TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ ዛሬ ህዳር 3/2016 ዓ.ም በመቐለ የተካሄደው የታክሲ አገልግሎት የማቆም አድማ ከማህበራቱ እውቅና ውጪ የተፈፀመና ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ሶስት የታክሲ ማህበራት ባወጡት መግለጫ አሳወቁ። ማህበራቱ ከሰዓት በኃላ ባሰራጩት ይፋዊ መግለጫ ፤ " ለመንግስት ያቀረብነው ጥያቄ በህጋዊ መንገድ እንዲመለስ ጥረት እያካሄድን ባለንበት ጊዜ አገልግሎት ማቋረጥ አግባብ አይደለም " ብለዋል። አድማ…
#Update

" የምንሰጠውን ምክርና ማሳሰብያ ችላ ብሎ በአድማው የሚቀጥል ባለንብረትና አሽከርካሪ ላይ #ጥብቅ_እርምጃ ይወሰዳል " - ወ/ሪት ራሄል ሃይለ

የትግራይ የትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ በመቐለ የተደረገው የታክሲ አገልግሎት ማቋረጥና አድማ " ህጋዊ አይደለም " ብሏል።

ቢሮው ከመቐለ የትራንስፓርት ፅህፈት ቤትና ፓሊስ በጋራ ' አካሄድኩት ' ባለው ግምገማ የታክሲ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች ቀድም ሲል አገልግሎት ለማቋረጥና አድማ ለመምታት የሚያበቃ ቅሬታና ጥያቄ አላቀረቡም ሲል ገልጿል።

የትግራይ የትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሪት ራሄል ሃይለ ህዳር 3/2016 ዓ.ም አመሻሽ ለሚድያ በሰጡት መግለጫ ፤ የታክሲ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች አገልግሎት የማቋረጥና አድማ የመምታት ደርጊቱ ችላ ተብሎ የማይታለፍ ህጋዊ እርምጃና ተጠያቂነት የሚያስከትል በመሆኑ በመገንዘብ ስራቸው ይቀጥሉ ዘንድ መክረዋል።

የመንግስት ምክርና ማሳሰብያ ችላ ብሎ በአድማ የሚቀጥል ባለንብረትና አሽከርካሪ ግን ጥብቅ እርምጃ ይወሰድበታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ለምለም ኪሓ ፣ ህዳሴና ሓወልቲ የተባሉ የመቐለ የታክሲ ማህበራት አመራሮች በማህተም አስደግፈው ህዳር 3/2016 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ለሚድያዎች በላኩት መግለጫ ፤ አግልግሎት ማቋረጡና አድማው ከእውቅናቸው ወጪ የተደረገ ኢ-ህጋዊ ነው ማለታቸው መዘገባችን ይታወሳል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

በመቐለ ከተማ የታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች ባደረጉት አድማ ነዋሪዎች ለእንግልት እና አላግባብ ለሆነ ወጭ ተዳርገዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ ያነጋገራቸው የታክሲ ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ በመሄድ ላይ የሚገኘው የኑሮ ሁኔታ ፣ የመኪና እቃ መለዋወጫ መወደድ የሹፌርና የረዳት ክፍያ ገበያ ላይ ባለው ታሪፍ መሸፈን እጅግ እንደከበዳቸው ፤ ያለው ታሪፍ እንዲስተካከል ከአንድ ወር በፊት መንግሥትን በማህበራቸው በኩል ቢጠይቁም ምላሽ ስላላገኙ ወደ አድማ እንደገቡ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia