TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በአዲስ አበባ 29 የቤት አልሚ ኩባንያዎች ቦታቸውን #እንዲነጠቁ ተወሰነ‼️

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ #ታከለ_ኡማ አስተዳደራቸው ባስጠናው ጥናት መሠረት ዝቅተኛ አፈፃፀም ያስመዘገቡ 29 የቤት አልሚ (‘ሪል ኢስቴት’) ኩባንያዎች ቦታቸው ተነጥቆ በቤቶች ልማትና አስተዳደር በኩል በማኅበር ለሚደራጁ ኗሪዎች እንደሚያስተላለፉ መወሰኑን አስታወቁ።

ዛሬ፣ የካቲት 6 በጽሕፈት ቤታቸው የአጥኚ ቡድኑ ግኝት በቀረበበት ወቅት እንደተገለጸው ጥናቱ በቦሌ፣ በየካ፣ በንፍስ ስልክ ላፍቶ፣ በኮልፌ ቀራኒዮ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ቤት ለማልማት መሬት የተረከቡ ኩባንያዎች ላይ መካሔዱ ተጠቁሟል። በጥናቱ ውጤት መሰረት በአምስቱ ክፍለ ከተሞች መሬት ከተረከቡት ቤት አልሚ ኩባንያዎች መካከል 19 ኩባንያዎች የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ ቤት ገንብተው ለባለ ቤቶቹ ያስረከቡ ሲሆን 52ቱ ኩባንያዎች ደግሞ መካከለኛ አፈፃፀም በማስመዝገብ በተለያዩ የግንባታ ደረጃ ላይ የሚገኙ መሆኑም ታውቋል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢ/ር #ታከለ_ኡማ የኪራይ ቤት ክፍያ ጭማሪ ተወደደብን ካሉ የፒያሳ አከባቢ ነጋዴዎች ጋር በስራ ቦታቸው ተወያይተዋል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ አነሳሽነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር "የወንዞች እና የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ መናፈሻ" ፕሮጀክት በይፋ ስራ የማስጀመር ስነ-ስርዓት ኢ/ር #ታከለ_ኡማ፣ የፌደራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተከናውኗል፡፡

፨ በ3 ዓመታት ውስጥ የሚጠናቀቀው፣ 56 ኪ.ሜ የሚሸፍነው እና 29 ቢሊዮን ብር ውጪ ይደረግበታል ተብሎ የሚገመተው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፦

•በ29 ቢሊዮን ብር ወጭ ይከናወናል፤ በሦስት ዓመታት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

•ከእንጦጦ ተራራ በጉለሌ በኩል አፍሪካ ህብረት እንዲሁም ከእንጦጦ በአፍንጮ በር በባንቢስ አድርጎ አቃቂ የውሃ ማጣሪያን ይሸፍናል(56 ኪሎ ሜትር)

•ድልድዮች፣ ሰው ሰራሽ ሐይቆች፣ አረንጓዴ ቦታዎች፣ የመዝናኛ ማዕከላት፣ የውኃ ትራንስፖርት እና የንግድ ማዕከላት ይገነቡበታል።

በተያያዘ መረጃ፦ በ50 ሄክታር ላይ ተግባራዊ የሚደረግ፣ 2.5 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚደረግበት እና በ1 ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ በተለምዶ ሸራተን ማስፋፊያ በሚባለው ቦታ ፓይለት ፕሮጀክት ይፋ ተደረጓል።

ምንጭ፦ ወ/ሮ መስከረም (የከንቲባው ቴክኒካል አማካሪ) ለTIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአምቦ ልማት ገቢ ማሰባሰቢያ!

በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የአምቦ ልማት ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ከ400 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገለፀ።

በአዲስ አበባ ሀያት ረጀንሲ ሆቴል በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ #ለማ_መገርሳና ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ ወቅቱ ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ ለህዝብ የሚሰራበት መሆኑን በመጥቀስ፥ ይህ ጅምር ፕሮግራም በሌሎች አካባቢዎችም #ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።

በዕለቱ በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢየ ፕሮግራም ከ400 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን የአምቦ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ሃላፊ ዶክተር #መንግስቱ_ቱሉ ለfbc ተናግረዋል።

በዚህ መሰረትም ፦

1. አቶ በላይነህ ክንዴ 15 ሚሊየን ብር
2. አቶ ገምሹ በየነ 5 ሚሊየን ብር
3. አቶ ተክለብርሀን አምባዬ 1 ሚሊየን ብር
4. ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ 100 ሺህ ብር
5. ጋዜጠኛ ግሩም ጫላ 100 ሺህ ብር እና ሌሎች ባለሃብቶችም ለልማቱ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም ለልማቱ ገቢ ማሰባሰቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የእጅ ስዓታቸውን ለጨረታ ያቀረቡ ሲሆን ፥ ጨረታውንም አቶ ገምሹ በየነ በ 5 ሚሊየን ብር ማሸነፍ ችለዋል።

በአጠቃላይ በዕለቱ በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ከ 400 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉ ነው የተገለፀው።

በገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ በተገኘው ገንዘብም በአምቦ ከተማ 12ሺህ ተማሪዎችን ማስተናገድ የሚችል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣20 ሺህ ሰው የሚይዝ ደረጃውን የጠበቀ ስቴዲየም፣ለሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን የአርት ጋለሪ ግንባታና ለሌሎች ፕሮጀክቶች ስራ ማስፈፀሚያ የሚውል ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በክቡር የኢፌድሪ ጠ/ሚንስተር #አብይ_አህመድ(ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሊተገበር የታቀደው የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክትን ለመደገፍ የቻይና መንግስት #ፍላጎት እንዳለው ገለፀ፡፡ ለዚህም የቻይና መንግስት የባለሞያ ልዑካን ቡድን የከተማ አስተዳደሩ የጀመረውን የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክትን በገንዘብ እና የቴክኒክ ዕገዛ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ከኢ/ር #ታከለ_ኡማ ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል፡፡ በዚህም የቴክኒክ ቡድኑ የቻይና መንግስት ፕሮጀክቱን የሚደግፍበት ሁኔታ ላይ ጥናት የሚያደርግ ይሆናል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በአዲስ አበባ ከተማ የተከበረው #123ኛው የአድዋ ድል በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር #በሰላም መጠናቀቁን የከተማ ፓሊስ ኮሚሽን እስታወቀ። የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በሚኒልክ አደባባይ እና በመስቀል አደባባይ  በደማቅ ስነ ስርዓት የተከበረው የድል በዓል ሰላማዊ ሆነ መጠናቀቁን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ሁኔታ የተከበረው 123ኛው የአድዋ ድል በዓል ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ ሰላማዊ እንደነበረ አንስተዋል፡፡ ይህ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች እና ለሁሉም የፀጥታ  አካላት በኮሚሽኑ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር #ታከለ_ኡማ በዓሉ በደማቅ ሁኔታ እንዲከበርና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላስቻሉ ሁሉም አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካቲት 11...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ የተገኙበት የህወሃት 44ኛ ዐመት የምስረታ በዓል በአዲስ አበባ #ኢንተር_ኮንትኔንታል ሆቴል እየተከበረ ይገኛል። #በድምፂ_ወያነ እና #በትግራይ_ቲቪ በቀጥታ እየተላለፈ ስለመሚገኘ መከታተል ትችላላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ #ታከለ_ኡማ በእጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት ለእጣ ከቀረቡ ቤቶች ውስጥ ቤቶቹ በተሰሩባቸው አካባቢዎች ላሉ #አርሶ_አደሮችና የአርሶ አደር ልጆች #እጣ_ሳይገቡ እንዲያገኙ የከተማ አስተዳድሩ ውሳኔ ማሳለፉን ተናግረዋል፡፡ ከተማዋ የምታካሂደው የተቀናጀ ልማት ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነትን ያጋገጠ እንዲሆን በማድረግ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ከንቲባው አመልክተዋል፡፡ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ #ዣንጥራር_አባይ በእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት አገራዊ የቤት ችግርን ለመፍታት የህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት ጭምር የቤት ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ በዘላቂነት የቤት ችግርን ለመፍታትም የግሉን ዘርፍ ማሳተፍ አማራጭ የሌለው ተግባር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢንተር ኮንቲኔታል በተካሄደው የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር #ታከለ_ኡማ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ #ለባለእድለኞች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ልማትን በጋራ መጠቀም ተገቢ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው፣ በቤቶቹ ግንባታ ከይዞታቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ለከፈሉት #መስዕዋትነት ዋጋቸውን እንደሚያገኙም አመልክተዋል፡፡ በዚህም ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ልማት ሲባል ከመሬታቸው ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች #ያለእጣ ቤት #እንዲሰጣቸው የከተማ አስተዳደሩ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ‼️
(20/80ና 40/60)

የ20/80ና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ይፋ ከመሆን ጋር ተያይዞ ቦታው የኦሮሚያ ነው በሚል ከ10 በላይ በሚሆኑ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ተቃውሞዎች ተቀስቅሰዋል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ የተገነቡባቸው አካባቢዎች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሆነው የአዲስ አበባ መስተዳድር ውሳኔ የሚያሳልፈው እንዴት ነው፤ ለተፈናቃዮቹ አርሶ አደሮች የተሰጠው ካሳ እዚህ ግባ የማይባል ነው፤ የተቀናጀው ማስተር ፕላን ቅጥያ ነው የሚሉ ሀሳቦችን ተቃዋሚዎቹ አንስተዋል።

#በምስራቅ_ኦሮሚያ ጪሮ ከተማ ቢቢሲ ያነጋገረው አንድ ሰልፈኛ " በዚህ ተቃውሞ ላይ ዋነኛ መልዕክታችን በአዲስ አበባ አካባቢ ያሉት መሬቶች ለኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ሊመለስ ይገባል" የሚል ነው። ተቃዋሚው ጨምሮም ለብዙዎች ሞት ምክንያት የሆነው አወዛጋቢው የተቀናጀ ማስተር ፕላን ሊመለስ አይገባም ብሏል።

ተቃውሞዎቹ በሻሸመኔ፣ ጪሮ፣ ጂማ፣ አሰላ፣ አዳማና ሂርና ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተስፋፉ ሲሆን በሻሸመኔ አካባቢ የሚገኙ ሰልፈኞች "ኦዲፒ ያልነውን ረስታችሁታል፤ መሬታችን የደም ስራችን ነው" የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ነበር።

በትናንትናው ዕለት 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል የዕጣ ማውጫ ስነ ስርአት ለተጠቃሚዎች የተላለፈ ሲሆን፤ ከአካካቢው ለተነሱ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ያለ እጣ እንዲሰጣቸው በከተማው አስተዳደር ካቢኔና በቤቶች አስተዳደር ውሳኔ መሰረት ያለ ዕጣ እንዲተላለፍ መወሰኑን ምክትል ከንቲባ #ታከለ_ኡማ በትናንትናው ዕለት ገልፀዋል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ሲገነቡ የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ ያልደበቁት ምክትል ከንቲባው "በተለይም የእርሻ መሬታቸውን ለነዚህ ተግባራት ሲሉ የለቀቁና ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ቀውስ የተዳረጉ የአርሶ አደር ቤተሰቦችና ልጆቻቸው ህመማችሁ የእኛ መሆኑን እንድታውቁ" የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ከንቲባው ይህንን ቢሉም ኦሮሚያ ውስጥ ተቀስቅሶ ለረጅም ጊዜ ለዘለቀው ሕዝባዊ ተቃውሞ መነሻ ምክንያት እንደሆነ የሚነገርለትና ከ2006 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የአዲስ አበባና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ቅጥያ ነው የሚሉ ትችቶችም እየተሰሙ ነው።

ምንም እንኳን የተቀናጀው ማስተር ፕላን ከፍተኛ ተቃውሞዎችን ተከትሎ ውድቅ ቢደረግም የቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባና ኦህዴድ ሊቀ መንበር አቶ ኩማ ደመቅሳ ጉዳዩ ከመፈናቀል ጋር አብሮ ስለመጣ እንጂ "ተራማጅ አስተሳሰብ ነው ብዬ አስባለሁ፤ ጊዜ ሊወስድ ይችላል እንጂ ማስተር ፕላኑ አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል" ብለው ለቢቢሲ መናገራቸው የሚታወስ ነው።

ምንም እንኳን ከመንግሥት በኩል ምንም አይነት መግለጫ ባይሰጥም በቅርቡ ከውጭ ሀገር የተመለሰው የተባበሩት ኦነግ በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ያለውን ድንበር መወሰን ያለበት የኦሮሚያ ክልል ነው የሚል ነው።

በ13ኛው ዙር የ20/80 ቤቶች 32ሺ 653 ቤቶችና በ2ኛ ዙር የ40/60 ቤቶች ለተጠቃሚዎች የሚተላለፉ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ 1ሺ 248 ስቱዲዮ፣ 18ሺ 823 ባለ አንድ መኝታ፣ 7ሺ 127 ባለሁለት መኝታ እና 5ሺ455 ደግሞ ባለ ሶስት መኝታ መሆናቸው ተገልጿል።

በ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ የሚካተቱትም በ1997 ተመዝግበው በ2005 ዓ.ም በነባር መደብ የተመዘገቡና በ2005 ዓ.ም የአዲስ ባለ ሶስት መኝታ ተመዝጋቢ ደንበኞች መሆኑ ተገልጿል።

Via BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia