TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ወጣቶቻችን😥

" ከአንድ ወረዳ ብቻ ከ2 ሺህ በላይ ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰደው 200 ያህሉ ለህልፈት ተዳርገዋል " - የእገላ ወረዳ አስተዳደር

እገላ ከትግራይ ማእከላዊ ዞን ወረዳዎች አንድዋ ስትሆን የኤርትራዋ ፆሮና ጎረቤት ናት።

ከትግራዩ ጦርነቱ በፊት የወረዳዋ ዋና ከተማ በሆነችው ገርሁስርናይ በቀን በርካታ የኤርትራ ስደተኞች በህገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚተላለፉባት ነበረች።

ከጦርነቱ በኋላ በእገላ ወረዳ በተለይ በገርሁስርናይ ከተማ ብዙ ነገሮች ተቀያይረዋል።

ወረዳዋ በተለይ ከተማዋ በከፍተኛ ሁኔታ ወድመዋል።

አሁንም ድረስ ወረዳዋ በኤትርራ ድንበር የምትገኝ በመሆንዋ የተሟላ ፀጥታ አላት ለማለት ያስቸግራል ይላሉ የአከባቢው ነዋሪዎች።

በወረዳዋ የሚታየው ህገ-ወጥ ስደት እጅግ አስደንጋጭና አስፈሪ መሆኑ የአደጋው ሰለባዎች እና የመንግስት አካላት ጭምር ይናገራሉ።

አቶ ዘርኢሰናይ መንግስቱ የተባሉ የገርሁስርናይ ከተማ ነዋሪ ለትግራይ የመገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ሬድዮ ባጋሩት መረጃ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ሹፌር በመሆን ሲተዳደር የነበረው የ22 ወጣት ልጃቸው ህገ-ወጥ ስደት ተነጥቀዋል።

ከእገላ ወረዳ አስተዳደር የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ባለፈው 2016 ዓ/ም የመጨረሻ ወራት ብቻ 192 ሴቶች የሚገኙባቸው ከ 2 ሺህ በላይ  ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰደው ከ1300 በላይ በስደት በተጓዙበት አገር ፓሊስ በአጭር ጊዜ ተይዘው ሲመለሱ 200 የሚያህሉ ግን ለህልፈት ተዳርገዋል።

የወረዳው ከፍተኛ አመራር ፅጌ ተ/ማርያም እንዳሉት፤ በአከባቢው የሚታየው ህገ-ወጥ የስደት ፍልሰት እጅግ አስፈሪና አስደንጋጭ ነው።

ወረዳው ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ይህ ነው የሚባል በጀት ያለው ባይሆንም የወጣቶች ስደት ለማስቀረት ያለመ የመስሪያ ቦታ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተያዘው የበጀት ዓመት የህገ-ወጥ ስደት ፍልሰት በከፍተኛ ቁጥር ለመቀነስ ወረዳው አቅዶ እየሰራ ነው።

ይሁን እንጂ ጦርነት ወለዱ የበጀት እጥረት ለተያዘው እቅድ መሳካት ሳንካ ሊሆን ስለሚችል በወጣቶች አቅም ግንባታ እና ህገ-ወጥ ስደት መከላከል ዙሪያ የሚሰሩ ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች እንዲያግዙዋቸው ሃላፊው ጥሪ አቅርባዋል።

#Ethiopia #TigrayRegion

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ወጣቶቻችን😥 " ከአንድ ወረዳ ብቻ ከ2 ሺህ በላይ ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰደው 200 ያህሉ ለህልፈት ተዳርገዋል " - የእገላ ወረዳ አስተዳደር እገላ ከትግራይ ማእከላዊ ዞን ወረዳዎች አንድዋ ስትሆን የኤርትራዋ ፆሮና ጎረቤት ናት። ከትግራዩ ጦርነቱ በፊት የወረዳዋ ዋና ከተማ በሆነችው ገርሁስርናይ በቀን በርካታ የኤርትራ ስደተኞች በህገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚተላለፉባት ነበረች።…
#ወጣቶቻችን😭
 
" በሶስት ወራት ብቻ ከ6,600 በላይ ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰድዋል !! " - የትግራይ የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ

በትግራይ ክልል ከተሞች በሚገኙ አውራ መንገዶች " ልጄ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ስደት ሲሄድ በአጋቾች ተይዞ ይህንን ብር ክፈል ፣ ካልከፈልክ ትገደላለህ ብለውኛል እርዱኝ " የሚሉ በትልቅ ባነር በተቀመጠ የወጣቶች ፎቶ አስደግፈው እርዳታ የሚለሙኑ ወላጆች ተበራክተዋል። 

ከነዚሁ ወላጆች የአክሱም ከተማ ነዋሪዋ ወ/ሮ ኣስካለ ውብኣንተ አንድዋ ሲሆኑ ፤ ይጦረኛል ብለው ኮስኩሰው አስተምረው ያሳደጉት ወንድ ልጃቸው ህገ-ወጥ ስደት የነጠቃቸው እናት ናቸው። 

" ልጄ በጦርነቱ ማግስት በአከባቢው የስራ እድል በማጣቱ በህገ-ወጥ መንገድ የተለያዩ ሃገራት ደንበር አቋርጦ ሊብያ ሲደርስ ለሰው ህይወት ቁብ በሌላቸው ሽፍቶ እጅ ወድቆ ቁም ስቅሉን እያሳዩት ነው " ብለዋል።

" አካል ጉዳተኛ ነኝ  ፤ ልጄ እኔ እናቱን ለመጦር ዳቦ መጋገሪያ ቤት ከፍቶ የነበረ ቢሆንም ንብረቱ መዘረፉ አናድዶት ነው በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ስደት የሄደው " ወ/ሲሉ እኚሁ እናት እንባ እተናነቃቸው ተናግረዋል።

" ልጄ በአጋቾች ቁጥጥር ስር ውሎ ጥዋት እና ማታ በሚደርስበት ገርፋት እየተሰቃየ ሲያናገርኝ የምይዘው የምጨብጠው ይጠፋብኛል ፤ ' የጠየቁኝ ብር ካልተከፈለ ኩላሊቴ ያወጡታል ምን ማድረግ ነው ያለብኝ ? ' ካለኝ ቀንና ሰዓት ጀምሮ አእምሮየ ልክ አይደለም " ብለዋል።

" ልጄ በመጀመሪያው አከባቢ በሙሉ  ጤንነት እያለ 1.5 ሚሊዮን ብር እንድከፍል ጠየቁኝ  ደጋግመው ደብድበው አካል ጉዳተኛ እና በሽተኛ ካደረጉት በኋላ ግን 300 ሺህ ቀንሰው 1.2 ሚሊዮን ብር ጠይቀውኛል። ይህንን ገቢ ካላደረግኩ ድግሞ እንገድለዋለን ብለውኛል እባካችሁ አርዱኝ " ሲሉ ተማፅነዋል።

ወ/ሮ አስካለ ልጆቻቸው የህገ-ወጥ ስደት ገፋት ቀማሽ ሆኖውባቸው ሌት ተቀን ከሚያለቅሱ በሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ እናቶች አንድዋ ናቸው።

እሳቸው ለሚድያ ቃላቸው በሰጡባት ቀን ሰዓትና ደቂቃ ሳይቀር በተለያዩ አቅጣጫዎች በርካታ ወጣቶች በአከባቢያቸው ተስፋ ሰጪ ሁኔታ በማጣት እግራቸው ወደ መራቸው ይሰደዳሉ።  

የትግራይ የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ሓይሽ ስባጋድስ ፣ የህገ-ወጥ ስደቱ ዋና መነሻ የሰራ እና መልካም አስተዳደር እጦት መሆኑ ገልጸዋል።

ወጣቶች በነዚህና ሌሎች ችግሮች ተማረው አደገኛ የሆነውን ስደት በመምረጥ ለተለያዩ አደገኛ ነገሮች እየተጋለጡ እንደሆነ አስረድተዋል።

በቢሮቸው የተካሄደው ዳሰሳ እንደሚያመለክተው ከሓምለ 2016 አስከ መስከረም 2017 ዓ.ም ባሉት ሦስት ወራት ብቻ በክልሉ ማእከላዊ ፣ ምስራቅ እና ሰሜናዊ ምዕራብ ከሚገኙ 11 ወረዳዎች ከ6,600 በላይ ወጣቶች በህገ-ወጥ መንገድ ተሰደዋል ሲሉ ገልጸዋል።

" የትግራይ የፓለቲካ አመራሮች ከገቡበት የስልጣን መቆራቆስ በመውጣት በህገ-ወጥ ስደት ለከፍተኛ አደጋ እና እልቀቂት የተጋለጠውን የወጣቱን ክፍል ለመታደግ ቅድሚያ መስጠት አለባቸው " ብለዋል። 

የመረጃው ምንጭ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ እና ትግራይ ቴሌቪዥን የህዳር 17/2017 ዓ/ም የዜና ዘገባ ናቸው።

@tikvahethiopia