TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Bahirdar

በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከተማ ማታ ማታ የሚኒቀሳቀሱ ባጃጆች ቁጥር እንዲወሰን ተደረግ።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ወንጀል እንዳይከሰት ለመቆጣጠር ያመች ዘንድ እንደሆነ ተነግሯል።

እንደሀገር ሆነ እንደ ክልል የተከሰተውን የፀጥታ ሁኔታ በተገቢ መንገድ ለመምራት በባህር ዳር በህጋዊ መንገድ ተደራጅተው የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የባጃጅ ማህበራት ከከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ጽ/ቤት፣ ከፖሊስና መሰል የህግና የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በሌሊት አገልግሎት የሚሰጡ ባጃጆች ተጠያቂነት ባለው አሰራር ታቅፈውና ለቁጥጥር እንዲያመች በቁጥር ተወስነው እንዲሰሩ መደረጉን የየማህበራቱ አስተባባሪዎች ተናግረዋል፡፡

በዚህ መሰረት ከስምንት የባጃጃ ማህበራት ውስጥ በስነ-ምግባር እና ለማህበረሰቡ ቅንና ታማኝ አገልግሎት ከሚሰጡ የባጃጅ አሽከርካሪዎች መካከል 120ዎችን በመመልመልና ከምሽቱ 3፡00 እስከ ንጋት 11፡00 ድረስ በሁሉም ቀበሌዎች እየተንቀሳቀሱ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል።

ይህ ለከተማው ሰላምና፣ ለማህበረሰቡ ደህንነት ሲባል የሚደረግ በመሆኑ የተመደቡ ባጃጆች ተጠያቂነት እንዲኖራቸው የማህበራቸውን ስምና አንፀባራቂ የደንብ ልብስ እንዲጠቀሙ፣ በዚያው ሰርጎ ገቦችን በመቆጣጠር በኩል ለሚደረገው ተግባር ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ መደረጉንም ገልፀዋል፡፡

ለዚህ ከተመደቡ ውጭ ማነኛውም ባጃጅ ከ3 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ እንደሌለበትና ይህን ውሳኔ ተላልፎ የተገኘ የባጃጅ አሽከርካሪ ካለ በህግ ይጠየቃል ተብሏል።

የተመደቡት 120 ባጃጆች ያለምንም ዋጋ ጭማሪና ያለ አድሎ በሌለበት ሁኔታ እንዲሰሩ በሚሰጡት አገልግሎትም እጥረት ካለ እየተገመገመ እንደሚስተካከል ከ #ባህርዳር_ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia