TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ!

ዜጎች በኢትዮጵያ ሰላም መስፈን ጥቅማቸው የሚነካ በሚመስላቸው ግለሰቦች ወጥመድ ወደ #ግጭት እንዳይገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሳሰቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንት ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች የሚነሱት አገሪቱ ሰላም ከሆነችና ዴሞክራሲያዊ ባህል እየዳበረ ከመጣ ጥቅማቸው የሚነካባቸው በሚመስላቸው ግለሰቦች ነው።

በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ አልፎ አልፎ የሚታዩ ግጭቶች ቀደም ሲል በተለያዩ ወንጀሎች የተሳተፉና በህግ እንዳይጠየቁ ጊዜ መግዣ አድርገው በሚቆጥሩ ግለሰቦች የሚፈጸሙ እንደሆኑ ተናግረዋል።

በመሆኑም ኀብረተሰቡ በሃሳብ ልዕልና የማያምኑና በማንኛውም አጋጣሚ ችግር መፍጠር የሚፈልጉ አካላትን ሊታገላቸው ይገባል።

በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እነዚህ ግለሰቦች በሚያጠምዱት ወጥመድ ወደ ግጭት እንዳይገቡ ነው ያሳሰቡት።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዜጎች በአገሪቱ የዴሞክራሲ ባህል ለማዳበር በሚካሄዱ የለውጥ ሂደቶች የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባም  አስገንዝበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ፅ/ቤት🔝የስብሰባ ጥሪ ለተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ለማክሰኞ፤ ህዳር 18 ቀን 2011።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ🛫ባህር ዳር

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ወደ ባህርዳር እያቀኑ ነው፡፡ 300 የሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ለ ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በዛሬው ዕለት የአማራ ክልል ዋና ከተማ ወደ ሆነችው ውቢቷ ባህር ዳር እያመሩ ይገኛሉ፡፡ በምክትል ከንቲባው የሚመራው የልዑካን ቡድን በሶስት ቀን የባህርዳር ቆይታው ብሄራዊ ሃብታችን የሆነውን ጣናን እየተፈታተነ ያለውን #የእንቦጭ_አረምን ያርማል፥ የህዝብ ለህዝብ ውይይት ከከተማዋ ወጣቶች እና ከከተማዋ ሀላፊዎች ጋር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፡ አዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሼህ አላሙዲን🔝

A developing fake news story...

በሚድያ ተቋሙ ድረ-ገፅ ላይ እንደዚህ አይነት ዜና #የለም

©ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ወረዳ ትናንት ምሽት በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኝነት ሃላፊ ኮማንደር #አስቻለው_ዓለሙ እንደገለፁት አደጋው የደረሰው ከአርሲ ነገሌ ከተማ 27 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ቡልቡላ ከተማ ሲጓዘ የነበረ ኮድ 3 -41772 ኦ.ሮ የሆነ አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ስድስት ሰዎችን አሳፍሮ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ባለሶስት እግር ባጃጅ ጋር በመጋጨቱ ነው።

በአደጋው በባለሶስት እግር በባጅ ውስጥ የነበሩ ስድስት ሰዎችና ሁለት እግረኞች ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን ኮማንደሩ ተናግረዋል።

አደጋውን ያደረሰው አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪና ረዳቱ ለባቱ ከተማ ፖሊስ እጃቸውን ሰጥተዋል።

የሟቾቹች አስከሬን በባቱ ሆስፒታል ምርመራ ከተደረገለት በኋላ ለቤተሰቦቻቸው መስጠቱን ኮማንደር አስቻለው ተናግረዋል።

“አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው ከመጠን በላይ በሆነ ፍጥነት ደርቦ ለማለፍ በመፈለጉ ምክንያት አደጋው ደርሷል” ብለዋል።

ባለሶስት እግር ባጃጅ ሶስት ሰዎች ብቻ መጫን ሲገባው ከመጠን በላይ መጫኑም ተገቢ እንዳልነበረ ኮማንደር አብራርተዋል።

አሽከርካሪዎች የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ህግና ደንብ በማክበር በሰውና ንበረት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት በመከላከል ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ኮማንደር አስቻለው መልእክት አስተላልፈዋል።

ምንጭ :- የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ‼️

የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተለያዩ ዘርፎች ጥፋት የሰሩ የስራ ሀላፊዎችን ለህግ ለማቅረብ የምርመራ ስራውን አበርትቶ መቀጠሉን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተናገረ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለሸገር እንደተናገረው በመጭዎቹ መቶ ቀናት በተመረጡ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ ምርመራውን ለመቀጠል ውጥን ይዟል፡፡

የኢኮኖሚ አሻጥር፣ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ ገንዘብ በህገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ማሸሽ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራባቸዋል ተብለው ከተመረጡ ዘርፎች መካከል ናቸው ብለዋል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ #ዝናቡ_ቱኑ፡፡ሥርዓት አልበኝነትን ለመቆጣጠርም አጥፊ የተባሉትን ለይቶም ለህግ ለማቅረብ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የምርመራ ስራውን ማበርታቱን ተናግረዋል፡፡

ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርም ሌላው በ100 ቀኑ እቅድ ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎችን ለመያዝ ከሚሰራባቸው ዘርፎች መካከል ነው ተብሏል፡፡

ዘርፉ እየተለየ ምርመራ የማድረግና ተጠያቂዎችን ለህግ የማቅረቡ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም የ100 ቀን እቅድ አውጥቶ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እየሰራ መሆኑን ተሰምቷል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ ዝርዝር መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሹመት🔝

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ክብር አቶ #ገዱ_አዳርጋቸው ለሁለት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ሹመት መስጠታቸው
ተገለጸ ፡፡

ሹመቱ የተሰጣቸው የስራ ኃላፊዎች አቶ #ዮሐንስ_ቧያለው እና አቶ #አለባቸው_የሱፍ ናቸው፡፡

አቶ ዮሐንስ ቧያለው ከህዳር ሰባት ቀን 2011 ዓ.ም ጀምረው በርዕሰ መስተዳደሩ ጽ/ቤት የበይነ መንግስታት ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ተሹመዋል፡፡

አቶ አለባቸው የሱፍ ደግሞ ከህዳር አንድ ቀን 2011 ዓ.ም ጀምረው የዚሁ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ መሾማቸው ታውቋል፡፡

አቶ ዮሐንስ ቀደም ሲል በመንግስት የተለያዩ ኃላፊነቶች ሲሰሩ መቆየታቸውና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በመምህርነት እያገለገሉ ነበር፡፡

አቶ ዮሐንስ ቧያለው በቅርቡ ብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን አካሄዶ ስሙን ወደ አማራ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (አዴፓ)ሲቀይር የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው እንደተመረጡ ይታወሳል፡፡

አቶ አለባቸው የሱፍም በተለያዩ የመንግስት የስራ ሓላፊነቶች በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ምንጭ፦ የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት(Amhara Democratic Party /ADP/ CC office)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አልተፈቱም‼️ሼህ ሞሃመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ከእስር አልተፈቱም። በማዕበራዊ ሚዲያ እየተረሰራጨ ያለው ዜና ፍፁም ከእውነት የራቀ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሊታረም ይገባል‼️ዩኒቨርሲቲዎች የእውቀት ስፍራ ናቸው። ለሀገር ለውጥ ትልቁን ድርሻ በሚወስዱት ተቋማት ውስጥ ሆኖ #ዱላ መያዝ እና #ድንጋይ መወራወር ብሎም እርስ በእርስ መጋጨት ተገቢ አይደለም።

ይታረም‼️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ5 ሺ 160 ዓመት እስር ፍርድ🔝

ጓቲማላዊው የቀድሞ ወታደር በሀገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት በተፈጸመ ጭፍጨፋ እጁ አለበት በሚል ከ5 ሺህ 160 ዓመት እስር ተፈረደበት፡፡

በፈረንጆቹ 1982 ጓቲማላ ውስጥ ዶስ ኤሬስ በተባለች ሀገር በተፈጸመ ጭፍጨፋ ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን በ36 ዓመታት #የእርስ_በእርስ ጦርነት አሳዛኙ አጋጣሚ ነው ተብሏል።

የቀድሞው ወታደር ሳንቶስ ሎፔዝ በአሜሪካ ስልጠና የተሰጣቸው የጓቲማላ ካይበለስ ሃይሎች አባል እንደነበር ተገልጿል።

ሎፔዝ በመንደሯ ከሞቱት ሰዎች መካከል በ171ዱ በእያንዳንዳቸው 30 ዓመት እስራት የተቀጣ ሲሆን በህይወት የተረፈች ሴት ልጅ #እንድትገደል በነበረው ሚና ተጨማሪ 30 ዓመት ተቀጥቷል።

በጓቲማላ ህግ መሰረት ማንኛው ግለሰብ በእስር ከተቀጣ ከፍተኛው ቅጣት 50 ዓመት ነው።

ከፈረንጆቹ 1960-1996 በቆየው የ36 ዓመታት የጓቲማላ የእርስ በእርስ ጦርነት ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሰላማዊ የማያን ማህበረሰብ ናቸው።

ምንጭ፦ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ📎

ዋሽንግተን ዩኒቨርሰቲ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር  ተባብረው ሊሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በአሜሪካ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቋሚ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር #ካሳ_ተክለብርሃን ከዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ የሚልጋርድ የቢዝነስ ትምህርት ቤት ኃላፊዎች ጋር ተባብረው በሚሰሩበት መንገዶች ላይ ምክክር ማድረጋቸውን  ተነግሯል፡፡

አምባሳደሩ  ከትምህርት ቤቱ ዲን ሃዋርድ ስሚዝ እና ሌሎች የተቋሙ ኃላፊዎች ጋር ነው በከፍተኛ የትምህርት መስክ ሊኖር በሚችል ትብብር ዙሪያ የተወያዩት፡፡

በውይይቱ ማጠናቀቂ በዋሽንግተን ዮኒቨርስቲ እና ሌሎች የአገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሀከል ትስስር ለመፍጠር ከመግባባት መደረሱ ተጠቁሟል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መግለጫ ላይ እንደተጠቀሰው የሚልጋርድ የቢሰኮስ ትምህርት ቤት በአንደኛና በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚሰጥ ሲሆን የተመሰረተው እ.ኤ.አ. 1994 ነበር፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሰትኛ መረጃ🔝

በተለያዩ የፌስቡክ ገፆች ስለ ጣርማበር - መለያ - ሰፈሜዳ መገንጠያ የመንገድ ፕሮጀክት ይህንን ምስል አስደግፎ ሰሞኑን የተላለፈው መረጃ #ሀሰት መሆኑን የመንገዶች ባለስልጣን ዛሬ ገልፁዋል።

"በምስሉ ላይ የሚታየው የዚህን የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደት የሚያሳይ አለመሆኑን እንገልፃለን።"

©ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት(AP)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ALERT‼️በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እየሆነ ያለውን ጉዳይ የሚመለከተው አካል #ትኩረት እንዲሰጠው። ተማሪዎች ፍርሀት እንደተሰማቸው እና ሁኔታው እንዳሰጋቸው ተደጋጋሚ መልዕክቶችን እየላኩ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopua
#Update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድና ትራንስፖርት የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች #ሀብታቸውን አስመዘገቡ፡፡ በቢሮው ስር የሚገኙ ተጠሪ መስሪያ ቤቶችም የስራ ኃላፊዎች የሀብት ምዝገባና እድሳት አድርገዋል ተብሏል፡፡ ይህ አሰራርም ለሌብነት እና ንቅዘት የሚመቹ መንገዶችን ይዘጋል መባሉ ተሰምቷል፡፡ የአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ እስከ ህዳር 30፣ 2011 ዓ.ም የሀብት ማስመዝገቡ ስራ #ይቀጥላል ብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#የዝንጀሮ መንጋ በአዳማ ከተማ የአንድ ቀበሌ ነዋሪዎችን ሰላማዊ ህይወት እያወከው ነው-ከፌደራል ፖሊስ የተገኘ መረጃ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia