TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በአዲስ አበባ በሞተር ብስክሌት በመታገዝ የቅሚያ ወንጀል ከፈፀሙ ግለሰቦች መካከል ግማሽ ያህሉ #መያዛቸውን የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የኢንዶክትሬሽንና ህዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር #ፋሲካ_ፈንታ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ 61 በሞተር ሳይክል የተደገፈ ቅሚያ በከተማዋ ተፈፅሟል።

ወንጀሉ የተፈፀመው በከተማዋ በሚገኙ 8 ክፍለ ከተሞች መሆኑንም ተናግረዋል።
ከፍተኛ የቅሚያ ወንጀል የተፈፀመበት የቦሌ ክፍለ ከተማ 21 በሞተር ሳይክል የተደገፉ ወንጀሎች የተፈፀመበት ሲሆን ዝቅተኛ የቅሚያ ወንጀል በተፈፀመበት ልደታ ክፍለ ከተማ አንድ ወንጀል ተፈጽሟል።

በአቃቂ ቃሊቲና ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች ምንም አይነት በሞተር ብስክሌት የተደገፈ ቅሚያ አለመፈጸሙን ገልጸዋል።
ወንጀል ፈፃሚዎቹ በራሳቸውና በተከራዩት የሞተር ብስክሌት የቅሚያ ወንጀሉን እየፈፀሙ መሆኑን የገለፁት ኮማንደር ፋሲካ ወንጀሉን ፈጽመው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች በፍርድ ቤት ጉዳያቸው እንደተያዘና ቀሪ የወንጀል ፈጻሚዎች ለመያዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

ፖሊስ የሚያከናውነውን ወንጀል የመከላከል ተግባር ኅብረተሰቡ ወንጀል ፈፃሚዎችን #የማጋለጥና ወንጀል የመከላከል ስራው እንዲደግፍ ጥሪ አቅርቧል።

”ወንጀልን መከላከል በፖሊስ ጥረት ብቻ የሚከወን አይደለም” ያሉት ኮማንደር ፋሲካ የኅብረተሰቡ ድጋፍ ከተጠናከረ ወንጀል ፈፃሚዎች ሊያመልጡ እንደማይችሉም ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ከቅሚያ ወንጀሉ በተጨማሪ ሌሎች የትራፊክ ደንብ ጥሰቶችን የፈፀሙ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ላይም እርምጃ መወሰዱን ኮማንደሩ ተናግረዋል።

#ሀሰተኛ_መንጃ_ፈቃድ ይዘውና ያለመንጃ ፍቃድ ሞተር ብስክሌት ሲያሽከረክሩ የነበሩ እንዲሁም ሲያሽከረክሩ ማሟላት የሚገባቸውን እንደሄልሜት ያሉና ሌሎች የትራፊክ ደንብ ጥሰት የፈፀሙ ከ7ሺህ በላይ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia