ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ግጭት‼️
በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ከባለፈው ረቡዕ ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት የሟቾች ቁጥር 24 መድረሱ ተሰምቷል፡፡ ከሟቾቹ በተጨማሪ በ167 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የአካባቢው አስተዳደር ዛሬ ለጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ከባለፈው ረቡዕ ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት የሟቾች ቁጥር 24 መድረሱ ተሰምቷል፡፡ ከሟቾቹ በተጨማሪ በ167 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የአካባቢው አስተዳደር ዛሬ ለDW ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የጸጥታ አካላት ወደ ሥፍራው መግባታቸውን ተከትሎ ግጭቱ #እየተረጋጋ መምጣቱን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በመስቃን እና በማረቆ ህዝቦች መካከል ባለፈው ረቡዕ ግጭቱ የተቀሰቀሰው በመሬት ይገባኛል በተፈጠረ አለመግባባት ነበር። ግጭቱ የተከሰተበት ቦታ በጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ሰሜን ዲዳ እና ባቶ ፎቶ በተባሉ ሁለት ቀበሌዎች የነበረ ሲሆን በዚህም ምክንያት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም መፈናቀላቸውን የዓይን እማኞች ለDW ተናግረዋል።
በደቡብ ክልል መስቃን ወረዳ መሰል ግጭት ሲከሰት የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ባለፈው መስከረም በደረሰው ግጭት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን እና ንብረት መውደሙ ይታወሳል።
ምንጭ፦ DW አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia