TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለተወዳጇ ድምጻዊት እጅጋየሁ ሽባባው (#ጂጂ) ፣ ለጌትነት እንየው እና ለአበበ ብርሃኔ የዕውቅና ሽልማት ተበረከተ።

የዕውቅና ሽልማቱ የተበረከተው ዛሬ ለ15ኛ ጊዜ በተካሄደው የአማራ ክልል ባሕልና ኪነ ጥበባት ፌስቲቫል ላይ ነው።

#ጂጂ

እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) ለሀገር ባቀነቀነቻቸው ዘፈኖቿ ብዙዎችን ማስተሳሰሯ ተገልጿል።

የሀገር በቀል ሥራዎቿ በእጅጉ የሚወደዱላት ፣ #ኢትዮያዊነትን የምታስተጋባ ፣ በኢትዮጵያዊነት ፍቅር የተንቀለቀለች፣ ሀገርን ያስቀደመች፣ ሕዝብ የሚያስፈልገውን ሁሉ የምታቀነቅን ድንቅ የጥበብ ሰው ነች ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ የራሷን አሻራ ያሳረፈች፣ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ እያለች የተሰማች፣ ትንቢት የሚመስል ቃል አስቀድማ የተናገረች በሳል ድምጻዊት መኾኗም ተገልጿል።

#ጌትነት_እንየው

ጸሐፈ ተውኔት ፣ ገጣሚ ፣ ተዋናይ እና አዘጋጅ ጌትነት እንየው በጥበቡ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፆ ማደረጉ ተገልጿል።

በሳንሱር ሳቢያ በርካታ ፈተናዎች ቢገጥሙትም ለጥበብ ራሱን በመስጠት አስተዋጽዖ እያደረገ የመጣ አሁንም እያደረገ ያለ መኾኑ ተመላክቷል፡፡

ሁለገቡ የጥበብ ሰው ጌትነት እንየው የቀደመውን እና የአሁኑን ትውልድ የሚያገናኝ ድልድይ ነውም ተብሏል፡፡

በበሳል ብዕሩ እየነቀሰ የሚያወጣቸው ማኅበራዊ ጉዳዮች ድንቆች መኾናቸውም ተመላክቷል፡፡

#አበበ_ብርሃኔ

የዜማና የግጥም ደራሲው አበበ ብርሃኔም ዘመኑን ሙሉ ለጥበብ አስተዋጽዖ ማድረጉ ተገልጿል።

ልብን በሚመስጡ ዜማዎቹ፣ ሰምና ወርቅን በተሞሉ ግጥሞቹ ለጥበብ ብዙ ዋጋ መክፈሉ ተነግሯል።

ከቀደሙት አርቲስቶች እስከ ዘመኑ ድምጻውያን ድረስ ያልተቋረጠው የዜማና የግጥም ድርሰቱ ለጥበብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ተብሏል።

ባልተቋረጠው ጥበቡ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ከፍ አድርጓል፣ ከፍም እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ለሀገር ጥሩ በሙያው ቀዳሚ መኾኑን ተነግሯል፡፡

Via AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከ20 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው። በዛሬው ዕለት በርካታ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ። ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ፦ - ጅማ ዩኒቨርሲቲ - ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ ካምፓስ) - ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (በዋናው ግቢ) - አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ (ዋናው ግቢ) - ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ - ጂንካ ዩኒቨርሲቲ - ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ…
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመቄዶንያ መስራች አቶ ቢንያም በለጠ እና ለአርቲስት ደበበ እሸቱ ፤ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለተወዳጇ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ( #ጂጂ ) የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበርክተዋል።

አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች አቶ ቢንያም በለጠ ላከናወኗቸው በጎ ስራዎች የክብር ዶክትሬት አበርክቶላቸዋል። በሰሩት ስራ በሰው ልጆች ደህንነት ላይ ለሀገር የማይተካ አስተዋፅኦ ማበርከታቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው አርቲስት ደበበ እሸቱ በኪነጥበብ ዘርፍ ላበረከቱት ውለታ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል።

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ለድምጻዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

ዕውቅናው ሁለገቧ አርቲስት #የኢትዮጵያን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም በማስተዋወቅ እንዲሁም በኪነ ጥበብ #የአዊን_ሕዝብ_ቋንቋ እና #ባህል በማሳደግ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ነው የክብር ዶክትሬት የተበረከተላት።

የክብር ዶክትሬቱን የእጅጋየሁ ሽባባው ወላጅ እናት ተቀብለዋል።

@tikvahethiopia