TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንጀለኞች መሸሸጊያ የላቸውም...

#በኢትዮጵያ_ወንጀል_ሰርተው በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የትም ሆነ የት መሸሸጊያ ያላቸውን እጃቸውንም #አንጠልጥዬ ለኢትዮጵያ መንግስት አስረክባለሁ ሲል አለም አቀፍ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል ማስተማመኛ ሰጠ፡፡

ትናንትና አዲስ አበባ የመጡት የኢንተርፖል ዋና ሀላፊ ዶ/ር ጀርጋን ስቶክ ከፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ነው ወሬው የተሰማው፡፡

ከንግግሩ በኋላ መግለጫ የሰጡት ኮሚሽነር ጀነራል #እንዳሻው_ጣሰው በኢትዮጵያ ወንጀል ሰርተው በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያንን ኢንተርፖል ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንደሚሰጥ ማስተማመኛ ሰጥቷል ብለዋል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራሉ በሰብአዊ ፍጡር ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙና ሀገር የዘረፉ ሰዎች ግማሾቹ በሀገር ውስጥ ግማሾቹ ደግሞ ባህር አቋርጠው በውጭ አገር እንደሚኖሩ ታውቋል ብለዋል፡፡

ይህንን ወንጀል ፈፃሚዎቹ የትም ይደበቁ የትም ይኑሩ ኢንተርፖል እጃቸውን አንጠልጥሎ ለኢትዮጵያ መንግስት እንደሚያስረክብ ሀላፊው አረጋግጠውልናል ሲሉ መናገራቸውን ከመንግስታዊ ምንጮች ስምቻለሁ ብሎ ሸገር ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሰሞኑ ባስተላለፉት መልዕክት በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች ማንም ይሁን ማን ከየትኛውም ብሔር ገብተው ይደበቁ፣ የትኛውም ወገን ይጩህላቸው በወንጀል እስከተጠረጠሩ ድረስ ካሉበት አድነን ለህግ እናቀርባቸዋልን ማለታቸው
ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌደራል ፖሊ ስ‼️

በአንዳንድ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶችን ከሕብረተሰቡ ጋር #በመወያየትና #በመተማመን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል #እንዳሻው_ጣሰው ለኢዜአ እንደገለጹት ፖሊስ በተለያዩ ቦታዎች የሚነሱ ግጭቶችን ለማስቆም እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ በውይይቶች እንዲፈቱ እያደረገ ነው።

በአንዳንድ ቦታዎች ግጭቶች ሲፈጠሩ ከመስመር የወጡና የተበላሹ ጉዳዮች እንዲስተካከሉ ለማድረግ በየደረጃው ውይይቶች እየተካሔዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሕዝቡን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የሚመሩ አካላት እንዲስተካከሉም በየደረጃው የሚገኙ የፀጥታና ባለድርሻ አካላት እየሰሩ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ይህ የሚሆነው እነዚህ ተሰሚነት ያላቸው አካላት ለህብረተሰቡ ቅርብ በመሆናቸው ችግሩ በእነርሱ አማካኝነት እንዲፈታና የተባባሰ ግጭት እንዳይመጣ መሆኑን አመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅት በሕብረተሰቡና በፖሊስ መካከል መተማመንን የሚሸረሽሩ ተግባራትን ለመከላከል ለውጡን ተግባራዊ ማድረግ የግድ መሆኑን ጠቁመዋል።

የፌዴራል ፖሊስ ከሕብረተሰቡና በየደረጃው ካሉ የፀጥታ መዋቅር አደረጃጀት ጋር በመሆን ሰላምና ደሕንነት ለማስጠበቅ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች ሕብረተሰቡን ነፃ ለማውጣት ነው የምንታገለው በማለት የሚንቀሳቀሱ አካላት መኖራቸውን ጠቅሰው ከተነሱበት ዓላማ ውጭ በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ዝርፊያ ሲገቡ መስተዋሉን ነው የጠቆሙት።

በተለያዩ ቦታዎች ፖሊስ ለሚያከናውነው ሰላምን የማስከበር፣ ሕገ-ወጦችን በቁጥጥር ስር የማዋልና ፀጥታ የማስፈን ስራ ሕብረተሰቡ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም አመልክተዋል።

በተለይ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ሕብረተሰቡና ፖሊስ በሚያደርገው ክትትል አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ሲሆን ይሕ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን‼️

የፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸውን እንደደረሰበትና ከፈፃሚዎቹ ጥቂቶቹን #በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል #እንዳሻው_ጣሰው እንደገለጹት፥ በተለያዩ አካባቢዎች የፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸው ተደርሶበታል።

በዚህ የወንጀል ተግባር ላይ ከተሳተፉት ውስጥም ጥቂቶቹም በቁጥጥር ስር መዋላቸወን አስታውቀዋል።

የወንጀሉ ፈፃሚዎች የፖሊስን የደንብ ልብስ በተለያየ መንገድ በእጃቸው እንደሚያስገቡ የጠቆሙት ኮሚሽነር ጄነራል እንዳሻው፥ የወንጀሉ ተሳታፊዎችን በማጋለጥ በኩል ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ሰራዊት ዩንፎርም ጋር ተመሳሳይነት ካላቸው የጎረቤት አገራትም የደንብ ልብሱ ለወንጀል መፈፀሚያነት ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ እንደሚችልም ጠቁመዋል።

በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ እየሰሩ ያሉ ጥቂት ግለሰቦችም በወንጀል ድርጊቱ ተሳታፊ ሆነው በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን በማጋለጥና ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል።

ፖሊስ በተያዘው ወር ለሚካሔዱት የጥምቀት በዓልና የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባም ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጉን ገልፀዋል።
ለዚህም ስኬት ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩንና እንግዳ ተቀባይነቱን እንዲያሳይ በማለት ኮሚሽነሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia