TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሶማሊያ ካቢኔ በነገው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ እንደተጠራ ተሰምቷል። አስቸኳይ ስብሰባው ፤ ዛሬ በሶማሌላንድ (ሶማሊያ ሶማሌላንድን እንደ ሰሜናዊ ክልሏ ነው የምትቆጥራት) እና በኢትዮጵያ መካከል ተደርጓል ስለተባለው ስምምነት በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ ለማሳለፍ ነው ተብሏል። ከዚሁ ከነገው አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ ዝግጅት ጋር በተያያዘ #በአሁን_ሰዓት በሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት…
#Update #Seaport

ሶማሊያ በኢትዮጵያ ያሉትን አምባሳደሯን ጠራች።

ሶማሊያ እንደ ራሷ ግዛት በምታያት ሱማሊላንድ እና ኢትዮጵያ መካከል ትላንት በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ እንዳስቆጣት መነገሩ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ከኢትዮጵያ አምባሳደሯን ለምክክር በሚል ጠርታለች።

የሀገሪቱ ካቢኔ ዛሬ ማክሰኞ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ፦
- የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት)
- አፍሪካ ህብረት
- ኦአይሲ
- ኢጋድ
- አረብ ሊግ ጣልቃ እንዲገቡ ጥሪ አቅርቧል።

በተጨማሪ የሶማሊያ ካቢኔ በሶማሌላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ለወደብ አጠቃቀም የተፈረመው ስምምነት " ዋጋ ቢስ እና ህጋዊ መሰረት የሌለው " ነው ማለቱ ተነግሯል።

ካቢኔው የኢትዮጵያ እርምጃ የቀጠናውን መረጋጋት እና ሰላም አደጋ ላይ የሚጥል ነው ማለቱም ተዘግቧል።

የካቢኔውን ስብሰባ የመሩት ጠ/ሚ ሃምዛ አብዲ ባሬ " ሉዓላዊነታችንን ለመጠበቅ ቁርጠኛ ነን " ብለው " ማንም የሶማሊያን የመሬት፣ የባህር እና የአየር ክፍል ሊጥስ አይችልም " ሲሉ ተደምጠዋል።

ራስ ገዟ ሶማሌላንድ ለሶስት አስርት ዓመታት ዓለም አቀፍ እውቅናን ማግኘት ያልቻለች ሲሆን ከኢትዮጵያ ጋር ባደረገችው ስምምነት ኢትዮጵያ በሊዝ የባህር ኃይል እና የንግድ የባህር በር እንዲኖራት አድርጋ በምላሹ እውቅናን ትጠብቃለች። ከዚህ ባለፈ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ ይኖራታል።

ለሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ቅርብ የሆኑ ምንጮች ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በይፋ ይቅርታ ካልጠየቁ እና ለሶማሊያ ልዓላዊነት ክብር ካልሰጡ ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን #እንደምታቋርጥ እየገለፁ ናቸው።

@tikvahethiopia