TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጉዞ_ዓድዋ_6🔝

ታላቁን የዓድዋ ድል ለመዘከር በየአመቱ የሚካሔደው የእግር ጉዞ ዘንድሮም ለ6ኛ ግዜ ቀጥሏል። ከሐረርና አዲስ አበባ የተነሱት ተጓዦች በድምሩ ከሺህ በላይ ኪሎሜትሮችን አቋርጠው #መቐለ_ከተማ እንደገቡ ታላቁን ኢትዮጵያዊ ጀግና ራስ አሉላ እንግዳን (አባ ነጋ) ለማስታወስ የሽሬ ልጆች መቐለ ከተማ በመግባት የአዲስ አበባ እና የሐረር ተጓዦችን ተቀላቅለዋል።

ብዛታቸው 5 የሆኑት #የሽሬ_ልጆች ከመቐለ እስከ ዓድዋ እናት ሀገራቸው ኢትዮጵያን እና ታላቁን የዓድዋ ድል ለማግዘፍ እንደ ታላቁ ራስ አሉላ አባ ነጋ ከወንድም እህቶቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።
"ታሪካዊ #ጀግኖቻችን የልዩነታችን ምክንያት ሳይሆኑ የአንድነታችን መሰረት ናቸው"

#ፍቅር_ለኢትዮጵያ !!
#የምናቋርጣቸው_የሀገራችንን_መንደሮች_እንጂ_ድንበሮች_አይደለም
#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም

Via Yared Shumete
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀለ ~ ኣነ ወያነ እየ🔝

በዛሬው እለት በትግራይ ክልል #መቐለ_ከተማ «እኔ ወያኔ ነኝ» በሚል መሪ ቃል #የህወሓትን 44ኛ #የምስረታ_በዓል በማስመልከት የሩጫ ውድድር ተካሂዷል።

Via Getu Temegen
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካቲት 11 በፎቶግራፍ🔝በትግራይ ክልል #መቐለ ከተማ የተከበረው የህወሓት 44ኛ የምስረታ በዓል። "ስእላዊ መግለፂ ኣከባብራ በዓል 11 ለካቲት 2011 ዓ/ም'

#Tigray #መቐለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ

"ዘመቻ መለስ ለአረንጓዴ ልማት" በሚል መሪ ቃል ከ80 ሚልዮን ችግኝ በላይ በዚህ የክረምት ወቅት ለመትከል የታቀደ ሲሆን እስከ ትናንት ድረስ 30ሚልየን ችግኞች ተተክለዋል። በዛሬው እለት በትግራይ #መቐለ ከተማ የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የክልሉ አመራሮች፣ የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ አባላት ፣የክሉሉ የፀጥታ ሀይል አባላት፣ ከተለያዩ የክልል ቢሮዎች የተውጣጡ የመንግስት ሰራተኞች እና ነዋሪዎች በተገኙበት ችግኝ ተከላ ተካሂዷል። ዛሬ ሀምሌ 22 /2011 በክልል ደረጃ 9 ሚልየን ችግኞች እንደሚተከሉ ታውቋል።

Via Tigray Express
@tsegabwolde @tikvahethiopia