TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የአፍሪካ ህብረት⬇️

ኢትዮጵያ ወደ አገሪቱ ለሚገቡ አፍሪካውያን ተጓዦች የቪዛ ፖሊሲዋን #ለማቅለል መወሰኗን የአፍሪካ ህብረት አወደሰ፡፡

የህብረቱ ሊቀመንበር #ሙሳ_ፋኪ ማህመት ኢትዮጵያ ቪዛን አስመልክቶ ለምትወስደው እርምጃ እውቅና በመስጠት የቪዛ ስርዓታቸውን ያስተካከሉ ሌሎች የአፍሪካ አገራትንም አመስግነዋል፡፡

ሊቀመንበሩ አፍሪካውያን በአህጉራቸው ውስጥ እንደልባቸው የሚዘዋወሩበት ጊዜ እሩቅ እንደማይሆን ገልፀው ሌሎች የአፍሪካ አገራትም የቪዛ ስርዓታቸውን እንዲያሻሽሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የሁለቱ ምክር ቤቶችን ስራ መጀመር አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ከያዝነው አመት ጀምሮ የየትኛውንም የአፍሪካ አገር ፓስፖርት ለያዘ ግለሰብ ኦን አራይቫል ቪዛ የሚያገኝበት ሁኔታ እንደሚመቻች መግለፃቸው ይታወቃል፡፡

እኤአ 2018 ጥር ላይ የተፈረመውን ስምምነት እስካሁን 32 የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት የፈረሙት ሲሆን ቀሪ አገራትም እንዲፈርሙ ህብረቱ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፡- ሺንዋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ዋና ጸሃፊ የተከበሩ #ሙሳ_ፋኪ_ማሃማት ጋር እየተካሄደ ባለው የህብረቱ ማሻሻያ ዙሪያ ዛሬ ጥቅምት 27 2011 በፅ/ቤታቸው ተገናኝተው ተወያይተዋል። ውይይቱም ከህዳር 8-9 2011 በህብረቱ ማሻሻያ ዙሪያ ለሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት ልዩ የመሪዎች ጉባዔ ግብአት ይሰጣል።

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ፕሬዝዳንት #ሳህለወርቅ_ዘውዴ የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሆነው መመረጣቸው ለአህጉር ጥሩ ዜና እንደሆነ የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር #ሙሳ_ፋኪ ተናገሩ። ሚስተር ፋኪ ዛሬ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ከኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር በአህጉሪቱ ሰላምና ፀጥታ እንዲሁም አጀንዳ
2063 በተሰኘው የአፍሪካ ህብረት የልማት መርሃ ግብር ትግበራ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የካሜሩን አምባሳደርና በአፍሪካ ኅብረት የካሜሩን አምባሳደር እንዲሁም ልዩ መልዕክተኛ ጃኮስ አልፍሬድ ሰኞ፣ ነሐሴ 6/2011 ማለዳ ላይ ሞተው መገኘታቸውን የአፍሪካ ኅብረት ዋና ፀሐፊ #ሙሳ_ፋኪ_መሐመት በትዊተር ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል። በአፍሪካ ኅብረት ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ሞተው የተገኙት አምባሳደሩ፥ የህልፈታቸው ምክንያት በውል አልታወቀም። የአፍሪካ ኅብረትም #ለወዳጆቻቸው እና ለመላው #የካሜሩን ሕዝብ መፅናናትን ተመኝቷል።

Via #አዲስማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia