TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀዋሳ🔝

ህገመንግሰታዊ #መብታችን_ይከበር በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ሰለማዊ ሰልፍ እየተደረገ ነው። በሰለማዊ ሰልፉ ከሲዳማ 36 ወረዳዎች እና ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ነው።

ሰለማዊ ሰልፈኞቹ “ህገ መንግስቱ ይከበር ! የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ መልስ ይሰጠው! የሪፈረንደም ቀን ይወሰን !” የሚሉና መሰል መፈክሮችን እያሰሙ ነው።

መነሻውን ከሀዋሳ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በሀዋሳ ዓለምአቀፍ ስታዲየም መደረሻውን በማድረግ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክረሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዲን/ ከወራት በፊት ባደረገው በ10ኛ መደበኛ ጉበኤው የሲደማ ብሔር በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ተቀብሎ ለህዝበ ውሳኔ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መምራቱ ይታወሳል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰልፉ በሰላም ተጠናቋል~ሀዋሳ🔝

"ህገመንግሰታዊ #መብታችን_ይከበር!" በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ የተካሄከው ሰለማዊ ሰልፍ #በሰላም ተጠናቋል። በሰልፉ ላይ ከሲዳማ 36 ወረዳዎች እና ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል።

ሰለማዊ ሰልፈኞቹ፦ “ህገ መንግስቱ እንዲከበር፤ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ መልስ እንዲሰጠው፤ የሪፈረንደም ቀን በአስቸኳይ ተወስኖ ለህዝብ እንዲነገር ጠይቀዋል።

በሰልፉ ላይ ሰልፈኞች ከያዟቸው መፈክሮች መካከል፦

•ሲዳማነት ከሌለ #ኢትዮጵያዊነት የለም!

•ለውጡን እንደግፋለን!

•በኮሚሽን የሚመለስ ጥያቄ የለንም!

•ለማንም ዘረኛ የማንበረከክ በባህላችን የምንኮራ ህዝን ነን!

•ህገ መንግስታዊ #መብታችን ይከበር!

•የሪፈረንደም ቀን #ተቆርጦ ይነገረን!

•የሲዳማ ህዝብ መንግስትን እንዳከበረ መንግስትም የሲዳማን ህዝብ ያክብር!

•ሁሉንም #ብሄር እንወዳለን፤ እናከብራለን!

•ሁሉንም #ሀይማኖት እንወዳለን፤ እናከብራለን!

•የሁሉንም #ባህል እንወዳለን፤ እናከብራለን! የሚሉት ይገኙበታል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰልፉ በሰላም ተጠናቀል...

#በሀዋሳ_ከተማ ህገ መንግስታዊ #መብታችን ይከበር በሚል ሲደረግ የነበረው ሴቶች ብቻ የተሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ #በሰላም ተጠናቀዋል::

@tsegabwolde @tikvahethiopia