ሰበር ዜና‼️
የኦነግ መሪዎች እና የኢፌዴሪ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት #ድርድር እና #ውይይት እያካሄዱ ነው። በምዕራብ ኦሮሚያ የተፈጠረው ችግር በአጭር ጊዜ ውስጥ #መፍትሔ እንደሚያገኝ ሁለቱም ወገኖች ቃል ገብተዋል። ውይይቱ የሚካሄደው በዝግ ስብሰባ ሲሆን ከውይይቱ ማብቃት በኋላ ለህብረተሰቡ #መግለጫ ይሰጣል ተብሏል።
ምንጭ፦ Afendi Muteki
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ነቀምት‼️
በነቀምቴ ከተማ አስተዳደር ተቋርጦ የቆየው የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ #መደበኛ ስራ መጀመሩን የከተማው አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የከተማው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፈይሣ ብርሃኑ እንዳሉት ተቋማቱ አገልግሎት ያቆሙት በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ምስራቅ ወለጋ አዋሳኝ ወረዳዎች በተፈጠረ ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች ዘላቂ #መፍትሔ እንዲሰጥ ለመጠየቅ ነው።
በዚህም ከጥቅምት 26/2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለሶስት ቀናት ስራቸውን አቋርጠው ቆይተዋል፡፡
እነዚህ በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች፣ የትራንስፖርት ፣ የትምህርትና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዛሬ ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውን ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡
የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ግርማ አብዲሣ በበኩላቸው በአሁኑ ጊዜ በከተማው አስተማማኝ ሠላም ሰፍኖ ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት መመለሱን ገልጸዋል፡፡
ከነዋሪዎቹ መካከል ወይዘሮ የሺ ሐረግ ፋንታሁን በሰጡት አስተያየት የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስራ ማቆማቸው በተለይ በቀን ሠራተኛውና በሌሎችም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንና የመንግሥት ስራም መበደሉን ጠቁመዋል፡፡፡
በመንገድ መዘጋጋት ምክንያት አምቡላንሶች ወላድ እናቶችንና ድንገተኛ ህሙማንን ወደ ጤና ተቋማት ለማድረስ ችግር ሆኖባቸው መቆየቱን የተናገሩት ደግሞ የከተማዋ ቀበሌ ሰባት ነዋሪ ወይዘሮ ድንቅነሽ ምትኩ ናቸው ፡፡
ሌላው የከተማዋ ቀበሌ ሶስት ነዋሪ አቶ ጌታሁን ወዳጆ እንዳሉት ማንም እንደፈለገው መንገድ የሚዘጋና የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን የሚያቋርጥ ከሆነ በነዋሪው ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው፡፡
መንግሥት የሕግ የበላይነትን ማስከበርና የሕዝቡ ቅሬታ መስማት እንዳለበት አመልክተዋል፡፡
ምንጭ፦ ENA

ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ሜሴንጀር እና ዋትስአፕ በአብዛኛው የዓለም ክፍል በአግባቡ #እየሰሩ_አይደለም። ተጠቃሚዎች ፎቶ እና ቪዲዮ መመልከት እና መጫን አይችሉም። የፌስቡክ ቃል አቀባይ ችግሩ መፈጠሩን አምነው #መፍትሔ_ፍለጋ እየሰራን ነው ብለዋል። ባለፈው መጋቢት ፌስቡክ በሶስቱ መተግበሪያዎች ላይ ተመሳሳይ እክል ገጥሞት ነበር።
Via #EshetBekele
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #EshetBekele
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Attention ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በአፋር ክልል በርካታ የቀድሞ አመራሮች እና አንዳንድ ባለሀብቶች በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሆነ ተሰምቷል። የጉዳዩ መነሻ ሶስት አወዛጋቢ ቀበሌዎች የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት ስልጣን ላይ እያሉ ወደ አፋር ክልል መካተታቸው ነበር። ይህ ውሳኔ የተላለፈው ከፍተኛ የፌደራል ባለስልጣናት ጭምር በተገኙበት ነበር። በቅርቡ ደግሞ የሶማሌ ክልል እነዚህ ቀበሌዎች…
የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ከአፋር!
ከሰሞኑ የተሰራጨው መረጃ የተዛባ ነው፤ ከሁለቱም ወገን ያማከለ አይደለም ሲሉ በአፋል ክልል የሚገኙ ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል። ስለሁኔታውም ተከታዩን ብለዋል፦
----
በአፋር ክልል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ያሉት የቀድሞ አመራሮችና ባለሀብቶች መኖራቸው #እውነት ብሆንም የተያዙበት ምክንያት ግን ከአፋር-ሱማሌ(ኢሳ) ጉዳይ ምንም የሚያገናኘው ነገር የለውም። የተያዙት ከአፍዴራ ጨው አምራቾች ማህበር (ከዳባ) ጋር በተገናኘ ስሆን ከተሰሩት ውስጥ አፋር የልሆኑም ይገኝበታል። እስሩ አሁንም እንደቀጠለ ስሆን እስካሁን ከመንግስት በኩል ግልፅ የሆነ መግለጫ አልተሰጠበትም።
የአፋር–ሱማሌ(ኢሳ) ግጭት በተመለከተ ግን ለ 80+ አመታት የዘለቀ ግጭት ሲሆን ያሁኑ ግጭት መንስኤው ከኢሳ በኩል ያሉ አንዳንድ አካላት የአፋርን ባንድራ አውርዶ በማቃጠል "በአፋር ክልል ስር አንተዳደርም" በማለታቸው ነው። ግጭት ከተጀመረ አሁን 9ነኛ ወር የያዘ ሲሆን ከመንግስት በኩል የተሰጠ #መፍትሔ የለም። ባለፈው ሳምንት በተፈጠረው ግጭት ከአፋር ወደ 30 ሰው እንደሞተ ተደርጎ የተዘገበው የተገጋነነ ዘገባ ነው። የሞቱት ከአፋር በኩል 7 ሲሆን 3 ቆለዋል። ግጭቱ አሁን መልክ እየቀየረ እስከ ጅቡቲ ደረስ እየዘለቀ በመሆኑ ከመንግስት በኩል አስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጠው የቀጠናው ሰላም ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን መታወቅ አለበት።"
------
በዚህ አጋጣሚ ከመንግስት በኩል ምንም ይፋዊ ነገር ባለመገለፁ፤ እየወጡ ያሉት መረጃዎች ያልተረጋገጡ ናቸው፤ የሟቾች ቁጥርም በተለያዩ አካላት የሚገለፀው የተለያየ ነው። በአካባቢው የሚገኙ TIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጉዳዩን እየተከታተሉ መረጃዎችን ያደርሱናል።
የመንግስት ዝምታ ግን🤔