TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኮሎኔል ጉደታ ኦላና‼️

የዐቃቤ ህግን ስራ ለማደናቀፍ የሞከረው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበ። የቀድሞው የኢትዮ ቴሌኮም የሴኪዩውሪቲ ዲቪዥን ኃላፊ የነበሩት ኮሎኔል #ጉደታ_ኦላና በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ቀርበዋል፡፡

ተጠርጣሪዉ የሙስና ወንጀልን እያጣሩ ባሉ ባለሙያዎች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ በመፈጸም እና የፌደራል የዐቃቤ ህግን ስራ በማደናቀፍ ተግባር ተጠርጥረው መቅረባቸውን የፌዴራል መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡

በተጠርጠጣሪው በባለቤቱ ስም 438 ሺህ 222 ብር በኦሮሚያ ኢንትርናሽናል ባንክ አፍሪካ ቅርጫፍ መኖሩን እንዲሁም በ2010 ሚያዚያ ወር ሱሉልታ አካባቢ 550 ሺህ ብር በመንደር ውል መሸጣቸውን በማስረጃነት ለፍርድ ቤት አቅርቧል።

ተጠርጣሪው በተከላካይ ጠበቃው አማካኝነት የቀረበበት የምርመራ መዝገብ ተገቢነት እንደሌለው በማስረዳት በዋስ ሊወጣ እንደሚገባ ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር ከተመለከተ በኃላ ፖሊስ ቀሪ የምርመራ ሰራዎቹን አጠናቆ እንዲያቀርብ በማለት ተጨማሪ 7 የምርመራ ቀናትን በመፍቀድ ለህዳር 20 ቀን 2011ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር🔝ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር የመጣው የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የልዑካን ቡድን በባህር ዳር ከተማ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት። የልዑካን ቡድኑ ዛሬ ማምሻውን ባህር ዳር ከተማ ሲገባ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባና በከተማው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በድሬዳዋ አስተዳደር ሰሞኑን ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎች መደበኛ እንቅስቃሴ መቀጠሉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ አስታውቋል። ላለፉት አራት ቀናት ችግር የተፈጠረባቸው አካባቢዎች ዛሬ ሙሉ ለሙሉ ወደ #መረጋጋት ተመልሰዋል። መደበኛና የንግድ እንቅስቃሴም ወደ ወትሮ ሁኔታ ተመልሷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት ለቴፒ‼️ትኩረት ለቴፒ‼️ትኩረት ለቴፒ‼️ትኩረት ለቴፒ‼️ትኩረት ለቴፒ‼️ትኩረት ለቴፒ‼️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ወ/ማሪያም ምላሽና ማብራሪያ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች‼️

🔹የተለያዩ መረጃዎች በግቢያችሁ ውስጥ ሲሰራጩ ስለመረጃው ትክክለኝነት በደንብ አረጋግጡ። ሀሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጩ ሀገሪቷን ለመበታተን እየሞከሩ ያሉ አካላት አሉ።

ሁሌም ጠያቂ እና ምክንያታዊ ሁኑ ከስሜታዊነት ውጡ እና ስለሰማችሁት ነገር በአግባቡ ጠይቁ፦

.ሴት ተደፈረች ስትባሉ (ማን የምትባል?? ስሟ ማነው?? የምን ተማሪ ናት?? ጓደኞቿ እነማን ናቸው?? የት ዶርም ነው የምትኖረው?? ቤተሰቦቿ ሰምተዋል?? ...)

.በሌሎች ጉዳይም ብዙ ጠይቁ። ተባራሪ ወሬ ከምትሰሙ የግቢውን አስተዳደር ለመጠየቅ ሞክሩ። ፕሬዘዳንቱን መጠየቅ ካለባችሁም ወደኃላ እንዳትሉ።

🔹ለታናናሾቻችሁ ትምህርት ሰጥታችሁ የምታልፉት መልካም እና ቀና አስተሳሰብ ሲኖራችሁ ብቻ መሆኑን አውቃችሁ በያላችሁበት ዘውትር ስለሰላም ምንነት አስቡ።

🔹በፍፁም የግለሰቦችን ፀብ ወደቡድን እንዲቀየር አትደግፉ። በእንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ ተማሪዎችንም ለመንግስት አሳልፋችሁ ስጡ። ማንም ከህግ በላይ ሆኖ መኖር አይችልምና።

🔹የሰው ልጅ ሲቸገር፣ ሲጎዳ፣ ሲደበደብ ስታዩ የምን #ብሄር ተወላጅ ነው? የሚለውን ጥያቄ ትታችሁ ሰው ክቡር ነው በማለት አጥፊውን ለመንግስት አሳልፋችሁ ስጡ። የሰውን ስቃይ በብሄር #እየከፈላችሁ የምትወዷት ሀገራችሁን ቁልቁል እንድትጓዝ በፍፁም አትፍቀዱ።

🔹ከፌስቡክ ሀሰተኛ ወሬዎች በቻላችሁት መጠን ራቁ። በፌስቡክ የሚሰራጩ መረጃዎችን እንደወረደ አትቀበሉ። የማያጋጩ የሚመስሉ ነገር ግን ሰዎችን ለግጭት የሚቀሰቅሱ መረጃዎችን ሼር ከማድረግ ተቆጠቡ።

🔹በፍፁም ታዋቂ ግለሰቦችን እንደፈጣሪ አትከተሉ። ግለሰቦቹን እና ሰፊውን ህዝብ ለዩ። ግለሰብ እና ብሄር ለዩ‼️ ግለሰብ ሲያጠፋ ብሄር አጠፋ ከሚል ዝቅተኛ አመለካከት ውጡ።

🔹ዘውትር ስለፍቅር አስቡ፤ ስለሰላም ተነጋገሩ! ሰላም ሲጠፋ የሚደርሰውን የከፋ ጉዳት ዘውትር ከማሰብ ወደኃላ እንዳትሉ።

🔹በህይወት ዘመናችሁ ሁሉ በፍፁም በሰዎች እንዳትነዱ። በመንጋ እንዳታስቡ።

🔹በእምነታችሁ ፅኑ የትኛውም ሀይማኖት ሰዎችን ስለማይከፍል በሀይማኖታችሁ በርቱ! ፈጣሪን ሁሌም ሰላም፣ አንድነት እና ፍቅር እንዲሰጠን ተማፀኑ። እውነተኛ ሰው ሁኑ! ጥዋት ቤተክርስቲያን ከሰዓት ደግሞ እርስ በእርስ ለመጋጨት ሰው ለመጉዳት ከመምከር ተቆጠቡ። መስጂድ ሄዳችሁ አላህ ማስተዋልን ብቻ እንዲሰጣችሁ ተማፀኑ! ሀይማኖት ካላችሁ ስልሰው ክቡርነት ትረዳላችሁ እና በየሀይማኖታችሁ ፅኑ! ተዋደዱ!!

በመጨረሻም፦ ኢትዮጵያን ጠብቋት! ድህነቷን ተመልከቱላት፤ ሳይበላ የሚያድረውን እዩላት፤ ተምራችሁ ወጥታችሁ በቻላችሁት መጠን ሀገራችሁን አገልግሉ።

ዩኒቨርሲቲዎች፦

🔹በዚህ በሰለጠነ ዘመን ኃላቀር አትሁኑ። ፌስቡክ ላይ ወሬ ሲወራ ጉዳዩን በአስቸኳይ አጣርታችሁ ከቻላችሁ በፌስቡክ ካልቻላችሁ በወረቀት ለተማሪው ግለፁ።

🔹ችግር ከደረሰ በኃላ ተማሪ ማወያየት ጥቅም አልባ ነውና በየትምህርት ክፍሉ ስለአንድነት እና ሰላም ውይይት እንዲደረግ አድርጉ።

🔹የተማሪ ህብረት ስራችሁን በአግባቡ ስሩ። በየዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያላችሁ ክበባት ከወሬ ይልቅ በስራ ተጠመዱ።

🔹ጥበቃዎች ስለፈጠራችሁ ተማሪዎን ከፋፍሎ ከማየት ተቆጠቡ። የአካባቢው ልጅ ነው እያሉ ሌሎችን ጥሩ ባልሆነ መልክ ማየቱን አቁሙ። ሀላፊነታችሁን የማትወጡ ከሆነም ስራውን ልቀቁት ምክንያቱም አሁን ኢትዮጵያ የሚሰራላት ሰው ያስፈልጋታል።

🔹ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተማሪውን የሚያቀራርቡ ዝግጅቶች ቢኖሩ መልካም ነው!!

🔹ለሁሉም ተማሪ በቂ ጥበቃ እና ከለላ ሊደረግለት ይገባል።

ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahthiopia
የጥላቻ ንግግር ላይ አዲስ ህግ ሊወጣ ነው‼️

ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግር ላይ አዲስ ህግ ልታወጣ መሆኗን አስታወቀች።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ #የጥላቻ_ንግግርን የተመለከተና ተጠያቂነትን የሚያመጣ አዲስ ረቂቅ ህግ እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል።

የጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ እንደገለጹት በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተስፋፉ የመጡት ሃላፊነት የጎደላቸው መልዕክቶችና የሀሰት ወሬዎች በሀገሪቱ ለሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት በመሆናቸው መንግስት ይህን አደጋ ለማስወገድ ህጋዊ ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያስችል አሰራር በማርቀቅ ላይ ነው።

ህጉ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እንዳይጋፋ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ምሁራን አስተያየት በመስጠት ላይ ናቸው።

የጥላቻ ንንግሮች የዓለማችን የወቅቱ ፈተና እንደሆኑ ይገለጻል።

በሃገረ አሜሪካ የጥላቻ ንግግር ሀሳብን በነጻነት ከመግለጽ መብት ጋር ተያይዞ ሰፊ የውይይት አጀንዳ የከፈተ ጉዳይ ነው።

አሜሪካ በህገመንግስቷ የመጀመሪያ ክፍል ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ሳይሸራረፍ እንዲከበር ማድርጓ ለጥላቻ ንግግር መበራከት አስተዋጽኦ አድርጓል የሚሉ ወገኖች ቢኖሩም ህዝብን ከህብ የሚያጋጩ፣ ሁከትን የሚፈጥሩና ሰላምን የሚያውኩ የጥላቻ ንግግሮች ላይ ግን አሜሪካ ጠበቅ ያለ ርምጃ ትወስዳለች።

የማህበራዊ ሚዲያዎች መምጣትና መስፋፋት ለጥላቻ ንግግሮች መበራከት አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚገልጹ የዘርፉ ባለሙያዎች ዓለማችን ከገጠሟት የጊዜው ብርቱ አደጋዎች አንዱ እንደሆነም ያስምራሉ።

ኢትዮጵያም የጥላቻ ንግግሮች ሰላባ ለመሆኗ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚከሰቱ #ግጭቶች አይነተኛ ማሳያ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የጥላቻ ንግግሮችና #ሀሰተኛ_ወሬዎች በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰቱ ላሉ ግጭቶች ሰበብ ምክንያት መሆናቸውን እንዳመነበት ገልጿል።

አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑ ይህን አደጋ ለመቀነስ የጥላቻ ንግግሮች ላይ ገደብና ተጠያቂነት የሚያሰፍን ህግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።

አቶ ዝናቡ እንዳሉት ኢትዮጵያ አዲስ የተስፋ ምዕራፍ ላይ መገኘቷን ተከትሎ ለጀመረችው የለውጥ ጎዳና እንቅፋት የሚሆኑትን ጉዳዮች በመለየት በህግ ልትፈታቸው ተዘጋጅታለች።

በተለይም ለህዝብ የሚቀርቡ ንግግሮችና የሚተላለፉ መልዕክቶችን በተመለከተ ሃላፊነትና ተጠያቂነት ማስፈን እንደሚገባ ነው አቶ ዝናቡ የገለጹት።

የማህበራዊ ሚዲያዎች መበራከት ከጥቅማቸው እኩል ጉዳቶችንም ማስከተላቸውን የጠቀሱት አቶ ዝናቡ በጥላቻ ንግግሮችና ሃላፊነት በጎደላቸው እንቅስቃሴዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም ብለዋል።

በመሆኑም መንግስት እነዚህን ግጭት ቀስቃሽና ሰላም አዋኪ የሆኑ የጥላቻ ንግግሮችን ለማስቆም ረቂቅ ህግ በማዘጋጀት ላይ ሲሆን በቅርቡ ተጠናቆ ለሚመለከተው አካል ለውይይት እንደሚቀርብ ገልጸዋል።

አንዳንድ ምሁራን ጉዳዩ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እንዳይጋፋው ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።

በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ መልዕክቶችን ሳንሱር ማድረግ አስቸጋሪ እንደሆነ በመግለጽ ህጉ በምን ዓይነት መልኩ ችግሩን ለማስቀረት እንዳሰበ ለማወቅ አስቸጋሪ እንደሆነም ይገልጻሉ።

የጥላቻ ንግግሮችን በህግ ለማስቀረት የሚቻል ቢሆንም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው ነው ምሁራን የሚገልጹት።

ምንጭ፦የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
110 ሺሻ ቤቶች ተዘጉ‼️

በፍቼ ከተማ 110 የሚሆኑ የሺሻ ማጨሻ ቤቶች #መዝጋቱን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማው ፖሊስ የኮሚኒቲ ፖሊሲንግና ወንጀል መከላከል ኃላፊ ኢንስፔክተር #ደረጄ_ፈዬ ለኢዜአ እንደገለፁት የሺሻ ማጨሻ ቤቶቹ ሰሞኑን እንዲዘጉ የተደረገው ህብረተሰቡ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ነው፡፡

ፖሊስ የህብረተሰቡን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ባለፉት አስር ቀናት ህግን ተከትሎ ባደረገው አሰሳ 97 የሺሻ መጠቀሚያ እቃዎችንና ድርጊቱን ሲፈፅሙ የነበሩ ሰዎችን እጅ ከፍንጅ መያዙን ገልፀዋል፡፡

እንዲሁም የማደንዘዝ አቅማቸው ከፍተኛ የሆኑ ሲጋራዎችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን በኤግዚቢትነት መያዙንና በፍርድ ቤት ውሳኔም እንደሚወገዱ ተናግረዋል፡፡

ቤቶቹ የተዘጉት በህጋዊ የቡናና የሻይ ማፍላትና መሸጥ ሰበብ ህገወጥ ድርጊት ሲፈፅሙና ሲያስፈፀሙ በመያዛቸው መሆኑን ኢንስፔከተሩ ገልፀዋል።

የከተማው አንዳንድ ወጣቶች በሃሽሽና በሌሎች ደባል ሱሶች በመጠመድ የሚፈፅሙት ህገወጥ ድርጊት ከጊዜ ወደ ጊዜ አየጨመረ መምጣቱን ሃላፊው ጠቅሰው ሁኔታውን ለመከላከል ፖሊስ ባደረገው ጥረት የከተማው ሕዝብ ያሳየው ትብብር የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።

በከተማው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከመቶ በላይ ሸሻ ቤቶች የተዘጉ ሲሆን ቁሳቁሳቸው በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መወገዳቸውን አስታውቀዋል፡፡

ፖሊስ ወጣቱን በተለያየ መድረክ በማሰባሰስብ በወንጀል አስከፊነትና አደነዛዠ እፅ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ፖሊስ በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ የሚገኙ ሽሻና ጫት ቤቶች መዝጋቱ ለሰላማዊ የመማር ማስተማር ሰራ የሚያግዝ መሆኑን የገለፁት የአብዲስ አጋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምሀር አቶ ሃይሉ ታፈሰ ናቸው።

ይህም የአንድ ወቅት ዘመቻ ሳይሆን ክትትልና ደጋፍ በማድረግ ለዘለቄታው እንዲቆም ማድረግን ታሳቢ ያደረገ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።

ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ፖሊስ ሽሻ ቤቶችን በመዝጋቱ፣ በከተማው አንዳንድ አካባቢዎች ሲፈፀም የነበረው የስርቆት፣ የዘረፋና የድብደባ #ወንጀል ይቀንሳል የሚል እምነት እንዳላቸው የገለፁት ደግሞ በቀበሌ 04 በንግድ ስራ የሚተዳደሩት አቶ ሙሃባ ነጂብ ናቸው።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች🔝

"ሀልዎት የበጎ አድራጎት ክለብ  ከብሔራዊ ደም ባንክ ጋር በመተባበር ቦሌ ድልድይ ዛሬ ቀኑን ሙሉ (ህዳር 15 , 2011 ዓ.ም) የደም ልገሳ ፕሮግራም ለአምስተኛ ዙር በማድረግ 500 ዩኒት ደም ከበጎ ፍቃደኞች ስለምንሰበሰብ በአካባቢው የሚኖሩ ወጣቶች ተሳታፊ እንዲሆኑ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን። እናመሰግናለን!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
 
ትግራይ🕊አማራ🔝

የትግራይና አማራ ክልል እግር ኳስ ክለቦች #ሰላማዊ የሆነ ጨዋታ ያደርጋሉ ተብሏል።

ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በትግራይና አማራ ክልል የእግር ኳስ ክለቦች መካካከል የሚደረጉ ጨዋታዎች ሲራዘሙ በገለልተኛ ሜዳ ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡ በ2011 የዉድድር መርሀ ግብሮች ያለ ዉከትና ብጥብጥ ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲተገበሩ የስፖርት ኮሚሽን እና የክልል አመራሮች ከስፖርት ማህበራት ጋር በቅንጅት ለመስራት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን መናገሩ የሚታወስ ነው፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፣ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እርስቱ ይርዳው እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ፤ ከትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል እና ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳጋቸው ጋር በሁለቱም ክልሎች የሚካሄዱ ዉድድሮች ስፖርታዊ ጨዋነትን ተላብሰዉ በሚካሄዱበት ሁኔታ ላይ ምክክር አድርገዋል።

ዶ/ር ደብረፂዮን ህዝቡ በክልሉ የሚካሄዱ የስፖርት ዉድድሮች በተለመደዉ የእንግዳ አቀባበል ባህል መሠረት ለማስተናገድ #ዝግጁ መሆናቸዉን አረጋግጠዋል።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በክልሉ የሚካሄዱ ውድድሮች እጅግ ሰላማዊ ሆነው እንዲካሄዱ የክልሉ ህዝብና መንግስት ፍላጎት እንደሆነ ገልፀው ከዚህ በኋላ የስፖርታዊ ጨዋነት ችግር እንዳይከሰት በትኩርት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

ስፖርት ኮሚሽን እንደገለፀው ስፖርት ያተለመለትን ዓላማ ይዞ መቀጠል የሚችለዉ ህጉንና ስርዓቱን ጠብቆ እንዲከናወን ጉዳዩ በሚያገባዉ አካል ጥበቃ ሲደረግለት ነዉ ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ አርትስ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ‼️

የአዳማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር #የተከሰሰን ግለሰብ በእስራትና በገንዘብ መቅጣቱን ፖሊስ አስታወቀ።

ከግለሰቡ ላይ በኤግዚቢትነት የተያዘው 73 ሺህ 900 የአሜሪካን ዶላር ለመንግስት ገቢ እንዲሆንም ፍርድ ቤቱ ውስኗል።

የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ዋና ሳጂን ወርቅነሽ ገልሜቻ እንዳሉት ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎች የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው #በርሄ_ገብሬ በተባለ ተከሳሽ ላይ ነው።

ግለሰቡ ህዳር 5 ቀን 2011 ዓ.ም 73 ሺህ 900 የአሜሪካን ዶላር በህገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋወር በፖሊስ ተይዞ ፍርድ ቤት መቅረቡን አስታውሰዋል።

በእለቱ ግለሰቡ በአዳማ ከተማ ከምሽቱ 2፡30 ላይ የተያዘው ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ በነበረ የሰሌዳ ቁጥር 3-03952 ድሬ ፒክ አፕ ተሽከርካሪ ላይ ተሳፍሮ ሲጓዝ እንደነበር አስታውሰዋል።

ፖሊስ ከሕብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በአዳማ ዳቤ ሶሎቄ ቀበሌ ልዩ ስሙ “ኬላ” በተባለ አካባቢ በተሽከርካሪው ላይ ባደረገው ፍተሻ ገንዘቡ በግለሰቡ ሻንጣ ውስጥ ተደብቆ መገኘቱን ፍርድ ቤቱ በሰውና በሰነድ ማስረጃ ማረጋገጡን ገልጸዋል።

ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የአዳማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በግለሰቡ ላይ የሁለት ዓመት ጽኑ እስራትና በአራት ሺህ ብር እንዲቀጣ ውሳኔ ማሳለፉን ሳጂን ወርቅነሽ አስታውቀዋል።

በኤግዚቢትነት የተያዘው 73 ሺህ 900 የአሜሪካን ዶላርም ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update ወ/ሪት #ብርቱካን_ሚደቅሳ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ በመሆን መሾማቸው የሀገሪቱን የምርጫ ስርዓት ታዓማኒነት ከፍ እንደሚያደርግ የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ገለፁ፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባ ምንጭ🔝በጋሞ ብሄር ክልል የመሆን ጥያቄ ላይ ህዝባዊ ውይይት በአርባ ምንጭ ሼቻ ኦሞ አዳራሽ እየተካሄደ ነው፡፡ ከዛሬው ውይይት በመቀጠል በመጪዎቹ ቀናት በሚካሄደው የጋሞ ዞን ምክር ቤት ጉባኤ ውሳኔ ይተላለፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia