#update አዲስ አበባ⬆️
በአዲስ አበባ #በካርቶን የታሸገ 3 ሚሊዮን 5 መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ብር እና 61400 የአሜሪካ #ዶላር በነሐሴ ወር 2010 ዓ/ም #መያዙን የከተማይቱ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የቻይና ዜግነት ያላቸው ሁለት ግለሰቦች ከቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን በየቀኑ ማታ ማታ በካርቶን የታሸጉ ብሮች ያወጡ እንደነበር ከአስራ አምስት ቀን በላይ ከፈጀ #ጥብቅ ክትትል በኋላ ፖሊስ ደርሶበታል፡፡
ነሀሴ 28 ቀን 2010 ዓ/ም ምሽት ላይ መነሻዋን ከቦሌ ሻላ ያደረገች ፕራዶ መኪና ወደ ቦሌ ሩዋንዳ ታመራለች፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የክትትልና ኦፕሬሽን ክፍል አባላትም መኪናዋን በቅርብ ርቀት መከታተል ይጀምራሉ፡፡
ፕራዶዋ ቦሌ ሩዋንዳ ከአንድ ሰዋራ ቦታ ትደርስና ከአንዲት ነጭ ዶልፊን መኪና አጠገብ ትቆማለች፡፡
ከዚያም ከፕራዶዋ ውስጥ የነበሩት ተጠርጣሪዎች በካርቶን የታሸጉት የገንዘብ ኖቶችን ወደ ዶልፊነኗ ሲያዛውሩ በክትትል ቡድኑ በቁጥጥር ስር ይውላሉ፡፡
በዕለቱ በቁጥጥር ስር የዋሉት ቀደም ሲል የተጠቀሱትና የቻይና ዜግነት ያላቸው ሁለት ግለሰቦችና አንድ ኢትዮጵያዊ ግብረአበራቸው በድምሩ 3 ተጠርጣሪዎች ናቸው፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በወቅቱ ለክትትል ፖሊስ አባላቱ 2 ሁለት ሚሊየን ብር እንስጣችሁነና ልቀቁን ሲሉ ተማፅነዋቸዉ የነበረ ቢሆንም የፖሊስ አባላቱ ግን ቀጥታ ጉዳዩን ለኃላፊዎቻቸው በመንገር ከእነ ኤግዚቢቱ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተነግሯል፡፡
©ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia