TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጣና ሐይቅን የወረረው የእምቦጭ አረም ስጋት ሆኖ ቀጥሏል!

ጣና ሐይቅን የወረረው የእምቦጭ አረምን ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ ባይቻልም እንኳን፣ መስፋፋቱ እንዲገታ ለማድረግ የሚረዱ እንቅስቃሴዎች ባሉበት መቆማቸውን የአማራ ክልል የአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ባለስልጣን ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስታውቋል፡፡

አረሙን በጢንዚዛ ለማጥፋት የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ያደረገው ጥናት ተጠናቆ፣ ምርምሩ ተሠርቶና ጥንዚዛዎቹ የት ቦታ ይለቀቁ የሚለው ሁሉ የተለየ ቢሆንም፤ ገና ተግባራዊ እንዳልሆነ ምርምሩን በበላይነት የሚመሩት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ጌታቸው በነበሩ (ዶ/ር) ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስረድተዋል፡፡

እንደ ጌታቸው ገለጻም፣ የተደረገው ጥናት ተግባራዊ እንዳይሆን ካደረጉት ችግሮች መካከል፣ በጥናት መፍትሔ ይሆናል ለተባለው የጢንዚዛ ማራቢያ ማዕከል መገንባት ያለመቻሉ ነው። ግንባታውን ታሳቢ ያደረገ ጨረታ የወጣ ቢሆንም፣ በጨረታው የቀረበው ዋጋ ከተገቢው በላይ ከፍተኛ መሆኑ የእንቦጭ አረምን ለመግታት የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንደገታው ነው አያይዘው ያነሱት። ‹‹እንቦጭን በቀላሉ ለማጥፋት እንዳይቻልና ስጋት ሆኖ እንዲቀጥል አድርጎታል›› ብለዋል።

#አዲስማለዳ_ጋዜጣ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-29-2
በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ የ10 ሰው እና የ10 ዝሆኖች ህይወት አለፈ!

በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ በህገ-ወጥ እርሻና ሰፈራ መስፋፋት እንዲሁም ህገ ወጥ አደን ሳቢያ የተቆጡ ዝሆኖች በ2011 14 ሰዎችን ያጠቁ ሲሆን ስድስቱ ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል። ሌሎች አራት ሰዎችም በተለያየ ጊዜ በደረሰባቸው ጥቃት ህይወታቸው ሲያልፍ በተመሳሳይም አራት ግለሰቦች ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።

አስር ዝሆኖች በአንድ ዓመት ውስጥ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ሦስቱ ግልገሎች መሆናቸውን የመጠለያው ኃላፊ አደም ሞሐመድ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ገልጸዋል። ሰባቱ አዋቂ ዝሆኖችም በህገወጥ አደን ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ ግልገሎቹ በአካባቢው በሰፈሩት ሰዎች በመረበሻቸውና ለጭንቀት በመዳረጋቸው መሞታቸውን ገልጸዋል።

Via #አዲስማለዳ_ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia