TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ብሄራዊ ቤተ መንግስት‼️

የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመና የቀድሞው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዳኜ መላኩ አሸኛኘት ተደረገላቸው፡፡

በዝግጅቱ ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበው፣ እርሳቸውም የተጣለባቸውን ኃላፊነት #በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድም ዶክተር ሙላቱ ላበረከቱት ያልተቆጠበ የዲፕሎማሲና የመሪነት ሚና ምስጋና አቅርበዋል፤ አዲስ ወደ ስልጣን የመጡ ተሿሚዎች ለአርዓያነት የሚበቃ ስራ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ሀገራቸውን በማገልገላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይም ባላቸው ልምድ መንግሥትን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በብሔራዊ ቤተ መንግሥት በተዘጋጀው የእውቅና እና ክብር ልዩ ፕሮግራም ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ከፍተኛ ኒሻንና የክብር ዲፕሎማ፤ አቶ ዳኜ መላኩ ደግሞ የምስጋና ወረቀትና ሜዳልያ ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንቶች፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የተፎካካሮሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ኃላፊዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትና የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia