TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጉዞ_ዓድዋ_6🔝

ታላቁን የዓድዋ ድል ለመዘከር በየአመቱ የሚካሔደው የእግር ጉዞ ዘንድሮም ለ6ኛ ግዜ ቀጥሏል። ከሐረርና አዲስ አበባ የተነሱት ተጓዦች በድምሩ ከሺህ በላይ ኪሎሜትሮችን አቋርጠው #መቐለ_ከተማ እንደገቡ ታላቁን ኢትዮጵያዊ ጀግና ራስ አሉላ እንግዳን (አባ ነጋ) ለማስታወስ የሽሬ ልጆች መቐለ ከተማ በመግባት የአዲስ አበባ እና የሐረር ተጓዦችን ተቀላቅለዋል።

ብዛታቸው 5 የሆኑት #የሽሬ_ልጆች ከመቐለ እስከ ዓድዋ እናት ሀገራቸው ኢትዮጵያን እና ታላቁን የዓድዋ ድል ለማግዘፍ እንደ ታላቁ ራስ አሉላ አባ ነጋ ከወንድም እህቶቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።
"ታሪካዊ #ጀግኖቻችን የልዩነታችን ምክንያት ሳይሆኑ የአንድነታችን መሰረት ናቸው"

#ፍቅር_ለኢትዮጵያ !!
#የምናቋርጣቸው_የሀገራችንን_መንደሮች_እንጂ_ድንበሮች_አይደለም
#ኢትዮጵያዊነት_ይለምልም

Via Yared Shumete
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዶክተር #ኤልያስ_ገብሩ የፌስቡክ ገፅ!
.
.
"የሚጓዙት በዝናብ ነው!
የሚጓዙት በምሽት ነው!
የሚጓዙት ለሰላም ነው!
የሚጓዙት ለፍቅር ነውና በውሽንፍሩ መሐል ነጩን የሰላም አርማ ከፍ አድርገው ይዘዋል። ለኢትዮጵያ ለአንድነት እንጓዛለን! እኛ ልጆቿ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም ብለው የተነሱትን የTIKVAH ቤተሰቦች እናመሰግናለን። በሁሉም የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ሲመጡ የጀግና አቀባበል ይደረግላቸው። ትላንት በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ደስ የሚል የአንድነት መንፈስ ፈጥረው ተመልሰዋል። ቀጣይ መዳረሻቸው የሐዋሳ ዩኒቨርስቲ እንደሆነም አሳውቀዋል።
#ጀግኖቻችን_ናችሁ!
#Keep_Walking #My_Generation"

@tsegabwolde @tikvahethiopia