TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️

የጋቦን ወታደሮች የሞከሩት መፈንቅለ-መንግሥት #መክሸፉን የአገሪቱ መንግሥት አስታወቀ። የመንግሥቱ ቃል-አቀባይ ጉይ በርትራንድ ማፓንጎ የጸጥታ ኹኔታው ወደ ነበረበት መመለሱን ተናግረው "ኹኔታው በቁጥጥር ሥር ውሏል" ብለዋል። ቃል-አቀባዩ የአገሪቱን ብሔራዊ የራዲዮ ጣቢያ በቁጥጥራቸው ሥር ካዋሉ አምስት ወታደሮች አራቱ #መታሰራቸውን ለሬውተርስ ተናግረዋል።

በድንገት ወደ ብሔራዊ የራዲዮ ጣቢያ የገሰገሱ ወታደሮች የአገሪቱ ሕዝብ በመንግሥቱ ላይ እንዲነሳ ጥሪ አቅርበዋል። በዋና ከተማዋ ሊበርቪል በሚገኘው የራዲዮ ጣቢያ አቅራቢያ የተኩስ ድምፅ ተሰምቷል። በዋና ከተማዋ የጸጥታ አስከባሪዎች መሰማራታቸው እና ለመጪዎቹ ቀናት በዚያው እንደሚቆዩ የመንግሥቱ ቃል-አቀባይ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ጵጥሮስ " አቋቁመናል ካሉት ውስጥ ሶስቱ #መታሰራቸውን የእንቅስቃሴው አስተባባሪ ነኝ ያሉ ዲያቆን አክሊሉ ዓለሙ የተባሉ ግስለሰብ ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ሶስቱ አባቶች የታሰሩት " መንበረ ጴጥሮስ " አቋቁመናል የሚል መግለጫ ከሰጡ በኃላ ሸገር ከተማ አስተዳደር በሚገኘው ቢሯቸው እንደሆነ እኚሁ አስተባባሪ ተናግረዋል።

የታሰሩት ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማዕረጋቸውን ገፍፌዋለሁ ያለቻቸው አባ ገብረማርያም ነጋሳ፣ አባ ወልደ ኢያሱስ ኢፋ እንዲሁም አባ ወልደኢየሱስ ተስፋዬ እንደሆኑ ለመረዳት ተችሏል።

ሌሎችም አብረው የነበሩ ግለሰቦች መያዛቸውም ተነግሯል።

የሸገር ከተማ አስታዳደር ፖሊስ ስለጉዳዩ ምንም ያለው ነገር የለውም።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትላንት ተቋቁሟል የተባለውን " መንበረ ጴጥሮስ " አውግዛ ፤ አሁን በሕገወጥ ድርጊታቸው የቀጠሉትን ቡድኖች በፍርድ እንደምትጠይቅ አሳውቃለች።

በኦሮሚያ ክልል ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት በእነ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የተመራ የ26 የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ተሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል።

ይህንን ሹመት ተከትሎም ቤተክርስቲያኗ በከፍተኛ ሁኔታ ያወገዘችና ግለሰቦቹንም የለየች ሲሆን ህገወጥ ባለችው ሹመት ላይ የተሳተፉ አካላትም ላይ እገዳ እና ማዕረጋቸውን የማንሳት ውሳኔ አሳልፋ ነበር።

እነ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በወቅቱ ቤተክርስቲያን " ህገወጥ ነው ! " ላለችው የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ያደረሳቸው ፤ " ቅዱስ ሲኖዶስ የተዋቀረው 85% ከአንድ ወገን በመሆኑ፣ ያለው የውስጥ አሰራር ችግር፣ አባቶችን ከየአካባቢው ከማፍራት ይልቅ ከአንድ ወገን ብቻ የመሾም ችግር ፣  የሚመደቡት አባቶች የህዝቡን ባህል እና ቋንቋ ባለማወቃቸው ለምእመናን እምነት መዳከም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገ መሆኑ ... " የሚሉና ሌሎች ምክንያቶች እንደነበሩ ይታወሳል።

ረጅም ጊዜ ከፈጀ አለመግባባት በኃላ በተደረጉ ሰፊ ውይይቶች፣ ምክክር እና መግባባት፣ መንግሥትም ገብቶበት በቤተክርስቲያን በቀረበ ጥሪ እነ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን ጨምሮ ሎሎችም ብፁዓን አባቶች ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሰው አሁን ላይ በስራ ላይ ይገኛሉ።

ከተወገዙት እና ከተለዩት ውስጥ ግን 4 አባቶች ጥሪውን ተቀብለው ያልመጡ ሲሆን አሁን 2015 ዓ/ም የተቋቋመ ነው ባሉት " የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ " መንበር መሰየም በማስፈለጉ " የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መንበረ ጴጥሮስ " አቋቁመናል ሲሉ በይፋዊ መግለጫ አሳውቀዋል።

ይህንን መግለጫ በሸገር ከተማ ከሰጡ በኃላ #መታሰራቸውን የእንቅስቃሴው አስተባባሪ ነኝ ያሉ ግለሰብ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia