TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው 4ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ #ሹመቶችን አፀደቀ።

በዚህም መሰረት፦

1.ዶክተር ግርማ አመንቴ፦ በምክትል ርእሰ መስተዳደር ማእረግ የግብርና ዘርፍ ሀላፊ

2. አቶ አህመድ ቱሳ፦ በምክትል ርእሰ መስተዳደር ማእረግ የኢኮኖሚ ዘርፍ ሀላፊ

3. ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን፦ በምክትል ርእሰ መስተዳደር ማእረግ የማህበራዊ ዘርፍ ሀላፊ

4. አቶ አሰግድ ጌታቸው፦ የርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ሀላፊ

5. አቶ ዳባ ደበሌ፦ የግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ

6. ዶክተር ኢንጂነር ፍቃዱ ፉፋ፦ የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ሀላፊ

7. አቶ ሙላቱ ጽጌ፦ የንግድ ቢሮ ሀላፊ

8. ዶክተር ሚልኬሳ ሚደጋ፦ የመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ቢሮ ሀላፊ

9. አቶ ገረመው ሁሉቃ፦ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ

10. ወይዘሮ ሙና አህመድ፦ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ሀላፊ

11. አቶ አድማሱ ዳምጠው፦
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ

12. አቶ ጥላሁን ወርቁ፦ የኢንተርፕራይዝና ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ

13. ወይዘሮ ፈቲያ መሃመድ፦ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ

14. አቶ ኤባ ገርባ፦ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ

15. ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ፦ የገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

16. አቶ ተሾመ ግርማ ፦ ጠቅላይ አቃቤ ህግ

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ የተለያዩ #ሹመቶችን ሰጠ።

በዚህም መሰረት፦

1. አቶ ምግባሩ ከበደ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/አዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ሃላፊ፣

2. አቶ እዘዝ ዋሴ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ እና

3. አቶ ደሴ ጥላሁን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ሆነው መሾማቸውን አስታውቋል።

ፓርቲው ቀደም ሲል በገጠርና በከተማ አደረጃጀትና ፖለቲካ ዘርፍ ሲገለገልበት የቆየውን አደረጃጀት በማጠፍ ወደ ሁለት ዘርፍ በመጠቅለል የአደረጃጀት ዘርፍ እንዲሁም የፖለቲካ ዘርፍ በሚል አዋቅሮ ሹመቱን መስጠቱንም ነው ያመለከተው።

ምንጭ፦ አ.ብ.መ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር‼️

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አራተኛ አስቸኳይ ጉባኤ አዳዲስ #ሹመቶችን አጸደቀ፡፡

ከተሿሚዎች መካከል የምክር ቤቱን አፈ-ጉባኤ በአዲስ የተኩ ይገኙበታል፡፡

ምክር ቤቱ አቶ ሱልጣን አልይን የድሬዳዋ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ ወይዘሮ ጫልቱ ሁሴን ደግሞ የድሬዳዋ አስተዳደር ዋና ኦዲተር ጽህፈት ቤት ዋና ኦዲተር በማድረግ በሙሉ ድምጽ መርጧል፡፡

ከምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤነት በተነሱት አቶ አብዱሰላም መሐመድ ምትክ አቶ ከድር ጁሃር ተመርጠዋል፡፡

ተሿሚዎቹ ህግና ስርዓትን አክብረው የህዝቡን የልማት ፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ትርጉም ባለው መንገድ ለመመለስና ሀገራዊ ለውጡን ከዳር ለማድረስ እንደሚተጉ ቃል ገብተዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳዲስ ሹመቶች‼️

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከጥር 9 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለተለያዩ የመንግስት ሀላፊነት ቦታዎች #ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት መረጃ መሰረት፦

•አቶ ፍራኦል ተፈራ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣

•አቶ ማተቤ አዲስ የኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣

•አቶ እዮብ አወቀ የስደተኞና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣

•ዶ/ር መብራህቱ ገ/ማሪያም የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣

•አቶ መስፍን ነገዎ የኮንስትራክሽን ስራዎ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣

•አቶ እስማኤል አሊሴሮ በሚንስትር ዴኤታ ማእረግ የሰላም ሚንስትር አማካሪ፣

አቶ ታምሩ ግንበቶ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾመዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ከፍተኛ #ሹመቶችን ያጸድቃል፡፡ በጠቅላይ ሚንስትሩ አቅራቢነት ምክር ቤቱ የሚያጸድቃቸው ሹመቶች የሚንስትር ሹመቶች መሆናቸውን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል፡፡ ለየትኛዎቹ መስሪያ ቤቶች ሹም እንደሚሾምላቸው ግን አልታወቀም፡፡

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia