TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ-ፒያሳ⬆️

ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የአንድ ሰው ህይዎት ማለፉ ተሰማ።

አደጋው ዛሬ ማለዳ 12 ሰዓት ከ30 አካባቢ መድረሱን፥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር #ማርቆስ_ታደሰ ለfbc ተናግረዋል።

በወቅቱ ከፒያሳ ወደ ለገሃር ይጓዝ የነበረ ሚኒ ባስ ታክሲ ቼርችል ጎዳና ባንኮ ዲሮማ ትራፊክ መብራት ሲደርስ ከ ቪ8 መኪና ጋር #ተጋጭቶ አደጋው መድረሱንም ነው የተናገሩት።

እስካሁንም በአደጋው የአንድ ሰው ህይዎት ሲያልፍ፥ በ10 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት መደረሱን ኢንስፔክተር ማርቆስ ገልጸዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ሆስፒታሎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ኢንስፔክተር ማርቆስ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
ፎቶ፦ TIKVAH-ETH,FANA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሌላ አሳዛኝ መርዶ...

"ፀግሽ ትላንት ለሊት የኩሪፍቱ አዳማ #ማኔጀር የነበረው #መለሰ_ደጀኔን በመኪና አደጋ ከጎናችን አተነዋል! ቀን ሰርግ ውሎ ማታ ወደ አዳማ እየሄደ ከሲኖትራክ ጋር #ተጋጭቶ በደረሰ አደጋ በመሞት አተነዋል። መለሰ ማለት በጣም መልካም ሰው ነበር፣ ይህ የመኪና አደጋ በዚህ ሳምንት 2ተኛዬ ነው እንጠንቀቅ!"

Via Dagi
@tsegabwolde @tikvahethiopia