#update አዲስ አበባ⬆️
በህገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶችና ሼዶችን በችግር ውስጥ ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የማስተላለፉ ስራ ቀጥሏል። ዛሬ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 302 የመንግስት ቤቶች ቤት ለሌላቸው በከፋ ድህነት ውስጥ ለሚኖሩ #ነዋሪዋች እና #አካል_ጉዳተኞች ተላልፈው ተሰጥተዋል።
ያልአግባብ ተይዘው የነበሩ እና አዲስ የተሰሩ 16 የጥቃቅን እና አነስተኛ ሼዶችም #ለወጣቶች ተላልፈዋል። በርክክብ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት ም/ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ህገወጥነትን በሁሉም መልኩ ለመዋጋትና ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ላይ አስተዳደሩ ከምንም በላይ ቅድሚያ ሰጥቶ እነደሚሰራ ገልፀው በተመሳሳይ ይህ ተግባር በሁሉም ክፍለከተሞች በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳ‼️
የቀድሞ የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኛ፣ የሕግ ባለሞያ(ጠበቃ)፣ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር፣ የአንድነት ፓርቲ መስራችና ሊቀመንበር እንዲሁም የቀድሞ የፖለቲካ እስረኛ ወ/ት #ብርትኳን_ሚዴቅሳ በመንግሥት ግብዣ ወደ ኢትዮጵያ #ሊመጡ መሆኑ ተሰምቷል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሕግ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ስመጥር ከሆነው ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ደግሞ በሕዝብ አስተዳደር (public Administration) ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የተቀበሉት ወ/ት ብርቱካን ዕረቡ ጥቅምት 28/2011 ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስተው፤ ሐሙስ
ጥቅምት 29/2011 ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ታውቋል። ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙትም መንግሥት ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት መሆኑ ታውቋል።
ምንጭ፦ፂዮን ግርማ(VOA አማርኛው አገልግሎት)

መከላከያ ሰራዊት‼️
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትላንት ባካሄደው 55ኛ መደበኛ ስብሰባ የመከላከያ ሰራዊት ማሻሻያ አዋጅን ጨምሮ በአራት ጉዳዮች ላይ #ውሳኔ አሳለፈ።
ውሳኔ ከተላለፈባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የአገር መከላከያ ሰራዊቱን የሚመለከት ሲሆን የአገር መከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ሰራዊት አዋጅ ቁጥር 809/2006ን ለማሻሻል የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አቅርቧል።
በአገሪቷ የተፈጠረውን ለውጥ ተከትሎ መከላከያ ሰራዊቱ አገራዊ ተልዕኮውን በተሻለ ብቃት እንዲወጣ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የማሻሻያ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የጠቀሰው ምክር ቤቱ የሰራዊቱን የግዳጅ አፈጻጸም ብቃት ለማጠናከርም የህግ ማዕቀፍ አስፈላጊ መሆኑን አመልክቷል።
በመሆኑም ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በኋላ ማሻሻያዎችን በማከል ረቂቅ አዋጁ እንዲጸድቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኳል።
ምክር ቤቱ በሌላ በኩል የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የተዘጋጀውን ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ደንቡ ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል።
ምክር ቤቱ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት እንዲሁም የፌዴራል ዓቃቢያን ህግ መተዳደሪያ ረቂቅ ደንብ ተግባርና ሃላፊነትን ለመሰወን በተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ላይም ተወያይቶ ደንቡ ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል።
የኢትዮጵያ ልማት ምርምር ኢንስቲትዩትና የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል በቅርቡ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ተብሎ መቋቋሙ ይታወሳል።
የኢንስቲትዩቱን ስልጣን፣ ተግባርና አደረጃጀት ለመወሰን የፕላንና ልማት ኮሚሽን ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ባቀረበው መሰረት ነው ምክር ቤቱ ዛሬ ውሳኔ ያሳለፈው።
በተመሳሳይ በስራ ላይ ያለው የፌዴራል ዓቃቢያን ህግ መተዳደሪያ ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ ስራ ላይ ከዋለ ረጅም ዓመታት ያሳለፈ በመሆኑ በአሰራር የታዩ ክፍተቶችና ሎላዊነት ያስከተላቸው ለውጦችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ደንቡን መለወጥ እንዳስፈለገ ተመልክቷል።
ምንጭ፡ ኢዜአ

#Update የአማራ ክልል ምክር ቤት አዳዲስ የካቢኔ አባላትን #ሹመት አፅድቋል።
ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ ለክልሉ የተለያዩ ቢሮዎች በእጩነት የቀረቡ ሃላፊዎችን ሹመት አጽድቋል።
በዚህም መሰረት:-
-አቶ ላቀ አያሌው – ምክትል ርዕሰ መስተዳድር
-አቶ መላኩ አለበል – በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደረጃ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ
-ዶክተር ቦሰና ተገኘ – የግብርና ቢሮ ሃላፊ
-አቶ ሻምበል ከበደ – የቴክኒክና ሙያ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሃላፊ –
-ወይዘሮ ብዙአየሁ ቢያዝን – የገቢዎች ቢሮ ሀላፊ
-አቶ ፍርዴ ቸሩ – ጠቅላይ አቃቤ ህግ
-ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ – የሰላም ግንባታና የህዝብ ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ
-አቶ ንጉሱ ጥላሁን – በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደረጃ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ
-ዶክተር ሙሉነሽ አበበ – የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ
-ወይዘሮ አስናቁ ድረስ – የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ቢሮ ሀላፊ
ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahthiopia

ብሄራዊ ቤተ መንግስት‼️
የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመና የቀድሞው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዳኜ መላኩ አሸኛኘት ተደረገላቸው፡፡
በዝግጅቱ ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበው፣ እርሳቸውም የተጣለባቸውን ኃላፊነት #በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድም ዶክተር ሙላቱ ላበረከቱት ያልተቆጠበ የዲፕሎማሲና የመሪነት ሚና ምስጋና አቅርበዋል፤ አዲስ ወደ ስልጣን የመጡ ተሿሚዎች ለአርዓያነት የሚበቃ ስራ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ሀገራቸውን በማገልገላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይም ባላቸው ልምድ መንግሥትን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በብሔራዊ ቤተ መንግሥት በተዘጋጀው የእውቅና እና ክብር ልዩ ፕሮግራም ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ከፍተኛ ኒሻንና የክብር ዲፕሎማ፤ አቶ ዳኜ መላኩ ደግሞ የምስጋና ወረቀትና ሜዳልያ ተበርክቶላቸዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንቶች፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የተፎካካሮሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ኃላፊዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትና የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ምንጭ፦ ena

ጫት ላይ የቀረበው ረቂቅ መግለጫ‼️
የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ #ልዑል_ዮሐንስ ለአማራ ክልል ምክር ቤት #በጫት ጉዳይ ላይ ያለውን ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡
አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ጫት በሃገራችን የጤናና ማህበራዊ #ቀውሶች እያስከተለ ነው፡፡
🔹ጫት ለተለያዩ በሽታዎች ይዳርጋል
🔹የዜጎችን ምርታማነትም ይቀንሳል
🔹ማህበራዊ ትስስርን ያስተጓጉላል
🔹ቤተሰባዊ መስተጋብርን ያዛባል
🔹ለሙስናና ብልሹ አሰራር መስፈንም የራሱ ድርሻ አለው፡፡
እናም፦
🔹የጫት ምርት ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ወደ ሌላ ምርት እንዲሰማሩ ቢደረግ
🔹በጫት ንግድ የተሰማሩ ወገኖችን በመምከር ወደ ሌላ ንግድ እንዲሰማሩ በጎ ተጽእኖ ቢደረግ፤ ማበረታቻም ባይሰጣቸው የሚል መነሻ አቅርበዋል፡፡
የተነሱ ሃሳቦች፦
🔹የጫትን ማህበራዊና የጤና መሰናክሎችን ለማስቀረት ጠንከር ያለ አዋጅ በማዘጋጀት ለተግባራዊነቱ መስራት አለብን፡፡
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው -የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የጫት ጉዳይ አጀንዳ ያደረግነው ወጥ አቋም( አመለካከት) እንዲኖረን ነው፡፡
- ጫት ጉጂ በመሆኑ አምራቾችን እና ተጠቃሚዎች ጋር እንወያያለን ፡፡ በአንድ ጊዜ ማቆም አይቻልም፡፡ #እንዳይስፋፋ ይሰራል፤ ጫት የሚያመርቱ አርሶአደሮች ጫት የተሻለ ምርት የሚያስገኝ ምርት ላይ መሰማራት አለባቸው፡፡ ወደ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያመርቱ
#ማበረታታት አለበት፡፡
- ህበረተሰቡ ጋር ከተግባባን በኋላ #ህግ ወደማምጣቱ እንሸጋገራለን፡፡ ነገር ግን ጫት ትምህርት ቤቶች አከባቢ እንዳይሸጡ በአፋጣኝ #መወሰን ይቻላል፡፡
- በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከለከለ እፅዋት እየሆነ ነው፡፡ ጫትን የሚኮንነው ማህበረሰብ እየበዛ ስለሆነ ሌላ አማራጭ መፈለግ ፣ ማሳየት እና መደገፍ ያስፈልጋል፡፡
- ጫት የሚሸጥባቸው ቦታዎችን #የታወቁ ብቻ ሊሆኑ ይገባል፡፡
- ህብረተሰቡ ይህን አደገኛ ሁኔታ መከላከል አለብን በማለቱ ምክር ቤቱ መወሰኑ ተገቢ ነው፡፡
- ምክር ቤቱ በጫት ጉዳይ ተነሱ ሐሳቦች እንዲተገበሩ ምክረ ሀሳብ ወስኗል፡፡

ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር⬆️ከረጅም አመት በኋላ በኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ቴዎድሮስ ካሳሁን የተሳካ ሙዚቃ ዝግጅቱን አቅርቧል። ዝግጅቱን 20 ሺ ሰው ገደማ ታድሞታል። ዝግጅቱ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ መጠናቀቁም ተሰምቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር ኤልያስ ገብሩ‼️
በቅርቡ ኤቶዮጵ የተሰኘ መፅሐፍ ያስነበበን ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ በNuha International Blogging ውድድር ላይ ብቸኛው የኢትዮጵያ ወኪል ሆኖ ቀርቧል። ከዓለም የተለያዩ ሃገራት የተወጣጡ ፀሐፊዎች በሚሳተፉበት በዚህ ውድድር ላይ ጠ/ሚንስትራችን ዶ/ር አብይ አህመድም Motto አድርገው በተጠቀሟት "Break down the wall, Build a Bridge" በሰየመው ፅሑፉ ነው ከእጩ ተወዳዳሪዎች ተርታ የተሰለፈው። ውድድሩ የሚዳኙት ሰዎች የፅሑፉን ጥልቀትና ውበት ከማየት ባሻገር በዌብሳይቱ ላይ አንባቢዎች የሚሰጡትን አስተያየት ከግምት ውስጥ ያስገባሉ። እናም የሀገሬ ሰው ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን ፅሑፉ ላይ አስተያየትህን አስቀምጥለት።
https://nuhafoundation.org/home/blog/bloggingentries/2018/adult/breakdown-the-wall-build-a-bridge/#.W9soFWhKhhE