TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቦንጋ እየተረጋጋች ነው‼️

በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ  ከቡና መገኛነት ጋር ተያይዞ በድረ-ገጽ በተላለፈ መረጃ  የተፈጠረው ችግር በመቃለሉ ወደ #መረጋጋት መመለሱን የዞኑ ባህል፣ ቱሪዝምና መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ አስታወቀ፡፡

የመምሪያው ኃላፊ አቶ #አስረስ_አዳሮ ለኢዜአ እንደገለጹት በተፈጠረው ችግር ምክንያት በከተማዋ ላለፉት አምስት ቀናት  ትራስንፖርትና ማህበራዊ አገልግሎቶች ተቋርጠው ነበር፡፡

ይህም የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እንደሚጎዳ የዞኑ አስተዳደር ከወጣቱንና ከሌላውም የህብረተስብ ክፍል ጋር ተወያይቶ  መግባባት ላይ በመድረሱ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከተማዋ ወደ መረጋጋት መመለሷን አስረድተዋል፡፡

የትራንስፖርት አገልግሎትም ጀምሯል፡፡

የቡና መገኛነት ጉዳይ መነሻ ሆኖ ለዓመታት የቆየው የቡና ሙዚየም ስራ አለመጀመር ህዝቡን እንዳስቆጣውም ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለስልጣን የተሰጠው ይቅርታና የቡና ሙዚየም ግንባታ ስራው እንደሚጀምር የሰጠው  መግለጫ ህዝቡን እንዳረጋጋው ተናግረዋል፡፡

ከህዝቡ የተነሱ  ጥያቄዎች ከክልልና ከፌደራል መንግስት ጋር በመነጋገር ምላሽ እንዲያገኙ ለመስራት መስማማት ላይ በመድረሳቸው  የግልና የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደቀድሞ ስራቸው መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

አካባቢውን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስና መንገዱን ለማስከፈት በተደረገው ጥረት የወጣቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ድርሻ ከፍተኛ እንደነበረ አስታውቀዋል፡፡

ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አቶ ገብረሚካኤል ወልደማርያም  በሰጡት አስተያየት በታሪክ የሚታወቀው የከፋ ቡና መገኛነት በተለያዩ ተቋማት የተሳሳተ መረጃ በመሰጠቱ ህዝቡን ማስቆጣቱን ተናግረዋል፡፡

ህዝቡ ያነሳቸውን ጥያቄዎች የዞኑ አስተዳደር ኃላፊነት ወስዶ እንደሚያስፈጽም ሃላፊነት በመውሰዱ ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት ወደ ነበረበት መመለሱን ገልጸዋል፡፡

መንግስት የሀዝቡን ጥያቄ በፍጥነት መመለስ እንዳለበትና ጉዳዩ ዳግም ጥያቄ የሚያስነሳ መሆን እንደሌለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ሌላኛው የከተማው ነዋሪ አቶ ረጋሳ ጸጋዬ በበኩላቸው ባለፉት ቀናት የተካሄደው ሰልፍ ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መጠናቀቁን ገልጸው ጥያቄው ተገቢነት ያለው በመሆኑ በመንግስት በኩል ምላሽ ያገኛል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡

“ቡናና ከፋ ከስያሜው ጀምሮ ጥብቅ ቁርኝት ያለው እና ታሪካዊ የሰነድ ማስረጃዎች የሚያረጋግጡ ሆኖ ሳለ የተላለፈው መረጃ መዛባት ለችግሩ ምንጭ ሆኗል “ያሉት ደግሞ አቶ ብርሃኑ  ገብሬ ናቸው፡፡

የዞኑ አስተዳደር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ጉዳዩ የመጨረሻ እልባት እንዲያገኝ ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

 ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia