TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ወረዳ ትናንት ምሽት በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የስምንት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኝነት ሃላፊ ኮማንደር #አስቻለው_ዓለሙ እንደገለፁት አደጋው የደረሰው ከአርሲ ነገሌ ከተማ 27 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ቡልቡላ ከተማ ሲጓዘ የነበረ ኮድ 3 -41772 ኦ.ሮ የሆነ አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ስድስት ሰዎችን አሳፍሮ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ባለሶስት እግር ባጃጅ ጋር በመጋጨቱ ነው።

በአደጋው በባለሶስት እግር በባጅ ውስጥ የነበሩ ስድስት ሰዎችና ሁለት እግረኞች ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን ኮማንደሩ ተናግረዋል።

አደጋውን ያደረሰው አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪና ረዳቱ ለባቱ ከተማ ፖሊስ እጃቸውን ሰጥተዋል።

የሟቾቹች አስከሬን በባቱ ሆስፒታል ምርመራ ከተደረገለት በኋላ ለቤተሰቦቻቸው መስጠቱን ኮማንደር አስቻለው ተናግረዋል።

“አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው ከመጠን በላይ በሆነ ፍጥነት ደርቦ ለማለፍ በመፈለጉ ምክንያት አደጋው ደርሷል” ብለዋል።

ባለሶስት እግር ባጃጅ ሶስት ሰዎች ብቻ መጫን ሲገባው ከመጠን በላይ መጫኑም ተገቢ እንዳልነበረ ኮማንደር አብራርተዋል።

አሽከርካሪዎች የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ህግና ደንብ በማክበር በሰውና ንበረት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት በመከላከል ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ኮማንደር አስቻለው መልእክት አስተላልፈዋል።

ምንጭ :- የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ‼️

ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ በሕገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 55 ኩንታል ቡና ትናንት መያዙን ፖሊስ ገለጸ።

የምሥራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር #አስቻለው_ዓለሙ እንዳስታወቁት ከኅብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ የተያዘው ቡና ከ300 ሺህ ብር በላይ ግምት አለው።

ኮድ 3 አዲስ አበባ 36952 በሆነ የጭነት ተሽከርካሪ የተያዘው በአዳሚቱሉ ወረዳ ቆሬ አዲ ቀበሌ ሲደርስ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ መሆኑንም አስረድተዋል።

የተሽከርካሪው ሹፌርና ረዳቱ ለጊዜው ቢሰወሩም፣ወንጀለኞችን ለሕግ ለማቅረብ በክትትል ላይ እንደሚገኝ ኃላፊው ተናግረዋል።

ሕገ ወጥ ንግድ እንቅስቃሴ በአገር ኢኮኖሚ ላይ በተለይ ቡና የውጭ ምንዛሪ ምንጭ በመሆኑ ጉዳቱ የከፋ መሆኑ ኅብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር በመተባበር ድርጊቱን እንዲገታው አሳስበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በምሰራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ #መርመርሳ በተባለው አካባቢ ዛሬ ጠዋት  ባጋጠመው የተሽከርካሪዎች ግጭት የአስር ሰዎች ህይወት ማለፉን  ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር #አስቻለው_ዓለሙ እንደገለፁት ዛሬ ጠዋት 12 ሰዓት ተኩል አከባቢ አደጋው የደረሰው ከአዋሽ ሰባት  ኪሎ ከተማ 16 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ አዳማ ሲጓዝ የነበረ ሃይሩፍ የህዝብ ማመለለሻ ተሽከርካሪ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ይጓዝ  ከነበረ ዋልያ አገር አቋራጭ የህዝበ ማመላለሻ አውቶቡስ ጋር መርመርሳ በተባለው አካባቢ በመጋጨታቸው ነው።

በአደጋው በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኢት 01289 ሃይሩፍ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ ሾፌሩን ጨምሮ 9 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸውን አልፏል።

በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኢት 97486 ዋልያ አገር አቋራጭ አውቶቡስ ውስጥ ከነበሩ ተሳታፊዎች መካከል የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ኮማንደሩ ተናግረዋል።

በአደጋው ህይወታቸው ካለፈው ሌላ በአራት ሰዎች ላይ ከባድ በሶስት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን አመልክተው ተጎጂዎቹ በአዳማ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

“የአደጋው መንስኤ አለአግባብ ደርቦ ለማለፍ መሞከርና ቅድሚያ አለመስጠት ነው” ያሉት ኮማንደር አስቻለው  የአውቶቡሱ ሾፌር ለጊዜው ባለመገኘቱ ፖሊስ ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑን አስረድተዋል።

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia