TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮጵያን እንፈልጋታለን‼️

ምስኪኑ ዜጋ ሲፈናቀል፣ ሲሰቃይ፣ ሲቸገር፣ ተበደልኩ ሲል፣ ፍትህ ተነፍጊያለሁ ብሎ ሲጮህ፣ መንግስት በድሎኛል ብሎ ሮሮውን ሲያሰማ ለርካሽ #የፖለቲካ_ትርፍ እና #ሀገር_ለማትራመስ የምትሯሯጡ ጨካኝ አረመኔ ሰዎች ኢትዮጵያን ስለምንፈልጋት እጃችሁን ሰብስቡልን።

ሰዎች ሰውነታቸውን ክደው #ሀዘናቸውን እንኳን #ብሄር ለይተው እንዲገልፁ የምትገፋፉ ሰውነታችሁን የከዳችሁ ሁሉ #ኢትዮጵያን ስለምንፈልጋት እጃችሁን ከሀገራችን ላይ አንሱ።

በደንብ ስሙኝ...🔥

ህዝቡን በብሄር ከፋፍላችሁ #ወደጦርነት ለመክተት ፌስቡክ ላይ #ተዘፍዝፋችሁ የምትውሉ ሰዎች--የምትወዱትን ማጣት ስትጀምሩ፣ ምስኪን ህፃናት እንደቅጠል ሲረግፉ ማየት ስትጀምሩ፣ ሚሊዮኖች ሰላም ፍለጋ መሰደድ ሲጀምሩ ስታዩ ደም እምባ እያለቀሳችሁ እያንዳንዷን ፌስቡክ ላይ የዋላችሁበትን ቀን #ትረግሟታላችሁ
.
.
መንግስት በአስቸኳይ #ፍትህ እንፈልጋለን ብለው የሚጮሁ ዜጎች ካሉ ያዳምጥ፤ ምላሽ ይስጥ፤ በምስኪን ዜጎች ህይወት ላይ #ቁማር የሚጫወቱ የፖለቲካ ነጋዴዎችንም አደብ ያስገዛ!

#FACEBOOK ከብዶናል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአኩን ሰዓት #Facebook ኢትዮጵያ ውስጥ የስድብ እና የጥላቻ ንግግሮችን ማሰራጫ፣ የግጭት መጠንሰሻ፣ የጦርነት መቀስቀሻ፣ የሰላም ማደፍረሻ እየሆነ በመምጣቱ ለ1 ሳምንት እራሴን ከፌስቡክ አግልያለሁ!

ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ፌስቡክ #የጥላቻ_ንግግርን በተመለከተ ያለውን ፖሊሲ እንደገና ሊከልስ ይገባል። #facebook🚫 #ፌስቡክ🚫

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOIA
ለሽብር ያነሳሳል...

የአውሮፓ ሕብረት በሚያዚያ 2017 ባወጣው መረጃ ላይ #ስድብ አዘል የማሕበራዊ ድረገጽ አስተያየቶች ሰዎችን እንደሽብር ላሉ #መጥፎ ሀሳቦች የሚያነሳሳ እንደሆነ ይገልጽና፣ በማህበራዊ ድረገጾች ላይ #ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል ሲል ይመክራል፡፡ የሕብረቱ ውሳኔ የተሳዳቢዎቹን ምክንያት አይገልጽም፡፡ ውጤቱ ወደ ሽብርተኝነት ያድጋል ሲል ማስጠንቀቁ ግን አልቀረም፡፡

#Facebook🚫

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምዕራፍ ሁለት!

ለ2 ሳምንት የሚቆይ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ #NoHateSpeechMovement /ETHIOPIA/ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጩ ያሉ የጥላቻ ንግግሮችን የምንዋጋበት፤ የተለያዩ መልዕክቶችን ፖስት በማድረግ ጥላቻን የምናሸንፍበት ሳምንታት ይሆናሉ! #ቲክቫህኢትዮጵያ

ዘመቻው የሚካሄደው፦
#Facebook
#Telegram
#Twitter ላይ ይሆናል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🚫STOP HATE SPEECH🚫

#TikvahEthiopia #Facebook #Telegram #Twitter ሀገራችንን እናድን! የጥላቻ ንግግሮች ሀገራችንን ወደአስፈሪ ሁኔታ ውስጥ እየከተታት ይገኛል። ሁላችም ከጥላቻ ንግግሮች ራሳችንን በማራቅ ሀገራዊ ሀላፊነታችንን እንወጣ!

#ከጥላቻ_ንግግሮች_እንቆጠብ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FaceBook

ፌስ ቡክ #ከጥላቻ_ንግግር ፖሊሲው ጋር የሚጣረሱ መልዕክቶችን በቀጥታ በሚያሠራጩ ተጠቃሚዎች ላይ አዲስ የቁጥጥር ህግ ሊያስተዋውቅ ነው። በኒውዚላንድ ክሪስት ቸርች መስጊዶች ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ለተወሰነ ጊዜ ተጠቃሚዎችን ከፌስቡክ ማገድ እንደ አንድ የመፍትሔ ሃሳብ ቀርቧል። በፓሪስ በሚካሄደውና በፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮንና በኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን በሚመራው ጉባዔ ላይም ፅንፈኛና ተንኳሽ የሆኑ ንግግሮችን ለመቀነስ የሚረዱ ሃሳቦች ይቀርቡበታል ተብሏል። በመስጊዶቹ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በስፋት ከተሠራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል በኋለ ፌስቡክ ትችት አጋጥሞታል። በኒውዚላንድ ክሪስትቸርች ከተማ ሁለት መስኪዶች ላይ በተከፈተ ተኩስ 49 ሰዎች ሲገደሉ ብዙዎች መጎዳታቸው ይታወሳል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የጥላቻ_ንግግር #facebook የጀርመን ባለስልጣናት የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ የሆነው ፌስቡክ የሀገሪቱን የጥላቻ ንግግር ህግ በመጣሱ በ2 ነጥብ 3 ሚሊየን የአሜሪካ እንዲቀጣ ውሳኔ ማሳለፋቸውን አስታውቀዋል።

ባለስልጣናቱ በፌስቡክ ላይ ቅጣቱን በትናንትናው እለት ያሳለፉ ሲሆን፥ ቅጣቱ የተላለፈውም ህጉን የጣሱ ይዘቶችን በፌስቡክ ገፅ ላይ ሲሰራጩ ምንም አይነት የማስተካከያ እርምጃ ባለመውሰዱ ነው ተብሏል። የጀርመን የፌደራል ፍትህ ቢሮ ባወጣው መግለጫ፥ ፌስቡክ የጥላቻ ንግግር ህግ የጣሱ ይዘቶች እና ህዝቡን የሚረብሹ ምስሎች ሲለቀቁ እርምጃ ባለመውሰዱ ውሳኔው እንደተላለፈበት አስታውቋል።

ፌስቡክ ህገ ወጥ የተባሉ ይዘቶች ላይ የወሰደውን እርምጃም ግልጽ አድርጎ በሪፖርት እንዳላቀረበም ነው ቢሮው ያስታወቀው። በጀርመን ህግ መሰረት ፌስቡክን ጨምሮ ሁሉም የማህበራዊ ትስስር ድረ ገፆች በበድረ ገፆቻቸው ላይ የሚያጋጥሙ ህገ ወጥ ይዘቶች ላይ የሚወስዷቸውን እርምጃዎች በየስድስት ወሩ በሪፖርት ማሳወቅ እንዳለባቸው ተደንግጓል።

ፌስቡክን ለቅጣት ከዳረጉት ምክንያቶች ውስጥም አንዱ የተሟላ ሪፖርት አለማቅረቡ አንደሆነም ነው እየተነገረ ያለው። የፌስቡክ ኩባንያ ግን በተላለፈበት የቅጣት ውሳኔ ላይ እስካሁን ምላሽ እንዳልሰጠ እና የይግባኝም አንዳልጠየቀ ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት።

ምንጭ፦ www.cnet.com
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FaceBook

ፌስቡክ ከአፍሪካ ቼክ ጋር በመተባበር የሦስተኛ ወገን የእውነታ ማረጋገጫ ፕሮግራሙን ለማጠናከር በርካታ የአፍሪካ ቋንቋዎችን በፕሮግራሙ ውስጥ ማካተቱን ይፋ አደረገ።

እርምጃው በፌስቡክ ገጽ ላይ የሚሰራጩ ዜናዎችን እውነተኝነት ለማረጋገጥ እና የተሳሳቱ መረጃዎችን ለመቀነስ ያግዛል ተብሏል።

እ.አ.አ ከ2018 ጀምሮ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል እና ካሜሩን ውስጥ የተጀመረው ፕሮግራሙ አሁን በእነዚህ ሀገራት ውስጥ ያሉ ተጨማሪ ቋንቋዎችን ማካተቱ ተነግሯል።

በተጨማሪነት ከተካተቱት ቋንቋዎች ውስጥም ከናይጄሪያ ዮሩባ እና ኢግቦ፣ ከኬንያ ስዋሂሊ፣ ከሴኔጋል ዎሎፍ፣ ከደቡብ አፍሪካ አፍሪካን፣ ዙሉ፣ ሴትስዋና፣ ሶቶ፣ ሰሜናዊ ሶቶ እና ደቡባዊ ንዴቤሌ ይገኙበታል።

በፌስቡክ የአፍሪካ የፐብሊክ ፖሊሲ ጉዳዮች ዋና ኃላፊ የሆኑት ኮጆ ቦክዬ የቋንቋዎቹን መካተት ምክንያት በማድረግ በሰጡት መግለጫ፣ "አጋዥ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ በመረጃ የበለጸገ እና አካታች የሆነ ማኅበረሰብ ለመገንባት ከምናደርገው ጥረት ጎን ለጎን በገጻችን ላይ የሚሰራጩ ሐሰተኛ ዜናዎችን በመታገሉ ረገድ አቅማችንን አጎልብተን መሥራቱን እንቀጥላለን" ብለዋል።

የሦስተኛ ወገን የእውነታ ማረጋገጫ ፕሮግራሙም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን ነው የገለጹት። የአፍሪካ ቼክ ዋና ዳይሬክተር ኖኮ ማክጋቶ በበኩላቸው፣ በፕሮግራሙ ውስጥ ተጨማሪ ቋንቋዎች መካተታቸው እንዳስደሰታቸው እና በርካታ ቋንቋዎች በሚነገርባቸው እንደ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ እና ሴኔጋል ውስጥ በተለያዩ የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የእውነታ ማረጋገጫ መተግበሩ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ፌስቡክ/ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የታገቱ ተማሪዎችን አስመልክቶ የሶሻል ሚዲያው ንቅናቄ!

የሶሻል ሚዲያ ንቅናቄዎች ምን ይመስላሉ ብለን ቃኝተን ነበር ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተጠለፉ ተማሪዎችን አስመልክቶ በርካታ ሰዎች እነዚህን ፎቶዎች ተጠቅመው መንግስት እውነታውን እንዲገልጽ ሲጠይቁ አስተውለናል፡፡ አብዛኞቹ ልጄን መልሱልኝ የሚሉና #Bringbackourstudents የሚሉ ናቸው፡፡

#Facebook
#Tiwtter
#instagram

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot