TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኦሮሚያ ክልል‼️

በህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ ዶክተር #ሚልኬሳ_ሚደግሳ ተናገሩ።

በጉዳዩ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የቢሮ ሃላፊው ሰሞኑን እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች የሊዝ አዋጅ 721ን መሰረት ያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። እርምጃው ከተሞች ስርዓት ባለውና ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲያድጉ ለማድረግ ያለመ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ዶክተር ሚልኬሳ በመግለጫቸው ህገ ወጥ ግንባታ መሆኑ እየታዋቀ በወንዞች ዳርቻና አረንጓዴ ስፍራዎች አካባቢ ግንባታዎች መከናወናቸውንም ጠቁመዋል። ከዚህ ባለፈም ግንባታዎቹ ለመኖሪያ #ምቹ_ባልሆኑ ስፍራዎች የሚካሄዱ በመሆናቸው መንግስት ተጠያቂ የሚሆንበትን እድል ይፈጥራልም ብለዋል።

በመግለጫቸው 2004 ዓመተ ምህረት ላይ የወጣውን የሊዝ ህግ ለማስፈፀም 2005 ዓመተ ምህረት ላይ መመሪያ መውጣቱን አስታውሰዋል።

መመሪያውም ከ2005 ዓመተ ምህረት በፊት የተገነቡ ቤቶች ከሳይት ፕላኑ ጋር የሚጣጣሙ ከሆነ ህጋዊ እንዲሆኑ፤ ከፕላኑ ጋር የማይጣጣሙ ከሆነ ደግሞ እንደሚፈርሱ ያስቀምጣል። አሁን እየተወሰደ ያለው እርምጃም ከዚህ አንጻር መሆኑን ነው ያስረዱት።

እርምጃው ከመወሰዱ በፊትም የህገ ወጥ ግንባታዎቹ መንስኤና መፍትሄ ላይ ያተኮረ ጥናት ተደርጓልም ነው ያሉት በመግለጫቸው። በጥናቱም በአንዳንድ አካባቢዎች መንግስት ለአርሶ አደሩ ካሳ ከፍሎ ለልማት ባዘጋጃቸው ቦታዎች ላይ ህገ ወጥ ግንባታ መካሄዱንም ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም በቀበሌ ቤቶች ሳይቀር ግለሰቦች የፈለጉትን ዓይነት ግንባታ አከናውነው መገኘታቸውም በጥናቱ ተደርሷል። ግንባታው ህገ ወጥ መሆኑ እየታወቀ ግንባታ መካሄዱም ትልቁ ችግር መሆኑን ጠቅሰው፥ መንግስትም ህግ የማስከበር ስራ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በቅርቡ በአዳማ፣ በሻሸመኔ እና መቱ ከተሞች በሺዎች የሚቆጠሩ ህገወጥ ግንባታዎች መፍረሳቸውን በማንሳትም፥ እርምጃው በፍንፊኔ ዙሪያ ብቻ እየተወሰደ አለመሆኑን ገልፀዋል። ዶክተር ሚልኬሳ እርምጃ በተወሰደባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎቹ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ከአንድ አመት ጀምሮ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው እንደቆየም አስታውሰዋል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም ቅሬታ ያላቸው አካላት #ቅሬታቸውን ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በማቅረብ መስተናገድ ይችላሉም ነው ያሉት።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞የካቲት 13/2011 ዓ.ም. #ሼር #Share @tikvahethiopia

የለገጣፎ -ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር አረንጓዴ ቦታዎችን፥ የወንዝ ዳርቻዎችን፥ ከፈቃድ ውጭ የተያዙ እና ካሳ ተከፍሎባቸው ግንባታ የተካሄደባቸው ናቸው ያላቸውን ቤቶች እያፈረሰ ውሏል።
.
.
በሃዋሳ ከተማ ነገ ለሚካሄደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ #ይፋጠንልን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የሃዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።
.
.
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በተሽከርካሪ አካል ውስጥ በረቀቀ መንገድ #ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረዬስ ጠብመንጃ እና ከ46 ሺ በላይ ጥይት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታውቋል፡፡
.
.
ዛሬ ጠዋት ጠቅላ ፍርድ ቤት የፌደራል ፖሊስ አቤቱታን ውድቅ በማድረግ ከእስር እንዲፈቱ ትእዛዝ የተሰጠላቸው አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው ሌላ ክስ ተመስርቶባቸው ማረሚያቤት ወርደዋል።
.
.
በምዕራብ ጎንደር ዞን #መቃ በተባለች አነስተኛ ከተማ በትንሹ 17 ሰዎች በትናንትናው ዕለት በአካባቢው ነዋሪዎች #መታገታቸውን የዐይን እማኝ ተናግረዋል።
.
.
ነገ ለሚደረገው #ሰላማዊ_ሰልፍ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ከዞን ፖሊስ፣ ከክልሉ ልዩ ሃይልና #ከፌደራል_ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ሰልፉ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በቂ ጥበቃ ያደርጋል።
.
.
ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ የሶማሊላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲንና ልዑካቸውን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
የደኢህዴን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ከየካቲት 12/06/2011 ዓ.ም ጀምሮ #በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
.
.
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ለተፈናቀሉ ወገኖች 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
.
.
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬድዮ /ኢሳት/ ጋዜጠኞች ዛሬ ኢቢሲን ጎብኝተዋል።
.
.
የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው ለሁለት ቀናት  በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባም በአራት አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
.
.
አክሱም ሽረ እንደስላሴ መስመር ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ የትራፊክ አደጋው ከሽረ እንደስላሴ ወደ አክሱምና ከአክሱም ወደ ሽረ እንደስላሴ  ሲጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች #በመጋጨታቸው ያጋጠመ ነው ተብሏል፡፡
.
.
በህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ ዶክተር #ሚልኬሳ_ሚደግሳ ተናግረዋል።
.
.
በለገጣፎ_ለገዳዲ ከተማ ቤታቸው #የፈረሰባቸው ዜጎች ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ fbc፣ etv፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ፣ wazemaradio፣ የጀርመን ራድዮ፣ OBN፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለገጣፎ ለገዳዲ‼️

በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ሕገወጥ ናቸው ተብለው የፈረሱ ቤቶች ጉዳይ የሰሞኑ መነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው እስከ ትናንት ምሽት ድረስ 3,800 ቤቶች ፈርሰዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ቤቶቹ #በሕገወጥ መንገድ የተሰሩ በመሆናቸው የወሰድኩት #እርምጃ ሕግን የማስከበር ሥራ ነው ብሏል፡፡

ነዋሪዎች በበኩላቸው ከ10 እስከ 19 ዓመት ቤት ገንብተው መኖራቸውን የአፈር ግብር ለመንግሥት እንደሚከፍሉና ውሃና መብራትን ጨምሮ መሰረተ ልማት የከተማ አስተዳደሩ እንዳሟላላቸው ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን መናገራቸው ይታወቃል፡፡ ነዋሪዎች ቤታችን በመፍረሱ ጎዳና ላይ ወድቀናል የሚል #እሮሮ እያሰሙ ነው፡፡

የኦሮሚያ ክልል የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊውን ዶክተር #ሚልኬሳ_ሚደግሳ ሸገር 102.1 ራድዮ በጉዳዩ ዙሪየ አነጋግሯቸዋል።

Via Sheger FM 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia