TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም‼️

"በአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም በጎፈንድሚ የተሰበሰበውን 73 ሺህ 9 መቶ ዶላር ወደ አካውንት #ለማስገባት ፈቃደኛ አይደለሁም። ምክኒያቱም በኮሚቴው እምነት የለኝም።" አርቲስት #ቴዎድሮስ_ተሾመ

"በአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም በጎ ፈንድሚም ሆነ በማናቸውም መልኩ የተሰበሰበው ገንዘብ በስሙ ወደተከፈተው የባንክ አካውንት መግባት አለበት።" የአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም የህክምና ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ

ይህ እሰጣ ገባ የተካሄደው ትላንት በአፍሮዳይት ሆቴል የአርቲስት ፍቃዱ ተ/ ማርያም የህክምና ገቢ ለማሰባሰብ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው ኮሚቴ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

ኮሚቴው ለሁለት የተከፈለበትን ጉዳይ አንስቶ ባቀረበው ሪፖርት ላይ እንደገለጹት በአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም የተሰበሰበው ገንዘብ ጉዳይን አስመልክቶ የተጓዘባቸውን ርቀቶች ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ከአርቲስት ፍቃዱ የህክምና ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ አማካኝነት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው አካውንት ላይ በአሁኑ ወቅት 1,200,895.69 (አንድ ሚልዮን ሁለት መቶ ሺህ ስምንት መቶ ከስልሳ ዘጠኝ ሳንቲም) ብር በአካውንቱ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ቀሪውን በጎፈንድሚ የተሰበሰበውን 73,900 ዶላር ወደ አካውንት እንዲያስገባ ለቴድሮስ ተሾመ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ለመቀበል እንዳልቻለና በኮሚቴው አባላት ላይ እምነት #የለኝም በማለቱ ልዩነት እንደተፈጠረ ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ጥቅምት 23 ቀን 2011 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል ተሰብስቦ የወሰነውን ቃለ ጉባኤ በንባብ አስደምጧል። ይህንን አስመልክቶም ምላሽ የሰጠው አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ "ህዝብ ገንዘቡን የሰጠኝ የእኔን ስም አይቶ ነው። በአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም የተሰበሰበውን ገንዘብ በኮሚቴው የአስተዳደር ችግር ምክንያት እምነት ስለሌለኝ ገንዘቡን ወደ ተባለው አካውንት ገንዘቡን አላስገባሁም። ወደፊትም በዚህ ገንዘብ ላይ ሙሉ ሀላፊነቱን የምወስደውም ሆነ እየወስድኩ ያለሁት እኔ ነኝ። ጠበቃዬም ገንዘቡን ገቢ እንዳላደርግ አማክሮኛል። ለዚህም ለህሊናዬም ሆነ ለፈጣሪ ታማኝ በመሆን ገንዘቡን ህጋዊ ወራሽ ይሆናሉ ብዬ ለማስባቸው ቤተሰቦቹ ጥቅምና ለሀውልቱ ማሰሪያ እንዲሆን እየተንቀሳቀስን ነው" ብሏል።

ሌሎች የኮሚቴ አባላት ደግሞ በአጠቃላይ የተሰበሰበውን ገንዘብ ወደ አንድ ቋት እንዲገባና ፍርድ ቤት የሚያሳውቃቸውን ህጋዊ ወራሾች መጠበቅ አለበት የሚል አቋም ይዘዋል።

ለአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም ከህዝብ የተሰበሰበው ገንዘብ መጨረሻ ምን ይሆን? አሁንም ምላሽ የለውም። በአርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ስም በተሰበሰበው ገንዘብ ላይ የተነሳው ንትርክ ከዚህ በኋም የጤና እክል የሚያገጥማቸው የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ህዝብ በአግባቡ እንዳያግዝ የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳያሳርፍ ስጋት አጭሯል።

ምንጭ፦ ጴጥሮስ አሸናፊ
@tsegabwolde @tikvahethiopia