TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የዓለም ጤና ድርጅት በቻይና የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው በሚል አወጀ። ድርጅቱ ቫይረሱን በዓለም አቀፍ የጤና ስጋትነት ያወጀው ከቻይና ውጭ ወደ ሌሎች ሀገራት መዛመቱን ተከትሎ ነው ተብሏል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እንዳስታወቁት፥ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ጤና ስጋትነት የታወጀበት ዋነኛው ምክንያት በቻይና እየሆነ ባለው ሳይሆን…
#NewsAlert

የዓለም ጤና ድርጅት ከ3 ዓመት በኃላ ኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ አጣዳፊ የጤና ስጋት መሆን #ማብቃቱን ይፋ አደረገ።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከዚህ ቀደም አውጀውት የነበረው የኮቪድ-19 የምድራችን አጣዳፊ የጤና ስጋት አሁን ላይ ማብቃቱን አሳውቀዋል።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው ትላንት ለዚሁ ጉዳይ የተቋቋመው ኮሚቴ ለ15ኛ ጊዜ በመገናኘት ባደረገው ስብሰባ ወቅት ባቀረበው ምክረ ሃሳብ መሆኑን ዶ/ር ቴድሮስ ገልጸው በዚህም መሰረት የኮሚቴውን ምክረ ሃሳብ በመቀበል የኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ አጣዳፊ የጤና ስጋትነት ማብቃቱን አውጀዋል።

ይህ ማለት ግን ኮቪድ አብቅቷል ማለት እንዳልሆነ አስገንዝበዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት እኤአ ጥር 20/2020 ላይ ነበር ኮቪድ-19 የዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ብሎ ያወጀው።

ይኸው ወረርሽኝ በትንሹ 20 ሚሊዮን ሰዎችን ገድሏል (እንደ WHO መረጃ) ፣ በርካቶችን ቤተሰብ አሳጥቷል ፤ የዓለምን ኢኮኖሚ እንዳልነበር አድርጓል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

ቦርዱ የህወሓትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ላይ ያስተላለፈውን የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ሥረዛ ፓርቲው " ይነሣልኝ " ሲል ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

ህወሓት ያቀረበው ጥያቄ ምንድነው ?

ህወሓት የፓርቲውን ህጋዊ ሰውነት ስረዛ፤ የፓርቲው ሃላፊዎች በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንደማይችሉ እና የፓርቲው ንብረት ተጠርቶ ፓርቲው ዕዳ ካለበት ለዕዳ መሸፈኛ እንዲውል፤ ቀሪው ገንዘብና ንብረት ለሥነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት እንዲውል ከዚህ በፊት በምርጫ ቦርድ የተላለፈው ውሳኔ እንዲነሳ ሲል በደብዳቤ ጠይቋል።

ለቦርዱ ውሳኔ ምክንያት የሆነው ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመፅ ተግባር አሁን ላይ ባይኖርም እንደገና ህጋዊ ሰውነቱን ለፓርቲው ለመመለስ የሚያስችሉ ድንጋጌዎች በአዋጅ 1162/2011 ተደንግጎ አይገኝም ሲል ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

በዚህም የህጋዊ ሰውነት ጥያቄ የማስመለስ ጉዳይ በህግ የተደገፈ ሆኖ እንዳላገኘው ቦርዱ አመልክቷል።

ፓርቲው ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ ለመንቀሳቀስ የሚችለው በአዋጅ 1162/2011 አንቀፅ 66 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት በድጋሚ የምዝገባ ጥያቄ ሲያቀርብ እና ቦርዱ ህጉን መሰረት አደርጎ ሲፈቅድ መሆኑን ቦርዱ ወስኗል።

የፓርቲው አመራሮች እና ንብረትን በተመለከተ የቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ ፓርቲው ላይ የሰጠው የስረዛ ውሳኔ ውጤቶች በመሆናቸው እንደአዲስ ሊጠየቁ የሚችሉ አይደሉም ያለው ምርጫ ቦርድ በዚህ በኩልም የተጠየቀውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

(ደብዳቤው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በትግራይ ክልል ከሚገኙ አባቶች ጋር ውይይት  ለማድረግ  የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን አሳወቀች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በግንቦት ወር 2015 ዓ.ም ባካሔደው የርክበ ካህናት ጉባኤ በትግራይ ክልል ከሚገኙ አባቶች ጋር የሚደረገው ውይይት ቀደም ሲል በቋሚ ሲኖዶስ በተሰየመው የልዑካን ቡድን አማካኝነት በአስቸኳይ  እንዲቀጥል መወሰኑ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ኮሚቴው ውይይቱን በተሳካ ሁኔታ ለማካሔድ የሚያስችለውን በእቅድ ላይ የተመሰረተ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲያከናውን የቆየ ሲሆን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ውይይቱ በተሳካ ሆኔታ መካሔድ የሚችልበትን ሁኔታ እንዲያመቻች በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተጻፈ ደብዳቤ ጥያቄውን አቅርቧል።

የልዑካን ቡድኑ አባላትም ከቅዱስ ፓትርያርኩ የተጻፈውን ደብዳቤ በአካል በመገኘት ለክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት በማቅረብ ከሚመለከታቸው የክልሉ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር የክልሉ ጊዚያዊ መንግስት ለውይይቱ መሳካት በሚያደርገው ድጋፍ ዙሪያ ውይይት በማድረግ መመለሱ ተገልጿል።

ስለሆነም ለክልሉ መንግስት በቀረበው ጥያቄ መሰረት ሁለቱም አካላት በሚያመቻቹት ጊዜና ቦታ ውይይቱ የሚካሔድ ይሆናል ተብሏል።

በዚህም መሰረት የጠቅላይ ቤተክህነት ልዑካን ቡድን ውይይቱን ውጤታማ ለማድረግ ይቻል ዘንድ እስከ አሁን ያከናወናቸውን ተግባራትና ወደፊት ውይይቱን ስኬታማ በሆነ መንገድ ማካሔድ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ሰኞ ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

መግለጫውን ተከትሎ ጉዳዩ በቀኖና ቤተክርስቲያን መሰረት የመጨረሻ እልባት እንዲያገኝ በፍጥነት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመግባት በሒደቱ የሚመዘገቡ ለውጦችን ሁሉ በመገናኛ ብዙሃን ይገለፃሉ ተብሏል።

መረጃው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የፌዴራል ፖሊስ ለልጆቻችሁ #ሙሉ_ኃላፊነት ይወስዳል ፤ አስተማማኝ ጥበቃም ያደርግላቸዋል " - የጋምቤላ ትምህርት ቢሮ ከሰሞኑን በጋምቤላ ክልል የፀጥታ ችግር መከሰቱና የሰዎች ህይወት ማለፉ ፣ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም በክልሉ የሰዓት እላፊ ገደብ ታውጆ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ…
#NewsAlert

በጋምቤላ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለት ቦታዎች እንዲሰጥ ተወሰነ።

በጋምቤላ ክልል ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ እና በጋምቤላ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንደሚሰጥ የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

የክልሉ መንግሥት ፤ " በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ብቻ ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ያለውን ጫና ለመቀነስ ታስቦ ፈተናው በኮሌጅም ጭምር እንዲሰጥ ተወስኗል " ብሏል።

የክልሉ መንግስት ውሳኔውን ያሳወቀው ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ዛሬ ወደ ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ መግባት ጀምረዋል።

በተለይም በ #ኑዌር_ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዛሬ ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ መግባት መጀመራቸው ተገልጿል።

#አኙዋ_ዞን፣ በከፊል ከ #ኢታንግ ልዩ ወረዳና ከ #ጋምቤላ_ከተማ ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ በጋምቤላ ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች በነገው ዕለት እስከ ቀኑ ሰባት ሰዓት ወደተመደቡበት የመፈተኛ ጣቢያ በመሄድ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የክልሉ መንግስት አሳስቧል።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴርና ሀገር አቀፍ የፈተናዎች አገልግሎት ከክልሉ መንግስት ጋር በመነጋገር ነው በሁለት ቦታ ፈተናው እንዲሰጥ የተወሰነው።

መረጃው ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ ዛሬ የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ በጸሎት ተከፍቷል። " የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በክልል ትግራይ ባሉ አህጉረ ስብከት ለመንፈሳዊ አገልግሎት ተመድበው የነበሩ አራት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በፈጸሟቸው የቀኖና ቤተክርስቲያን እና የሕግጋተ ቤተክርስቲያን ጥሰቶች ዙሪያ ለመወያየትና ሕግጋተ ቤተክርስቲያንን መሠረት ያደረጉ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ጉባኤውን…
#NewsAlert

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በክልል ትግራይ ኤጲድ ቆጶሳት ሹመት ጉዳይ ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በኃላ ውሳኔዎችን አሳለፈ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፦

1. ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ የመቀሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የእንቅስቃሴው ሰብሳቢ
2. ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በክልል ትግራይ የማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
3. ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ የአዲግራት ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
4. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ   መሪነት እጅግ አሳዛኝ ኢ-ሲኖዶሳዊ የሆነ አስነዋሪ፣ ሕገ-ወጥ፣ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት በመፈጸም 10 መነኮሳትን በእጩነት በመምረጥና ለዘጠኙ ህገወጥ ሲመት ፈፅመዋል ብሏል።  

ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ድርጊታቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያንን በማታለል የክህደት እና የኑፋቄ ተግባር ፈፅመዋል ሲል ገልጿል።

በዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ፤ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ እንደለያቸው ገልጿል።

ሥልጣነ ክህነታቸውና የማዕረግ ስማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ውሳኔ የተነሣ ስለሆነ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቀድሞ ዓለማዊ ስማቸው እንዲጠሩ ውሳኔ ተላልፏል።

በቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያም በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን እንደለያቸው ተገልጿል።

በሠሩት የቀኖና ጥሰት ተጸጽተው ይቅርታን ቢጠይቁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምህረት ደጆች ሁል ጊዜ ክፈት በመሆናቸው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት እንቀበላቸዋለን ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል።

የኤጲስ ቆጶስነት ሹመት አግኝተናል፤ ተሹመናል እያሉ የሚገኙ 9 መነኮሳት ፦
- አባ ዘሥላሴ ማርቆስ
- አባ ኃይለ ሚካኤል አረጋይ
- አባ እስጢፋኖስ ገብረ ጊዮርጊስ
- አባ መሓሪ ሀብቶ
- አባ ኤልያስ ታደሰ ገብረ ኪዳን
- አባ ጽጌ ገነት ኪዳነ ወልድ
- አባ ዘርአ ዳዊት ብርሃነ
- አባ ዮሐንስ ከበደ
- አባ የማነ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል በሕገ ወጥ መንገድ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንን ጥሰው የተገኙ በመሆኑ አስቀድሞ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸው ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት ተሽሮ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያ በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን ለይቷቸዋል፡፡
  
ቅዱስ ሲኖዶስ ህገወጥ ሢመቱ እንዲፈጸም ከመጀመሪያው ጽንሰ ሀሳብ ጀምሮ መሪ ተዋናይና ቀስቃሽ ነበሩ ያላቸው አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤልና ሂደቱን በዋና አስፈጻሚነት በመምራትና መግለጫ በመስጠት ላይ ያሉት መ/ር ተስፋዬ ሐደራ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተወግዘው ከቤተክርስቲያን ተለይተዋል ብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ " መንበረ ሰላማ "  የሚለው ስያሜ ሕገወጥ መሆኑን ገልጾ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ትውፊትም ሆነ በቀደምት አብያተ ክርስቲያናት ትውፊት የማይታወቅ፣ ሃይማኖታዊ መሠረት የሌለው፣ ከቀኖና የወጣ፣ አስተዳደራዊ መዋቅርን የሚያዛባ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም ብሏል።

(ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

Pic ፡ EOTC TV

@tikvahethiopia
#NewsAlert

በአዲስ አበባ ሞተር ብስክሌት እስከ ረቡዕ ድረስ ታገደ።

የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ፤ በከተማው ለሚገኙ የሞተር ብስክሌተኞች በሙሉ ባስተላለፈው መልዕክት ከነገ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ እሮብ ነሀሴ 3/2015 ዓ.ም እስከ ምሽት 12:00 ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ፍፁም የተከለከለ መሆኑን አሳውቋል።

ቢሮው ፤ ክልከላው በምን ምክንያት እንደተጣለ በግልፅ ያለው ነገር የለም።

ክልከላው #የፀጥታ እና #የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት መሆኑን የገለፀው ቢሮው ፤ የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል።

ይህንን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም ቢሮው አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara እጅግ አስከፊ ከነበረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ገና ያላገገመው አማራ ክልል ዳግም የግጭት ቀጠና እየሆነ መምጣቱና የፀጥታውም ሁኔታ አሳሳቢ የሆነ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገልጿል። በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በ " ፋኖ " የታጠቁ ኃይሎች እና በ " መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች " መካከል በተከሰቱ ግጭቶች የሰዎች ህይወት አልፏል፤ ጉዳትም ደርሷል። በተለይ ከጥቂት ወራት ወዲህ " የክልሉና የአማራ…
#NewsAlert

የአማራ ክልል መንግሥት በክልሉ ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ ለመቆጣጠር የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር ጥያቄ አቀረበ።

የክልሉ መንግሥት ፤ ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ በመደበኛው የህግ ማስከበር ስርዓት #ለመቆጣጠር_አዳጋች ሆኖ መገኘቱን ገልጿል።

በዚህም የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር ይፋዊ ጥያቄ አቅርቧል።

በክልሉ የተከሰተው የሰላም መደፍረስ በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እያደረሰ መሆኑን የክልሉ መንግሥት ገልጿል።

" የተከሰተውን የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር ለማዋል እስካሁን በክልሉና በፌደራል የፀጥታ ኃይሎች በኩል በርካታ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል " ያለው የአማራ ክልል መንግሥት ፤ " የፀጥታ መደፍረስና ጥቃት ፤ ንፁሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት በአስቸኳይ ለማስቆም የፌደራል መንግስት ከመደበኛው ህግ የማስከበር ስርዓት ባሻገር በኢፌዴሪ ህገ መንግስት መሰረት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ በአፋጣኝ እንዲተገበር " ሲል ጥይቄ አቅርቧል።

" ክልሉ ወደ ቀደመው መረጋጋቱ እንዲመለስ ፤ ዜጎች ሰላማቸው ተመልሶ አርሶአደሩ ወደ እርሻው ክልሉም ወደ ልማት ስራዎች ፊቱን እንዲያዞር ለማድረግ መንግስት ያለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ ይገባል " በሚል የአማራ ክልል መንግሥት የፌደራል መንግስትን መጠየቁ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በመደበኛ የሕግ ማስከበር ስርአት ለመቆጣጠር አዳጋች ሁኔታ ተገኝቷል " - የአማራ ክልል መንግሥት በቀን 27/11/2015 ዓ/ም በአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ተፈርሞ ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በተላከ ደብዳቤ ፤ አሁን ላይ በአማራ ክልል ያለውን የፀጥታ ችግር በመደበኛው የሕግ ማስከበር ስርዓት ለመቋቋም የማይቻልበት ሁኔታ እንደተፈጠረ ይገልጻል። የፀጥታ መደፍረሱ በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ…
#NewsAlert

በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ።

የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት 23ኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዶ ነበር።

በዚህም ስብሰባ ፤ " የሕዝብን ሠላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ " በቀረበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6 /2015 ላይ መመምከሩ ተነግሯል።

ምክር ቤቱ ፤ " በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚታየውን በትጥቅ የተደገፈ ህገወጥ እንቅስቃሴ በመደበኛ የህግ ማስክበር ስርዓት ለመቆጣጠር ወደ ማይቻልበት ደረጃ የተሸጋገረ በመሆኑ፤ ይህ እንቅስቃሴ የክልሉን ነዋሪ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ያወከ እና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ፤ የሕዝብን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም ህግ እና ስርዓት ለማስከበር የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ እንቅስቃሴው በሃገር ደህንነት እና በህዝብ ሰላም ላይ የደቀነው አደጋ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መጥቷል፡፡ " ብሏል።

" መንግስት ትጥቅ አንስተው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ሁሉ የሰላም እና ህጋዊ መንገድን እንዲከተሉ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ " ያለው ምክር ቤቱ  " የታጠቁ ፅንፈኛ ቡድኖች እየፈፀሙ ባለዉ ጥቃት ምክንያት የክልሉ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል፡፡ " ሲል ገልጿል።

የክልሉ መንግስትም በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ያጋጠመው የፀጥታ መደፍረስ በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያስከተለ የሚገኝ መሆኑን በመግለጽ፣ ሁኔታውን በመደበኛው የህግ ማስከበር ሥርዓት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ፣ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ በኢፌድሪ ህገ መንግስት መሰረት እንዲደነግግ እና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ጥያቄ አቅርቧል ሲል አመልክቷል።

" በመደበኛ የህግ ስርዓትን መሰረት አድርጎ ይህን ፈር የለቀቀ  እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር አዳጋች ሁኔታ በመፈጠሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ " ሲል ምክር ቤቱ አሳውቋል።

በዚህም ፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው ረቡዕ፣ ሐሙስ እና ዓርብ ወደ ፦ - ደሴ (ኮምቦልቻ) - ጎንደር - ላሊበላ - ባህርዳር የሚደረጉ በረራዎች #የተሰረዙ መሆናቸውን አሳውቋል። ወደሥፍራው ለመጓዝ ትኬት የቆረጡ ደንበኞቹ ትኬታቸው ለአንድ (1) ዓመት ያህል የሚያገለግል መሆኑን አውቀው ወደፊት በፈለጉበት ቀን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ መቀየር የሚችሉ መሆኑን ገልጿል። ነገር ግን ገንዘብ ተመላሽ…
#NewsAlert

ወደ ጎንደር እና ባህር ዳር በረራ ነገ ይጀምራል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረው መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 4 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀምር መሆኑን ዛሬ አሳውቋል።

መንገደኞች በአቅራቢያቸው በሚገኙት የአየር መንገዱ ሽያጭ ቢሮዎች ወይም ወደጥሪ ማዕከሉ የስልክ ቁጥሮች 6787 / +251116179900 በመደወል መስተናገድ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከክልል በታች ያሉ መዋቅሮች እንዲደራጁ ለመወሰን የቀረበው ሞሽን በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ።

ሁለት መዋቅሮች በዞን እና ሶስት መዋቅሮች በልዩ ወረዳነት እንዲደራጁ የቀረበውን ሞሽን ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ የወሰነው።

በዚህም መሠረት :-

- የም ዞን

- ምስራቅ ጉራጌ ዞን

- ጠምባሮ ልዩ ወረዳ

- ቀቤና ልዩ ወረዳ

- ማረቆ ልዩ ወረዳ ሆነው የአስተዳደር መዋቅራቸው እንዲሻሻል በሞሽኑ ቀርቦ ፀድቋል።

የምክር ቤቱ ጉባኤም ተጠናቋል፡፡

መረጃው የደ/ሬ/ቴ/ድ ነው።

@tikvahethiopia