእነዚህ ቦታዎች ፀሐይ እስክ 99 ፐርሰንት ተሸፍና ቀለበታዊውን ግርዶሽ ማየት ይቻላል፡፡

ቀለበታዊ ግርዶሽ ማየት ከሚችሉ አነስተኛ ከተሞች/ቦታዎች ቤጊ ፣ ሜቲ፣ መንዲ ፣ ጫልቱ ፣ ቡሬ ፣ አገው ግምጃቤት ፣ እንጅባራ ፣ ግሽ አባይ፣ ሞጣ ፣ ዳሞት ፣ ጋይንት ፣ ንፋስ መውጫ ፣ ጋሸና ፣ ሙጃ ፣ ዋጃ ፣ ቆቦ ፣ ኮረም፣ አላማጣ ፣ ጊራራ እና ላሊበላ ይገኙበታል፡፡

በአዲስ አበባ ፤ ሐዋሳ ፤ ድሬደዋ ፤ መቐለ ፤ ደሴ ፤ አዳማ ፤ በመሳሰሉት ከተሞች ቀለበታዊ ግረዶሽ ባይኖርም ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ግን ይኖራቸዋል - #ESSS

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ግርዶሹ ጀምሮ እስኪጠናቀቅ ስንት ሰዓት ይፈጅበታል ?

በኢትዮጵያ የሚከሰተው ግርዶሽ መታየት ከሚጀምርበት ምእራብ ኢትዮጵያ (ከጠዋቱ 12:50 ሰዓት) ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ግርዶሹ እስከሚጠናቀቅበት ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ (ከጥዋቱ 3:25 ሰዓት) በአጠቃላይ 2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ ይፈጅበታል።

ዋናው "ቀለበታዊ ግርዶሽ" በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች ውስጥ በተለያየ ሰዓት የሚታይ ሲሆን ለምሳሌ ወለጋ አካባቢ ከጥዋቱ 1:55 ሰዓት ላይ (ለ1 ደቂቃ ከ12 ሴኮንድ) ፣ ላልይበላ ከጥዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ (ለ1 ደቂቃ ከ8 ሴኮንድ) እንዲሁም አፋር ላይ ከጥዋቱ 2:03 (ለ1 ደቂቃ ከ6 ሴኮንድ) ይታያል - #ESSS

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#REPOST

የፀሐይ ግርዶሽ እና ጥንቃቄ!

የፀሐይ ግርዶሽን በዓይን በቀጥታ መመልከት ቋሚ ጉዳት በዓይን ላይ ያደርሳል። ግርዶሹን ለመመልከት ፦

1. ደረጃውን የጠበቀ የግርዶሽ መነፅር መጠቀም

2. ፒን ሆል ካሜራ ወይም በአነስተኛ ቀዳዳ ወደ ድፍን ካርቶን የሚገባውን ብርሃን የሚስለውን ስእል ጀርባ ለፀሐይ በማዞር መመልከት

3. ጨለማ ክፍል ውስጥ በቀዳዳ የሚገባውን የፀሐይ ብርሃን መሬት ወይም ግድግዳ ላይ የሚሰራውን ስእል መመልከት

4. በዛፎች ቅጠል አልፎ መሬት ላይ የሚያርፈውን የፀሐይ ስእል መመልከት

5. ለቴሌስኮፕም ሆነ ባይነኩላር የፀሐይ ብርሃን መጣኝ ደረጃውን የጠበቀ ፊልተር ግጥሞ መመልከት

6. ግርዶሹን የሚያሳዩ የቀጥታ ስርጭቶችን መመልከት

የፀሐይ መነፅር ፣ ፍሎፒ ዲስክ ፣ የፎቶ ፊልም ፣የራጅ ፊልም እና የመሳሰሉት ቁሶች መጠቀም በዓይን ላይ ጉዳት ያደርሳል - #ESSS

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጸሃይ ግርዶሽ ምንድነው ?

ፀሐይ ግርዶሽ ጨረቃ በፀሐይ እና መሬት መሃከል ስትገባና ፀሐይን እንዳናያት ስትጋርድብን የሚከሰት ክስተት ነው።

የጸሃይ ግርዶሽ አይነቶች ስንት ናቸው ?

'ሙሉ የፀሐይ ግርዶች' የምንለው ጨረቃ ጸሃይን ሙሉ ለሙሉ የምትጋርድ ከሆነ ሲሆን ጨረቃ ከፊሉን የፀሐይ ክፍል ብቻ የምትጋርድብን ከሆነ 'ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ' (Partial Solar Eclipse) ይባላልም

ጨረቃ ፀሐይን ሙሉ ለሙሉ መሸፈን ሳትችል ስትቀርና በጨረቃ ጠርዝ ዙሪያ ቀለበት ሠርታ ፀሐይ የምትታየን ከሆነ 'ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ (annular solar eclipse)' ይባላል።

ነገ በሀገራችን የምናየው ግርዶሽ ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ የሚባለውን ነው - #ESSS

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የነገው ግርዶሽ የትና ስንት ሰዓት ?

ነገ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል ፀሐይ ከ60-80 ፐርሰነት ተሸፍና ከፊል ግርዶሽ ይታያል፡፡

ከ80 ፐርሰነት በላይ ያለው ዋናው ግርዶሽ ግን ከምዕራብ ኢትዮጵያ አንሥቶ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ በሚገኝ ስፍራ ጎልቶ ይታያል፡፡

ግርዶሹ መታየት ከሚጀምርበት ምእራብ ኢትዮጵያ (ከጠዋቱ 12:50 ሰዓት) ጀምሮ ግርዶሹ እስከሚጠናቀቅበት ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ (ከጥዋቱ 3:25 ሰዓት) በአጠቃላይ 2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ ይፈጅበታል።

ቀለበታዊ ግርዶሽ ማየት ከሚችሉ አነስተኛ ከተሞች/ቦታዎች ቤጊ ፣ ሜቲ፣ መንዲ ፣ ጫልቱ ፣ ቡሬ ፣ አገው ግምጃቤት ፣ እንጅባራ ፣ ግሽ አባይ፣ ሞጣ ፣ ዳሞት ፣ ጋይንት ፣ ንፋስ መውጫ ፣ ጋሸና ፣ ሙጃ ፣ ዋጃ ፣ ቆቦ ፣ ኮረም፣ አላማጣ ፣ ጊራራ እና ላልይበላ ይገኙበታል፡፡

በአዲስ አበባ ፤ ሐዋሳ ፤ ድሬደዋ ፤ መቐለ ፤ ደሴ ፤ አዳማ ፤ ባህር ዳር በመሳሰሉት ከተሞች ቀለበታዊ ግረዶሽ ባይኖርም ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ግን ይኖራቸዋል።

ከላይ ባለው ምስል ግርዶሹ የሚጀምርበትን ሰዓት ፣ ቀለበት ካለ ቀለበት የሚታይበትን ሰዓት ፣ ግርዶሹ የሚያልቅበት ሰዓት እንዲሁም ጸሃይ የምትሸፈንበትን መጠን መመልከት ትችላላችሁ - #ESSS

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሰማይ ላይ ያየነዉ እንግዳ ነገር ፍርሀት ዉስጥ ጥሎናል " - ነዋሪዎች ዛሬ ምሽት በበአርባ ምንጭ ፣ ወላይታ ሶዶ ፣ ቡርጂ ፣ ሱሮ ባርጉዳ (ምዕራብ ጉጂ ዞን) እና ሌሎችም በርካታ ስፍራዎች በሰማይ ላይ የታየዉ ተምዘግዛጊ ሮኬት መሳይ ተቀጣጣይ ነገር ፍርሃት አንደጫረባቸዉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ " ምሽት 2 ሰዓት ገደማ ሮኬት መሳይ ተቀጣጣይ ብርሃናማ ነገር በሰማይ…
" የማጣራት ሥራውን እስክናጠናቅቅ ሁሉም ሰው በተረጋጋ መንፈስ እንዲጠባበቅ በትህትና እንጠይቃለን " - የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ

የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 1፡30 ገደማ በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቁስ አካላት ስብስብ መታየታቸው ሪፖርት እንደደረሰው ዛሬ ጥዋት አሳውቋል።

" በደረሰን ተንቀሳቃሽ ምስል ለመመልከት እንደቻልነው የእነዚህ አካላት ስብስብ የጠፈር ፍርስራሾች አልያም የሚቲዮር አለቶች ይመስላሉ " ብሏል።

" ስብስቡ ወደ ደቡባዊ የሃገሪቱ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት በሰማይ ላይ ሲምዘገዘግ እንደነበረም ለማወቅ ተችሏል " ሲል አክሏል።

" የክስተቱን ተፈጥሮ በእርግጠኝነት ለማብራራት ያስችለን ዘንድ ሁኔታውን በቅርበት እያጣራን የምንገኝ ሲሆን ፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እንደደረሱን የምናቀርብ ይሆናል " ብሏል።

" የማጣራት ሥራ እንኪጠናቀቅ ድረስ  ሁሉም ሰው በተረጋጋ መንፈስ እንዲጠባበቅ በትህትና እንጠይቃለን " ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

#ESSS

@tikvahethiopia