TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዱራሜ🔝በዱራሜ ከተማ ሲደረግ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል። ህዝቡም ወደየቤቱ እየተመለሰ ነው።

©ሲሳይ ከዱራሜ(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ማርቆስ‼️

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር #መብራት ለአንድ ወር ያክል እንደሚጠፋ በመወራቱ ወፍጮ ቤቶች በወረፋ መጨናነቃቸውን ተሰምቷል።

ስለሚወራው ወሬ አብመድ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰሜን ምዕራብ ሪጂን የትራንስሚሽን ሰብስቴሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ውበት አቤን በስልክ አነጋግሯል፡፡

‹‹ሽብር ለመፍጠር የሚነዛ #አሉባልታ ነው፤ በባለፈው በመኪና ክሬን ዋና የኃይል መስመሩ ተነካክቶ ችግር ተፈጥሮ ኃይል ተቋርጦ ነበር፡፡ እሱንም አስተማማኝ በሆነ መልኩ ጠግነን ሥራ አስጀምረናል፡፡ አሁን ለመብራት መጥፋት የሚሆን ምክንያት የለም›› ብለዋል፡፡

የደብረ ማርቆስና አካባቢውን የኃይል አቅርቦት የበለጠ አስተማማኝ ለማድረግ ተጨማሪ ትራንስፎርመር ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑን የገለጹት አቶ ውበት ኅብረተሰቡ #የሚወራውን ሙሉ በሙሉ ወደ ጎን በመተው መደበኛ ሕይወቱን እንዲመራ አሳስበዋል፡፡

‹‹ለአንድ ወር ቀርቶ ለአንድ ቀን የምናቋርጥበት ምክንያት የለም፡፡ የተለመዱ የደቂቃዎች መቆራረጦችም እንዳይኖሩ አቅማችንን አሟጠን እየሠራን ነው›› ብለዋል አቶ ውበት፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ማርቆስ አገልግሎት መስጫ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ቸኮልም ‹‹ወሬው ሰንብቷል፤ ማን እንዳስወራው ግን አላወቅንም፡፡ ሕዝቡ መደናጥ እንደሌለበት በከተማ አስተዳደሩ በኩልም መረጃ ለማድረስ ሞክረናል፡፡ በዝናብና ዛፎች ንክኪ ምክንያት ድንገተኛ ችግር ካላጋጠመን በቀር የኃይል አቅርቦት ሥራችንን ያለመቆራረጥ እያደረስን ነው›› ብለዋል፡፡

በደብረ ማርቆስ ከተማ በጥቅምት ወር አጋማሽ ከአንድ ሳምንት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ እንደነበር ይታወቃል።

ምንጭ፦ የአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአቋም መግልጫ🔝የዱራሜው ሰላማዊ ሰልፍ የአቋም መግለጫ ከላይ የምትመለከቱት ነው።

ምንጭ፦ fi(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH v1.1.apk
4.3 MB
ያውርዱት እና ስልኮት ላይ ይጫኑት!!
ከቴሌግራም ቻናላችን በተጨማሪ የስፖርት፣ መዝናኛ እና ቢዝነስ መረጃዎችን ታገኛላችሁ!!
TIKVAH-ETH የሞባይል አፕሊኬሽን‼️

ከእናንተ በደረሰው አስተያየት መሰረት የተስተካከሉ ችግሮች፦

🔹ለመጫን ሲሞከር “Error while parsing" አይልም

🔹አልፎ አልፎ “Stopped Working" አይልም

🔹ወደ ላይ እና ወደ ታች scroll ሲደረግ አይንቀራፈፍም

አሁንም ያላችሁን አስተያየት በሚከተለው bot ያድርሱን @tikvahethbot
አቶ ያሬድ ዘሪሁን‼️

መርማሪ ፖሊስ የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ሀላፊ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አቶ #ያሬድ_ዘሪሁን በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በከባድ ሙስና ወንጀል እንደጠረጠራቸው
ገለፀ።

ተጠርጣሪው ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበዋል።

መርማሪ ፖሊስ አቶ ያሬድ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የቀድሞ ሀላፊ ጋር በመመሳጠርና ቀጥተኛ ትእዛዝ በመቀበል በርካታ ኢሰብዓዊ ድርጊት መፈፀማቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

🔹በአሁኑ ወቀት ጉዳያቸው በፍርድ ቤቱ በመታየት ላይ ይገኛል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ያሬድ ዘሪሁን‼️

ፖሊስ በያሬድ ዘሪሁን ላይ ያቀረበውን የክስ ማመልከቻ ለፍርድ ቤት አሰምቷል።

ፖሊሲ እንዳለው አቶ ያሬድ ዘሪሁን አሁን በቁጥጥር ስር ካልዋለው የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገለግሎት የቀድሞ ኃላፊ #ጌታቸው_አሰፋ ጋር #በመመሳጠርነ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በመቀበል በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል፡፡

ዜጎችን አፍነው በመውሰድና በማሰር ብልታቸው ላይ ውሃ በማንጠልጠል ራቁታቸውን ቆሻሻ ውስጥ በመጣል ጉንዳን እንዲበሉ አድርገዋል ብሏል ፖሊስ፡፡

መርማሪ ፖሊስ እንዳለው በተፈፀመባቸው ድብደባ ብዛትም የሞቱ ዜጎችም አሉ፡፡ ግለሰቦች ወደ ኤርትራ ሄደው ህገ ወጥ መሳሪያ እንዲያስገቡ በማቀነባበር ህዝብ እንዲሸበርና ተጠርጣሪዎች ላይ እንዲሳበብ ማድረግ
በሚል ወንጀል እንደጠረጠራቸውም ፖሊስ አስታውቋል። ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ 14 ቀን እንዲሰጠው ፍርድቤቱን ጠይቋል ፡፡

ተጠርጣሪው አቶ ያሬድ በበኩላቸው ከህግ አማካሪያቸው ጋር መገናኘት እንደሚፈልጉ በመግለፅ ለሚቀጥለው ማክሰኞ ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ከማንም ጋር እንዳልገናኝ እየተደረኩ ነው፤ አንድ ክፍል ውስጥ ብቻዬን ነው የታሰርኩት ሲሉም ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ ተጠርጣሪው ከማንም ጋር እንዳልገናኝ እየተደረኩ ነው፤ አንድ ክፍል ውስጥ ብቻዬን ነው የታሰርኩት ሲሉ ያቀረቡትን ያስተባበለ ሲሆን፥ ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪው ከህግ ባለሙያ ጋር እንዲገናኙና የተጠየቀው የ14 ቀን ቀጠሮ ላይ ብይን ለመስጠት ለፊታችን ማክሰኞ 8 ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የቀድሞ የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ሀላፊ አቶ #ጌታቸው_አሰፋ እስካሁን በፖሊስ ቁጥጥር ውስጥ እንዳልዋሉ ለመስማት ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቴዲ ማንጁስ‼️

በሶማሌው ክልል ግጭት የተጠረጠሩት #ቴወድሮስ_አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) ላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ #እጃቸው አለበት በተባሉት ቴወድሮስ አዲሱ ላይ ፖሊስ ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ እንደሚያስፈልገው የጠየቀ ሲሆን፥ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎትም የወንጀሉን #ውስብስብነትና ቀሪ ስራዎችን በማገናዘብ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለህዳር 21 ቀን 20011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኮሎኔል አሰፋ ዮሃንስ‼️

የቀድሞው የመከላከያ ፓዎር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጅ ኮሎኔል #አሰፋ_ዮሃንስ ከ2 ሚሊዮን ዶላር በላይ የህዝብ ሀብት በማባከን #መጠርጠራቸውን ፓሊስ አስታወቀ፡፡

ፖሊስ እንዳለው ተጠርጣሪው የበለስ ቁጥር 1 የስኳር ፕሮጀክት ከአንድ የቻይና ኩባንያ ጋር ፈርሞት የነበረው ኮንትራት ያለጨረታ በ5 ሚሊዮን 720 ሺህ ዶላር እንዲሻሻል አስደርገዋል፡፡

ኩባንያውም ገንዘቡን ተቀብሎ ምንም ሳይሰራ ከሀገር እንዲሸሽ በማድረግ ራሳቸውንና ኩባንያውን ብቻ አላግባብ ተጠቃሚ አድርገዋል፡፡

በዚህም የህዝብና የመንግስት ሀብት መዝብረው አስመዝብረዋል በሚል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረዋል፡፡

ኮሎኔል አሰፋ የ6 ሚሊዮን 400 ሺህ ዶላር ሌላ የፕሮጀክት ኮንትራት ፈርሞ የነበረ ሌላ ኩባንያም ከዚህ ውስጥ 1 ሚሊዮን 920 ሺህ ዶላር በቅድሚያ ተቀብሎ ግዴታውን ሳይፈፅም እንዲጠፋ አስደርገዋል በሚል ተጨማሪ የሙስና ወንጀልም ተጠርጥረዋል ብሏል ፖሊስ፡፡

ተጠርጣሪው የተከላካይ ጠበቃ ለመቅጠር አቅም እንደሌላቸው በመግለፅ መንግስት እንዲመድብላቸው ፍርድ ቤቱን የጠየቁ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በበኩሉ ግራ ቀኙን አዳምጦ ውሳኔ ለመስጠት ለመጪው ሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ጥሏል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ🔝በተቋሙ ውስጥ የሚማሩ ሴት ተማሪዎች ደህንነታች አልተጠበቀም፣ እንዘረፋለን፣ መፀዳጃ ቤት እንኳን ስንሄድ እየተሳቀቅን ነው የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይስጠን በማለት ሰልፍ እያደረጉ ናቸው።

ፎቶ፦ የTIKVAH-ETH አባላት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE ሼኽ ሙሐመድ አሊ አላሙዲን በሚቀጥለው ሳምንት ከእስር #እንደሚለቀቁ አንድ የሳውዲ አረቢያ ጋዜጣ ይፋ አድርጓል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በመጪው እሁድ የሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በሚያካልላቸው አካባቢዎች የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች የሚጠቀሙባቸው #ተለዋጭ መንገዶች ይፋ ሆነዋል።

44 ሺህ ሯጮችን የሚያሳትፈው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከነገ በስትያ መነሻና መድረሻውን ስድስት ኪሎ የሰማዕታት ሐውልት አድርጎ ይከናወናል።

ሩጫው ከስድስት ኪሎ አደባባይ ተነስቶ ምኒሊክ ሆስፒታል-ቀበና-እንግሊዝ ኤምባሲ-በሾላ ገበያ ዞሮ በሱመያ መስጊድ-ሲግናል-አቧሬ-ራስ አምባ ሆቴል አድርጎ ወደ አራት ኪሎ በመሄድ ፍጻሜውን ስድስት ኪሎ አደባባይ ያደርጋል።

ይህን ተከትሎም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዚህ አካባቢ የሚያልፉ አሽከርካሪዎች የሚጠቀሟቸውን ተለዋጭ መንገዶች ይፋ አድርጓል።

በዚህ መሰረት ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ ሽሮ ሜዳ ፈረንሳይ ለጋሲዮን የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ከጊዮርጊስ- በአፍንጮ በር-በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአልአቅሳ መስጊድ ወደ መነን አቅጣጫ መጠቀም ይችላሉ።

ከሽሮ ሜዳና ፈርንሳይ መስመር ተነስተው ወደ ስድስት ኪሎ፣ አራት ኪሎና መስቀል አደባባይ የሚጓዙ ደግሞ በተለዋጭነት በአፍንጮ በር- ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን-ቸርችል ጎዳናን ይጠቀማሉ።

እንዲሁም ከሽሮ ሜዳ ተነስተው ወደ መገናኛና ቦሌ አቅጣጫ የሚሄዱ አሽከርካሪዎች በአፍንጮ በር-ጊዮርጊስ አድርገው በቸርችል ጎዳና ኢሚግሬሽን-በካሳንቺስ-ኡራኤል ቤተክርስቲያን አድርገው ወደ መገናኛ መጓዝ ይችላሉ ብሏል።

በተጨማሪም ከነገ ህዳር 8 ቀን 2011 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ሩጫው በሚካሄድባቸው መንገዶች ላይ አሸከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia