TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ታሪካዊ በረራ...🛩

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ ዳግም ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ ታሪካዊ በረራ ያደርጋል። የአውሮፕላኑ አብራሪ፣ የበረራ አስተናጋጅ እና መላው ሰራተኞች #በኢትዮጵያውያን_ሴቶች ሙሉ በሙሉ የሚመራ በረራ ነው የሚደረገው።

ኢትዮጵያ(አ/አ)🛫ኖርዌይ(ኦስሎ)

#አለም_አቀፍ_የሴቶችን_ቀን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሀገራት በፀጥታው ም/ቤት ምን አሉ?

#Russia

በUN ፀጥታ ም/ቤት የሩሲያ ተወካይ የኢትዮጵያ መንግስት ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ያወጀው የተናጥል የተኩስ አቁም በህወሓት ሀይሎች መጣሱ አሳዛኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የህወሓት ሀይሎች ከትግራይ ውጪ ወደ አማራና አፋር ክልሎች ጥቃት መክፈታውን፤የሀገር ውስጥ ፈናቃዮች ቁጥር በእጥፍ እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።

“የሰብአዊ ድጋፍ ጉዳይን ፖለቲካዊ ማድረግ ተገቢ አይደለም፣ በሚዲያ የሚካሄደው መርዛማ አካሄድ የመሳካት እድሉ አነስተኛ ነው” ብለዋል፤ሰብአዊ ድጋፍ ሲቀርቡ ለትግራይ ብቻ ተብሎ ሳይሆን፤ለአማራ፣ አፋር፣ ሶማሌና ኦሮሚያም ክልሎችም መሆን አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

“በኢትዮጵየ ፖለቲካው ውይይት እንደጀመር እንደግፋለን፤ ነገር ግን ውይይቱ ያለማንም ጣልቃ ገብነት #በኢትዮጵያውያን መሪነት ሊካሄድ ይገባል" ብለዋል።

ለኢትዮጵያ ሚደረጉ ድጋፎች የሀገሪቱን ሉአላዊነት እና አንድነት ባስጠበቀ መልኩ ሊካሄድ ይገባል ያሉ ሲሆን፤ ሰኔ ወር በተካሄደው ምርጫ ኢትዮጵያውያን የመረጡት መንግስት ሀገሪቱን ወደቀድሞ መስመር የመመለስ አቅም እንዳለው የሩሲያ መንግስት ያምናል ሲሉ ተግረዋል።

#China

የቻይና ተወካይ በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም አካላት በራሳቸው መንግድ በሚያድርጉት የፖለቲካ ውይይት ልዩነቶቻቸውን እንደሚፈቱ ቻይና ታምለች ብለዋል። በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ስራቸውን በሚሰሩበት ጊዜ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ባከበረ መልኩ መሆን ይገባል ብለዋል። ለኢትዮጵያ ሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። በሰብአዊ መብትና በሰብዓዊ ድጋፍ ስም በኢትዮጵየ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚደረጉ ጣልቃ ገብነቶችን ቻይና አጥብቃ ትቃወማለች ብለዋል።

ያንብቡ፦ telegra.ph/UNSC-08-27

@tikvahethiopia