TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በኢንተር ኮንቲኔታል በተካሄደው የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር #ታከለ_ኡማ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ #ለባለእድለኞች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ልማትን በጋራ መጠቀም ተገቢ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው፣ በቤቶቹ ግንባታ ከይዞታቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ለከፈሉት #መስዕዋትነት ዋጋቸውን እንደሚያገኙም አመልክተዋል፡፡ በዚህም ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ልማት ሲባል ከመሬታቸው ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች #ያለእጣ ቤት #እንዲሰጣቸው የከተማ አስተዳደሩ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ‼️
(20/80ና 40/60)

የ20/80ና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ይፋ ከመሆን ጋር ተያይዞ ቦታው የኦሮሚያ ነው በሚል ከ10 በላይ በሚሆኑ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ተቃውሞዎች ተቀስቅሰዋል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ የተገነቡባቸው አካባቢዎች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሆነው የአዲስ አበባ መስተዳድር ውሳኔ የሚያሳልፈው እንዴት ነው፤ ለተፈናቃዮቹ አርሶ አደሮች የተሰጠው ካሳ እዚህ ግባ የማይባል ነው፤ የተቀናጀው ማስተር ፕላን ቅጥያ ነው የሚሉ ሀሳቦችን ተቃዋሚዎቹ አንስተዋል።

#በምስራቅ_ኦሮሚያ ጪሮ ከተማ ቢቢሲ ያነጋገረው አንድ ሰልፈኛ " በዚህ ተቃውሞ ላይ ዋነኛ መልዕክታችን በአዲስ አበባ አካባቢ ያሉት መሬቶች ለኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ሊመለስ ይገባል" የሚል ነው። ተቃዋሚው ጨምሮም ለብዙዎች ሞት ምክንያት የሆነው አወዛጋቢው የተቀናጀ ማስተር ፕላን ሊመለስ አይገባም ብሏል።

ተቃውሞዎቹ በሻሸመኔ፣ ጪሮ፣ ጂማ፣ አሰላ፣ አዳማና ሂርና ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተስፋፉ ሲሆን በሻሸመኔ አካባቢ የሚገኙ ሰልፈኞች "ኦዲፒ ያልነውን ረስታችሁታል፤ መሬታችን የደም ስራችን ነው" የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ነበር።

በትናንትናው ዕለት 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል የዕጣ ማውጫ ስነ ስርአት ለተጠቃሚዎች የተላለፈ ሲሆን፤ ከአካካቢው ለተነሱ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ያለ እጣ እንዲሰጣቸው በከተማው አስተዳደር ካቢኔና በቤቶች አስተዳደር ውሳኔ መሰረት ያለ ዕጣ እንዲተላለፍ መወሰኑን ምክትል ከንቲባ #ታከለ_ኡማ በትናንትናው ዕለት ገልፀዋል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ሲገነቡ የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ ያልደበቁት ምክትል ከንቲባው "በተለይም የእርሻ መሬታቸውን ለነዚህ ተግባራት ሲሉ የለቀቁና ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ቀውስ የተዳረጉ የአርሶ አደር ቤተሰቦችና ልጆቻቸው ህመማችሁ የእኛ መሆኑን እንድታውቁ" የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ከንቲባው ይህንን ቢሉም ኦሮሚያ ውስጥ ተቀስቅሶ ለረጅም ጊዜ ለዘለቀው ሕዝባዊ ተቃውሞ መነሻ ምክንያት እንደሆነ የሚነገርለትና ከ2006 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የአዲስ አበባና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ቅጥያ ነው የሚሉ ትችቶችም እየተሰሙ ነው።

ምንም እንኳን የተቀናጀው ማስተር ፕላን ከፍተኛ ተቃውሞዎችን ተከትሎ ውድቅ ቢደረግም የቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባና ኦህዴድ ሊቀ መንበር አቶ ኩማ ደመቅሳ ጉዳዩ ከመፈናቀል ጋር አብሮ ስለመጣ እንጂ "ተራማጅ አስተሳሰብ ነው ብዬ አስባለሁ፤ ጊዜ ሊወስድ ይችላል እንጂ ማስተር ፕላኑ አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል" ብለው ለቢቢሲ መናገራቸው የሚታወስ ነው።

ምንም እንኳን ከመንግሥት በኩል ምንም አይነት መግለጫ ባይሰጥም በቅርቡ ከውጭ ሀገር የተመለሰው የተባበሩት ኦነግ በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ያለውን ድንበር መወሰን ያለበት የኦሮሚያ ክልል ነው የሚል ነው።

በ13ኛው ዙር የ20/80 ቤቶች 32ሺ 653 ቤቶችና በ2ኛ ዙር የ40/60 ቤቶች ለተጠቃሚዎች የሚተላለፉ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ 1ሺ 248 ስቱዲዮ፣ 18ሺ 823 ባለ አንድ መኝታ፣ 7ሺ 127 ባለሁለት መኝታ እና 5ሺ455 ደግሞ ባለ ሶስት መኝታ መሆናቸው ተገልጿል።

በ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ የሚካተቱትም በ1997 ተመዝግበው በ2005 ዓ.ም በነባር መደብ የተመዘገቡና በ2005 ዓ.ም የአዲስ ባለ ሶስት መኝታ ተመዝጋቢ ደንበኞች መሆኑ ተገልጿል።

Via BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ የስራ መልቀቂያ አስገብተዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ዜና ሀሰት ነው። ምክትል ከንቲባው የስራ መልቀቂያ አላስገቡም፤ በዛሬው ዕለትም በስራ ገበታቸው ላይ ነበሩ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፈ ጉባኤ #ታገሰ ለምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ የፃፉት ማሳሰብያ!

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ከትናንት በቀን 27/06/2011 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ ለምክር ቤቱ እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ግንባታ ተብሎ የተተወውን ባሻ ወልዴ ሰፈር ያለውን ቦታ ለመናፈሻ አገልግሎት መዋሉን ተችተው በቦታው ያለው እንቅስቃሴ #እንዲቆም አሳስበዋል።

Via Elias Mesret & Zinashi Tadesse
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ ከአዲስ አበባ ህዝብ የተሰበሰበውን #ድጋፍ ለማስረከብ #ጌዴኦ ገብተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት...

(ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ)
#STOP_HATE_SPEECH

በሀገር አቀፍ ደረጃ TIKVAH-ETH "የፀረ ጥላቻ ንግግር" ዘመቻ በማካሄድ ላይ ይገኛል። በተለይም በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ያሉ የጥላቻ ንግግሮች ሀገራችንን #ወደማትወጣው መከራ ውስጥ የሚከታት በመሆኑ ጊዜው ሳይረፍድ ይህን እኩይ ተግባር በጋራ መዋጋት ያስፈልጋል።

በቅድሚያ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀገራችን ወጣቶች በሚገኙባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ትኩረት በማድረግ የጥላቻ ንግግር ሊያመጣ የሚችለውን ችግር የማስገንዘብ ስራ እየሰራን እንገኛልን።

ሀሳቡን ካቀረብንላቸው የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ሀሳቡን በመደገፍ እንዲሁም ዘመቻውን ለማገዝ ፍቃደኝነቱን ያሳየን #የመጀመሪያውን ተቋም ነው። በዚህ አጋጣሚ በዶክተር #ታከለ ለሚመራው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እንዲሁም #ለተማሪዎች_ህብረቱ ያለንን ላቅ ያለ ምስጋናና ክብር እንገልፃለን!!
.
.
.
ውድ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኑ ...3 ተከታታይ ምሽቶችን ከTIKVAH-ETH ጋር አሳልፉ! ስለጥላቻ ንግግሮች እና ከጊዜ ወደጊዜ እየከፋ ስለመጣው አግባብነት የሌለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እንነጋገር! የሀገራችሁ ጉዳይ ካሳሰባችሁ ሀሳባችሁን ስጡ...የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ጠቁሙ!

ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ በተከታታይ!

🔹ቦታ - ዋናው ግቢ(በተማሪዎች መግቢያና መውጫ በር አካባቢ)

⌚️ሰዓት - ከምሽቱ 12:30 ጀምሮ

እንግዶች ይኖራሉ!!

#በፍቅር ኢትዮጵያን እንገንባ!!
ከጥላቻ ንግግሮች #እንቆጠብ!!

(የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት)

በቀጣይ፦

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
አምቦ ዩኒቨርሲቲ
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
መቀለ ዩኒቨርሲቲ
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

#ለቀጣዩ_ትውልድ ከጥላቻ የራቀችን ሀገር እናወርሳለን! ሀሳቡን ለመደገፍ የምትፈልጉ፦
0919 74 36 30 @tsegabwolde

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዕጣ የወጣባቸው #የኮዬ_ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሚቀጥለው ሳምንት ለባለዕድለኞች ይተላለፋሉ‼️
.
.
#በድሃ ገንዘብ የተሠራ ነው፤ ቤቶቹን ባለዕድለኞች ከማስተለለፍ የሚያግደን ነገር የለም” - ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
.
.
በወሰን ይገባኛል ውዝግብ እጣ ለወጣላቸው ዕድለኞች ያልተላለፉት የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሚቀጥለው ሣምንት ለባለዕድለኞች እንደሚተላለፉ ተገልጿል፡፡ 

ቤቶቹን ለማስተላለፍ አስቸጋሪ ሆኖ በቆየው የወሰን ይገባኛል ውዝግብ ጉዳይ የህግ ችግር አጥንቶ እንዲፈታ የተቋቋመው ኮሚቴ፤ ውሣኔውን ሰሞኑን ያሳውቃል ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑን የገለፁት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር ሠናይት ዳምጤ፤ የኮሚቴውን ውሣኔ ተከትሎ ቤቶቹን በአንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ የማስተላለፍ ተግባር ይከናወናል ብለዋል፡፡ 

በም/ከንቲባ ኢ/ር #ታከለ_ኡማ የሚመራውና ከኮዬ ፈጬ ጋር ተያይዞ የተነሳውን የወሰን ጥያቄ ለመመለስና ዘላቂ መፍትሔ ለማስቀመጥ የተቋቋመው የአስተዳደር ወሰን አጣሪ ኮሚቴ ስራውን ባለመጨረሱ የቤት እጣ ከወጣ ጀምሮ መተላለፍ የነበረባቸው ቤቶች ለባለዕድለኞች ሳይተላለፉ መቆየታቸውን ኢ/ር ሰናይት ተናግረዋል፡፡
 
በቀጣይ የሚኖረውን እጣ አወጣጥ በተመለከተ የቤቱ ግንባታ 30% ከተጠናቀቀ በኋላ ዕጣውን በማውጣት ያላለቁ ግንባታዎች እንደሚሠሩ የገለፁት ኃላፊዋ፤ ይህ የሚደረገው ባለ ዕድሎች ቤታቸውን ተከታትለው የማየትና የመቆጣጠር ሃላፊነት እንዲኖራቸው ታስቦ ነው ብለዋል፡፡ 

መመሪያው የሚፈቅደው 80 በመቶ የሚሆነው ተጠናቆ ከተሰራ በኋላ ቢሆንም 30 በመቶ ላይ ሳለ እጣ አውጥቶ 80% ሲደርስ ግን ለባለዕድለኞቹ እንደሚያስተላልፉ ተናግረዋል፡፡  

አያይዘውም ቀደም ሲል ከባንክ ጋር ውል የመፈፀም ስራ ይከናወን እንደነበር ገልፀው፤ አሁን ግን በቤቶችና ልማት አስተዳደር የባንክ ሒሳብ ገቢ በማድረግ ውል ለመፈፀም የሚያስችል አሠራር ተዘርግቶ መጠናቀቁን ኃላፊዋ ገልፀዋል፡፡ 
ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሰጡት መግለጫ፤ ዕጣው ለባለ ዕድሎች እንዲተላለፍ ታስቦ የተሠራ በመሆኑና የተሰራውም በድሃው ገንዘብ በመሆኑ ከመተላለፍ መስተጓጐል እንደማይገባው ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም የአስተዳደር ወሰን ማጣራቱ ከግለሰቦች የዕጣ አወጣጥ ጋር እንደማይገናኝ ተናግረዋል፡፡ 

Via አዲስ አድማስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ🔝

ለአዲስ አበባ ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት እና ግለሰቦች ምስጋና እና ዕውቅና የመስጠት መርሃ-ግብር ተካሄደ፡፡

የጎዳና ላይ ነዋሪዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተመሠረተው የማህበራዊ ትረስት ፈንድ ባደረገው ጥረት እስከ አሁን 3147 የጎዳና ላይ ነዋሪዎች የተነሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል 701 ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተገናኙ ሲሆን ቀሪዎቹን ህይወታቸውን በዘላቂነት ለመቀየር የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

በእስከ አሁን የማገገሚያ ቆይታቸው የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችን እና የስነ-ልቦና ትምህርቶችን እንዲያገኙ እየተደረገ ነው፡፡

ለዚህ ስራ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ዕውቅና ለመስጠት በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ የተገኙት ኢ/ር #ታከለ_ኡማ እስከአሁን ማገገሚያ የገቡትን ስራ የማስጀመርና ከቤተሰቦቻቸው ጋር የመቀላቀል ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና በቅርቡም ተጨማሪ የጎዳና ላይ ልጆችን የማንሳትና ወደ ማገገሚያ ማዕከል የማስገባት ስራው እንደሚካሄድም ጠቅሰዋል፡፡

በመጨረሻም ለማህበራዊ ትረስት ፈንዱ በዋናነት ድጋፍ ላደረጉ አካላት የምስጋና የምስክር ወረቀት የሰጡ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ የጎዳና ላይ ነዋሪዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ህብረተሰቡን እና ተቋማትን በማስተባበር የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech🔝

TIKVAH-ETH ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር #በመተባበር እያደረገ የሚገኘው የStop Hate Speech እንቅስቃሴ ቀጥሎ በዛሬው ዕለት #የሁለተኛው_ቀን መድረክ ተካሂዷል። በዛሬው እለት ከዩኒቨርሲቲ አመራሮች መካለል አቶ #እሸቱ ተገኝተው መልዕክት አተላልፈዋል። አቶ እሸቱ እንደተናጋሩት ተማሪዎች ከየትኛውም አይነት #የጥላቻ_ንግግር እና አንደንዛዥ አስተሳሰቦች #ሊርቁ ይገባል ብለዋል። በተጨማሪ ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ ሀሰተኛ መረጃዎችን እንዲሁም የጥላቻ መልዕክቶችን ላይክ እና ሼር ባለማድረግ ለሀገራቸው #ሰላም ዘብ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፤ ከዚህ ባለፈም ስለግቢያቸው #ሀሰተኛ መረጃ ሲሳራጭ #ሲመለከቱም እውነታውን መፃፍና እውነቱን ብቻ ማጋራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። አቶ እሸቱ ከወራት በፊት በግቢው በተሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ የተፈጠረውን ክስተት አንስተው ተማሪው እውነቱን በማህበራዊ ሚዲያ በማጋራት ላሳየው ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል።

•በዛሬው ምሽት ቆይታ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በአካል ተገናኝተው አጭር ቆይታ አድርገዋል፤ በርካታ ስራዎችን በቀጣይ ለመስራትም አጭር ውይይት ተደርጓል። እንዲሁም TIKVAH-ETH በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እንደ ማህበር የሚቋቋምበት መንገዶች ላይ በቀጣይ ሰፊ ውይይት ለማድረግ እቅድ ተይዟል።

ምሽቱ ልክ እንደትላንቱ #በትሩ_ላይፍ የኪነ ጥበብ ቡድን ታጅቦ አልፏል። #TrueLife

በነገው ዕለት የ3ኛውና የመጨረሻው ቀን መድረክ የሚኖር ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር #ታከለ ተገኝተው መልዕክት ያስተላልፋሉ።

በቀጣይ፦

አምቦ ዩኒቨርሲቲ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ
አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

#StopHateSpeech
#TIKVAH_ETH

ፎቶ፦ @odansiif (ዱሬሳ-TIKVAH-ETH)

የሀሳቡ ደጋፊዎች፦ 0919 74 36 30

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች እንዳትቀሩ፦

ዶክተር #ታከለ በተገኙበት የመጀመሪያው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ #StopHateSpeech እንቅስቃሴ በዛሬው ዕለት #ይጠናቀቃል

ቦታ፦ በፕሬዘዳንት ፅ/ቤት ህንፃ ፊት ለፊት
ሰዓት፦ ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ

በቀጣይ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተዘጋጁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia