TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የሰራተኞችድምጽ

" ቢብስብን ነው ወደ ህዝብ ፊትና ሚዲያ የመጣነው " - የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ መምህራን

በሚሰሩበት ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በፋይናንስ ስርዓት መማረራቸውን የገለጹ የአካዳሚክ ጉዳይ አካላት፣ መምህራንና ሌሎችም ችግሮች ካልተፈቱ ስራ ሊያቆሙ እንደሚችሉ አሳስቡ።

ይኸው ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደምም በኦዲት ግኝት እንዲሁም በሌሎችም ችግሮች በስፋት ስሙ መነሳቱ የሚዘነጋ አይደለም።

" ከፍተኛ የሆነና እስካሁን ያልተፈታ ቅሬታ አለን " ያሉት የተቋሙ ሰራተኞች ሰሞኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ምን አሉ ? ምንድነው እንዲህ አማሮ ወደ ህዝብ ያስወጣቸው ጉዳይ ?

➡️ ተቋሙ ይኸው ከ10 ዓመት በላይ ቢሆነም ዛሬም እጅግ ብዙ ነገሮቹና ክፍተቶች አሉበት።

➡️ ተቋሙን ከውድቀት መታደግ ያስፈልጋል።

➡️ ዘንድሮ ጥቅምት ላይ ከላይ አመራሮች አንስቶ ሪፎርም ተደርጎ ነበር። ፋይናንስ ላይ ሪፎርም አልተደረገም።

➡️ ምንም እንኳን በሪፎርሙ ብዙ ለመስራት ቢሞከርም ትልቅ ችግር የነበረው የፋይናንስ ስርዓቱ በዛው ነው የቀጠለው።

➡️የፋይናንስ ስርዓቱ በዛው በመቀጠሉ ከክፍያም ሆነ ከሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ትልቅ ችግር ነው ያለው።

➡️ የፋይናንስ ችግሩ ለመምህራን ፈተና ሆኗል። ይህ ሁኔታ በተማሪዎች ትምህርት ላይም የሚያሳድረው ተጽእኖ ከፍተኛ ነው።

➡️ አካዳሚክ ስታፎች ምንም አይነት የአቅም ማጎልበቻ የሚያገኙበት እድል የላቸውም። በሪሰርች፣ በሶፍትዌር ስልጠና ፣ በመማር ማስተማርም ...ይሁን በሌላ ምንም እየተሰጠ አይደለም። ለዚህ ጉዳዮች እቅድ ወጥቶ ፋይናንስ ላይ ይደውቃል።

➡️ ከመምህራን ክፍያ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግር ነው ያለው።

➡️ በጫና ውስጥ ሆነው የሚሰሩ ሰራተኞች በአግባቡ ከፍያ አያገኙም።

➡️ ከሌላ ዩኒቨርሲቲ ተጋብዘው የሚያስተምሩ መምህራን ለክፍያ ስቃይ ነው። መጀመሪያ ተጋብዞ የመጣ " ድጋሚ ወደዚህ አንመጣም ነው " የሚሉን።

➡️ ከክፍያ ጋር በተያያዘ ተጋባዦች ስለሚቸገሩ አንዳንዴ ኮርሶች ወደ ሌላ ጊዜ ይዞራሉ ይህ ደግሞ በተማሪዎች ላይ ጫና ያሳድራል።

➡️ ብዙ ላብራቶሪ ግቢው ስለሌለው ተማሪዎች የግድ መማር ስላለባቸው ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ይላካሉ በዚህ ወቅት ከክፍያ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ መጓተት አለ። በመምህራን ክፍያም ላይ ችግር አለ። በዚህ ምክንያት ብዙ ትምህርቶች የላብራቶሪ የሚፈልጉ ትምህርቶች ድሮፕ ይደረጋሉ።

➡️ ኢተርንሺፕ የሚወጡ ተማሪዎች ክፍያም ችግር ነው። ተማሪዎች በዚህ በጣም ነው የሚጎዱት።

➡️ ተማሪዎችን ጠብቀው አጅበው የሚወስዱ የሴክዩሪቲ ሰዎችም ክፍያ ቶሎ አይፈጸምም ይጓተታል።

➡️ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን የሚመጡ መምህራን የሚያዙበት መንገድም ጥሩ አይደለም። ህግና ደንብ ተከትሎ ባለመስራት  ምክንያት ይጎዳሉ። እጅግ በጣም የክፍያ መጉላላት አለ።

➡️ የመንግሥት ተቋም መሆኑ እስኪያስጠረጥር ድረስ ነው የፋይናንስ ችግር ያለው።

➡️ በአግባቡ ስራ ስለማይሰራ የበጀት ችግር አለ። መከፈል ያለበት አይከፈልም።

➡️ ተቋሙ ችግር በበዛባት ቁጥር ውጤታማ ተማሪ ፍራት አይችልም። ይህም ባለፉት የመውጫ ፈተናዎች ታይቷል። በዘንድሮው አመት ከአምናው ያነሰ (29%) ተማሪዎችን ነው በመውጫ ፈተና ያሳለፈው።

.... ሌሎችንም አሉ ያሏቸውን ችግሮች በዝርዝር አሳውቀዋል።


የአካዳሚክ ጉዳይ ሰራተኞች፣  መምህራንና ሌሎች ከዚህ ቀደም ሪፎርም ሲደረግ የፋይናንስ ዘርፉ ማታለፉን አመልክተው ባለው ችግር የሚቀጥል ከሆነ ስራ ለመስራት እንደሚቸገሩ አሳስበዋል።

" ካልሆነ የአካዳሚክ ጉዳዩን እነሱ የፋይናንስ ሰዎች ይስሩት አናስረክባቸዋለን " ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

ጉዱዩን በመለከተ ከሰሞኑን የፋይናንስ ስርዓቱ እንዲቀየር ፒቲሽን ፈርመው በ72 ሰዓት መልስ እንዲሰጣቸው እንዳስገቡ  ነገር ግን ምንም ምላሽ ሳይገኝ ሰዓቱ ማለቁን ጠቁመዋል።

" ያለው ችግር በውስጥ እንዲፈታ ጥረናል " ያሉት ሰራተኞቹ " ቢብስን ነው ወደ ህዝብና ሚዲያ የቀረብነው " ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር እና ገንዘብ ሚኒስቴፍ ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ አይተው ማስተካከያ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በዚህ አይነት የትምህርት ስርዓት ውስጥ የሚያልፉ ተማሪዎችን ነገ መውቀስ ስላማይቻል ዛሬ ያሉ ችግሮች ይፈቱ ብለዋል።

(መምህራኑና ሰራተኞቹ በፋይናንስ ሴክተር አሉ ያሏቸውን ችግሮች ዘርዝረው ፈርመው ያስገቡት ፒቲሽን ከላይ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተቋሙን ጉዳይ እስከመጨረሻ ይከታተላል። የተቋሙን አመራሮችና ኃላፊዎችንም ያነጋግራል።

#GambellaUniversity

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የሰራተኞችድምጽ " ቢብስብን ነው ወደ ህዝብ ፊትና ሚዲያ የመጣነው " - የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በሚሰሩበት ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በፋይናንስ ስርዓት መማረራቸውን የገለጹ የአካዳሚክ ጉዳይ አካላት፣ መምህራንና ሌሎችም ችግሮች ካልተፈቱ ስራ ሊያቆሙ እንደሚችሉ አሳስቡ። ይኸው ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደምም በኦዲት ግኝት እንዲሁም በሌሎችም ችግሮች በስፋት ስሙ መነሳቱ የሚዘነጋ አይደለም። " ከፍተኛ የሆነና…
#Update #GambellaUniversity

“ አዲስ ዳይሬክተር ተመድቦ ' ይነሳልን ' ያሉት ሰው #ተነስቷል ” - የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ዩኒቨርሲቲው ሪፎርም ቢያደርግም ከፍተኛ ትኩረት የሚሻው የፋይናንስ ጉዳይ እንዳልተደረገ፣ በዚህም ችግሩ በተለይ ከክፍያና ከስልጠና ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግር እንዳለባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ፒቲሽን አሰባስበው ዩኒቨርሲቲውን ቢጠይቁም ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ገልጸው፤ “ በቢብስብን ነው ወደ ህዝብና ፊትና ሚዲያ የመጣነው ” ብለው የነበረ ሲሆን፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ለቅሬታው ምላሽ ተሰጥቶ እንደሆነ ዩኒቨርሲቲውን ጠይቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ደሪባ ኢቲቻ (ዶ/ር) ምን ማላሽ ሰጡ ?

“ ከዚህ በፊትም በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ቅሬታውን አቅርበው ቅሬታውን አክኖሌጅ አድርገን በአሰራር ለውጥ ለማምጣት ከተወሰኑ መምህራን ጋር ውይይት አድርገናል፡፡

እንደተባለው በዩኒቨርደሲቲ ደረጃ ሪፎርም ተደርጓል፡፡ ያ ማለት ከዚህ በፊት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ካለው አፈጻጸም አንጻር መዘጋት አለበት ተብሎ፤ ከሚዘጋ ደግሞ ሪሮርም መደረግ አለበት ተብሎ ከፍተኛ የአመራር ለውጥ ተደርጓል፡፡

የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል አለበት የሚል እምነት አለን እኛም፡፡ ዩኒቨርሲቲ ያለተማሪዎችና ያለመምህራን የሚሰራው ሥራ የለም፡፡

ስለዚህ መምህራን የጠየቋቸውን ጥያቄዎች ላለመመለስ ሳይሆን ወደ ሚዲያም የወጡበት 'በ72 ሰዓታት ውስጥ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ እርምጃ ካልተወሰደ ከዩኒቨርሲቲ በላይ ላሉት አካላት ሪፖርት እናደርጋለን ' ብለው ነው፡፡ ያንን ደግሞ እኛ መከልክል አንችልም፡፡

ፋይናንስ ውስጥ ያሉ ሠራተኞች አገልግሎት አሰጣጣቸውን በዬጊዜው እንዲያሻሽሉ አድርገናል፡፡

ሪፎርም አልተደረገም ማለት አልችልም ምክንያቱም እኛ ሥራ ስንጀምር የነበረውን ዳይሬክተር (ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ክፍተት አለበት የተባለውን ሰው) አንስተናል ከዛም በፊት፡፡

አሁን እዛው ክፍል የነበረ በቡድን ደረጃ ያለውን በጊዜያዊነት ነው ያስቀመጥነው፡፡ እሱንም ደግሞ ለማንሳት መጀመሪያም ፒቲሽን አቅርበው ነበር፡፡ የመጀመሪያውን ፒቲሽን በሚያቀርቡበት ጊዜ ያለውን አብረን ተነጋግረናል እንደምናስተካክል፡፡

ትልቁ ችግር በቂ ፋይናንስ ባለመኖሩ ሁሉንም ጥያቄ በአንዴ መመለስ አይቻልም፡፡ ብዙ ሪፎርም ያደረግንባቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ 'በ72 ሰዓታት ውስጥ' የሚባለው ግን ፋይናንስ ላይ የሚሰራ ሰው ሰነድ ማስረከብ አለበት፡፡ የኮሚዩኒኬሽን ክፍተት ነበረ ይህንን ሲያስተባብሩ ከነበሩ መምህራንና በከፍተኛ ማኔጅመንት።

የ10 ዓመት እድሜ ታሪክ ያለው ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ እንዳሉትም ላብራቶሪ በትክክል ሰርቪስ አልተደረገም፡፡ ግን መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶት እየተሰራ ነው ያለው አሁን፡፡ ለመምህራን እውነት ለመናገር ትልቅ አክብተሮት አለን፡፡

የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጣቸው ስለሚፈልጉ፣ ስለጓጉ ነው እንጂ፡፡ ይህም መብታቸው ነው፡፡ ለምን ይህንን አደረጉ አንልም፡፡ ግን መሻሻል እንዳለበት ከእነርሱ ጋርም ተነጋገረናል፡፡ ግልጽ ነው፡፡ እነርሱ ፒቲሽን አመጡም አላመጡም ያው ሪፎርሙ ይቀጥላል፡፡

ችግሩ ወዲያው የማይቀረፈው በኢትዮጵያ ደረጃ አዲስ የሠራተኛ ምደባ ተደርጓል፡፡ አዲስ ቅጥር ደግሞ በሲቪል ሰርቪስ አይፈቀድም፡፡ ቅጥር ተፈቅዶ ገና በፕሮሲጀር የሚከድበት ነው፡፡ የሰለጠነ ባለሙያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማግኘት ይከብዳል፡፡ ጠይቀናል፤ ሊሳካ አልቻለም፡፡

' በ72 ሰዓት ምላሽ ስጡን ' የሚለውም ቢያልፍ እኛ ወስነን ስለነበረ አዲስ ዳይሬክተር ተመድቦ ይነሳልን ያሉት ሰው ከዛ ተነስቷል፡፡ ባይሉም እኛ እንደ ከፍተኛ አመራር ይህንን ወስነናል፡፡ መወሰናችንን ደግሞ አስቀድመን ነግረናቸዋል፡፡ አሁን ያለው እውነታ ይሄ ነው፡፡

በቂ በጀት የለም፡፡ ፍላጎትና በጀት ስለማይመጣጠን ቅድሚያ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ የ2015 ዓ/ም ያልተከፈሉ እዳዎች እንደተባለው የ12ኛ፤ የዊኬንድ፤ የኦቨርሎድ ክፍዎች እየተከባለሉ መጥተው 2016 ዓ/ም ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አሳድረዋል፡፡

ለመምህራን ስልጠና አለመስጠት፣ ወርክሾፕ ላይ ላብራቶሪ አለማሟላት የተፈጠረው የበጀት እጥረት በመኖሩ ነው፡፡ እጥረቱ ደግሞ እንዲፈታ ከፌደራል ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተበነጋርን ነው፡፡

በጀትና የምናቅፀደው እቅድ አለመጣጣም ነው፡፡ አንዱ ያነሱት ቅሬታ 'እዛ ያለው ኃላፊ ይነሳልን' የሚል ነው ተነስቶላቸዋል፡፡ ይህንንም ኮሚዩኒኬት አድርገናል፡፡ መምህራንም አሁን ሥራዎችን እየሰሩ ነው፡፡ እንደተባለው ግን በ72 ሰዓት የተባለውን አንደርስታንድ መደራረግ ያስፈልግ ነበር፡፡

ይህንን ፒቲሽን ከተፈራረሙ በኋላ መምህራንን ለማነጋር እየሄድንብት ያለውን ፕሮሲጀር ለማስረዳት ቀጠሮ ይዘንላቸው እኔ ሌላ ስብሰባ ነበረኝ፤ የአስተዳደርና የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲያገኟቸው ወደ አዳራሽ ሲሄዱ አንድም ሰው እዛ አልተገኘም፡፡

ነገር ግን አሁን አዲሱ ሪፎርም ላይ ባለው አመራር 24 ሰዓት በራችን ክፍት ነው፡፡

ከእነርሱ የምንደብቀው ነገር የለም አንድ ላይ ነው የምንሰራው፡፡ ቀጠሮም ይዘንላቸው እዛ ላይ አልተገኙም ” ብለዋል፡፡


በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ዩኒቨርሲቲው የኦዲት ክፍተት እንደነበረበት መረጃዎች መውጣታቸው ይታወሳል፤ ለመሆኑ እርምጃ ተወስዷል ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ፤ የማስተካከያ እርምጃዎች እንደተወሰዱ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

“ ኮመንት የተደረጉት የፌደራሉ ኦዲት መስሪያ ቤት የአመቱን የኦዲት ሪፖርት ይጠይቃል፡፡ ግኝቶቹ ላይ በቂ ማብራሪያ ወይንም ግብረ መልስ ተሰጥቷል ” ነው ያሉት፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia