ሰበር ዜና‼️
የኢትዮ ቴሌኮም የሴኪዩውሪቲ ዲቪዥን ሀላፊ ኮለኔል #ጉደታ_ኦላና በቁጥጥር ስር ዋሉ። ኮለኔል ጉደታ ኦላና በሜቴክ ውስጥ የተፈፀመ የሙስና ወንጀልን የሚያጠኑ ባለሙያዎች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ በመፈጸም እና የአቃቤ ህግ ስራን በማደናቀፍ ተግባር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ኮሎኔል ጉደታ ኦላና‼️
የዐቃቤ ህግን ስራ ለማደናቀፍ የሞከረው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበ። የቀድሞው የኢትዮ ቴሌኮም የሴኪዩውሪቲ ዲቪዥን ኃላፊ የነበሩት ኮሎኔል #ጉደታ_ኦላና በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ቀርበዋል፡፡
ተጠርጣሪዉ የሙስና ወንጀልን እያጣሩ ባሉ ባለሙያዎች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ በመፈጸም እና የፌደራል የዐቃቤ ህግን ስራ በማደናቀፍ ተግባር ተጠርጥረው መቅረባቸውን የፌዴራል መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡
በተጠርጠጣሪው በባለቤቱ ስም 438 ሺህ 222 ብር በኦሮሚያ ኢንትርናሽናል ባንክ አፍሪካ ቅርጫፍ መኖሩን እንዲሁም በ2010 ሚያዚያ ወር ሱሉልታ አካባቢ 550 ሺህ ብር በመንደር ውል መሸጣቸውን በማስረጃነት ለፍርድ ቤት አቅርቧል።
ተጠርጣሪው በተከላካይ ጠበቃው አማካኝነት የቀረበበት የምርመራ መዝገብ ተገቢነት እንደሌለው በማስረዳት በዋስ ሊወጣ እንደሚገባ ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር ከተመለከተ በኃላ ፖሊስ ቀሪ የምርመራ ሰራዎቹን አጠናቆ እንዲያቀርብ በማለት ተጨማሪ 7 የምርመራ ቀናትን በመፍቀድ ለህዳር 20 ቀን 2011ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

#update የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት በኢትዮ-ቴሌኮም የሴኪዩሪቲ ዲቪዥን ሃላፊ ኮሎኔል #ጉደታ_ኦላና ላይ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቀደ። ተጠርጣሪው ግለሰብ ኮሎኔል ጉደታ ኦላና ህዳር 6 ቀን 2011 ዓ.ም በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎች ላይ ምርመራ በሚያደርጉ የዐቃቤ ህግና ፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ ዛቻና ማስፈራራት በማድረግ የምርመራ ሂደቱን አደናቅፈዋል በሚል ነበር የተያዙት። ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ በኮሎኔል ጉደታ ኦላና ዙሪያ የሚሰራቸው ቀሪ ስራዎች እንዳሉት በመግለጽ የተጨማሪ የ14 ቀን ፈቃድ እንዲሰጠው ጠይቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኮሎኔል ጉደታ ኦላና‼️
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ሕግ በኮሎኔል #ጉደታ_ኦላና ላይ የጠየቀውን የ15 ክስ የመመስረቻ ቀናት በአብላጫ ድምጽ አፀደቀ።
የፍርድ ቤት 10ኛ የወንጀል ችሎት የኢትዮ-ቴሌኮም የሴኪዩሪቲ ዲቪዥን ኃላፊ ኮሎኔል ጉደታ ኦላና ላይ ክስ ለመመስረት ዐቃቤ ሕግ በጠየቀው የ15 ቀን ክስ የመመስረቻ ቀን ላይ በአብላጫ ድምጽ ነው ውሳኔ የሰጠው።
በሜቴክ ውስጥ የተፈፀመ የሙስና ወንጀል በሚያጣሩ ባለሙያዎች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ በመፈጸም እና የዐቃቤ ህግ ስራን በማደናቀፍ ተግባር ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።
ዐቃቤ ሕግም ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ መዝገቡን ያስረከበው መሆኑን ጠቁሞ በኮሎኔል ጉደታ ኦላና ደረሰ የተባለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ መዝገቡን ለማደራጀትና ክስ ለመመስረት ነው ተጨማሪ ጊዜውን የጠየቀው።
ፍርድ ቤቱ በአብላጫ ድምጽ ለክስ መመስረቻ የተጠየቀውን ቀን በመፍቀድም ለጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
ምንጭ፦ ENA