TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AmharaRegion

የአማራ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ 160 እጩ የወረዳ ፍ/ቤት ዳኞችን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

#AMC

@tikvahethiopia
#AmharaRegion

በጦርነት ምክንያት በአማራ ክልል ፤ ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ባለው እጅግ የከፋ ችግር በርካታ ህፃት እና እናቶች ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፤ ይሄ በተደጋጋሚ ተገልጿል።

በችግር ላይ ላሉት ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ ቢሆንም ካለው የከፋ ሁኔታ አንፃር ምንም ነው።

የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለሴቶች እና ሕጻናት 3 ሚሊዮን ብር የሚገመት የአይነት እና ለ300 እናቶች ደግሞ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አሚኮ ዘግቧል።

እንዲሁም በክልሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እስካሁን 200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ቢያደርጉም ከተከሰተው ችግር ስፋት ጋር የሚጣጣም ሆኖ አልተገኘም።

ችግሩንም መፍታት አልተቻለም።

መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ፣ ባለሃብቶች በችግር ላይ ለወደቁ ወገኖች አሁንም ድጋፋቸው አጠናክሮ እንዲቀጥሉ እና ሕጻናትን እና እናቶችን መታደግ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።

ፎቶ ፦ አሚኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AmharaRegion በጦርነት ምክንያት በአማራ ክልል ፤ ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ባለው እጅግ የከፋ ችግር በርካታ ህፃት እና እናቶች ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፤ ይሄ በተደጋጋሚ ተገልጿል። በችግር ላይ ላሉት ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ ቢሆንም ካለው የከፋ ሁኔታ አንፃር ምንም ነው። የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለሴቶች እና ሕጻናት 3 ሚሊዮን ብር የሚገመት የአይነት እና…
#AmharaRegion

በአማራ ክልል ውስጥ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት " የዕለት ምግብ ያስፈልጋቸዋል " ተብለው ከተለዩት ዜጎች መካከል ፦

👉 50 በመቶ ሴቶች ናቸው።

👉 400 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ሕጻናት ናቸው።

በአማራ ክልል፤ ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ብቻ ፦

👉 በ3 መጠለያ ጣብያዎች የተፈናቃዩ ቁጥር ከ65 ሺ 700 በላይ ደርሷል። ከዚህ ውስጥ:-

• 18 ሺህ የሚያጠቡ ናቸው።

• ከ1 ሺህ 100 በላይ አረጋውያን ናቸው።

• 590 የሚሆኑት አካል ጉዳተኞች ናቸው።

ምንጭ ፦ የአማራ ክልል ሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ / የዋግኽምራ ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ / አሚኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AmharaRegion የጠቅላላ ሀኪም የቋሚ ቅጥር ፦ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ ስር ባሉ ጤና ተቋማት ጠቅላላ ሀኪሞችን መድቦ ማሰራት ይፈልጋል። 👉 የስራ መደቡ መጠሪያ - ጠቅላላ ሀኪም 👉 ደመወዝ - 9,056 ብር (ዘጠኝ ሺ ሃምሳ ስድስት ብር) 👉 ብዛት - 631 (#ስድስት_መቶ_ሰላሳ_አንድ) 👉 የስራ ቦታ - በክልሉ ባሉ የጤና ተቋማት ክፍት ቦታዎች 👉 ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት - በጠቅላላ…
#AmharaRegion

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ከዚህ ቀደም ለ631 ጠቅላላ ሃኪሞች የስራ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል።

ዛሬ ይፋ በሆነው መረጃ ቢሮው ለ84 ሆስፒታሎች 409 ጠቅላላ ሃኪሞችን መቅጠሩ ታውቋል።

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጤና ሚኒስቴር እና የክልሉ ጤና ቢሮ (በማችንግ ፈንድ) በመተባበር ለ631 ጠቅላላ ሃኪሞች የቅጥር ማስታወቂያ ቢወጣም ቢሮው አወዳድሮ ሊቀጥር ያቻለው 409 ጠቅላላ ሀኪሞችን ነው።

የአብክመ ጤና ቢሮ የሰዉ ሃብትና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳኛቸዉ ደሬ ፤ " የማችንግ ፈንድ ለ631 ጠቅላላ ሃኪሞች በጀት ቢለቅም በገባያ ላይ 409 ጠቅላላ ሃኪሞች ብቻ ነው የተገኙት " ሲሉ ገልፀዋል

የክልሉ ጤና ቢሮ በቀጣይ ጊዜ ለቀሩት 222 ጠቅላላ ሃኪሞች የቅጥር ማስታወቂያ እንደሚወጣ አሳውቋል።

ያልተቀጠሩ በተለያየ ሙያ ያሉ የጤና ዘርፍ ባለሙያዎች በነበረዉ ሃገራዊ ችግር ምክንያት ቢሮዉ " በሙሉ በጀቱን ለህልዉና ዘመቻ በማዋሉ " እደሆነ ገልፆ በቀጣይ ጊዜያት ከጤና ሚንስቴር እና ከአጋር አካላት ጋር በመነጋገር የቅጥር ማስታወቂያ እንደሚያወጣ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሰሜን ሸዋ ዞን ፤ በኤፍራታና ግድም ወረዳ እና በቀወት ወረዳ እንዲሁም በኦሮም ብሄረሰብ ዞን አዋሳኝ አካባቢ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ተዘግቶ የነበረው የፌድራል መንገድ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ክፍት ሆኖ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ አሳውቋል። መንገዱ ወደ አገልግሎት የተመለሰው በሰሜን ሸዋ ዞን አመራሮችና በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አመራሮች ፣ በፀጥታ አካላቶች እንዲሁም በሀገር ሽማግሌዎች በተሰሩ…
#AmharaRegion

በቅርቡ በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች አስተዳደር አጎራባች አካባቢዎች የፀጥታ ችግር ተፈጥሮ እንደነበር አይዘነጋም።

ይህንን ተከትሎ ዳግም ግጭት እንዳይፈጠር እና ሰላምን ለማጠናከር በአጣዬ ከተማ ትላንት የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

መድረኩ ሰላምን ለማጠናከር የሚጠቅሙ አንኳር ሀሳቦች የተነሱበት መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን በዋናነት ለግጭቱ መንስኤ የሆኑ አካላት በሕግ እንዲዳኙና ማኅበረሰቡም አሳልፎ እንዲሰጥ መግባባት ላይ ተደርሷል።

የሃይማኖት አባቶች ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት የሕዝቦች ትስስር ዋልታ ነው፤ የሰው ልጅ ሁሉ ደሙ አንድ ነው፤ በሰውነቱ ሁሉም ከአንድ የተገኘ ነውም ብለዋል።

ምክክሩ የተጠናቀቀው ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ሲሆን የአቋም መግለጫው በዚህ ተያይዟል ፦ https://telegra.ph/Amhara-Region-04-27

ምንጭ፦ የአማራ ክልል የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ጉዳዮች ቢሮ

@tikvahethiopia
#AmharaRegion #እንድታውቁት

ከዛሬ ግንቦት 9 ጀምሮ በአማራ ክልል የጦር መሳሪያ ምዝገባ ይካሄዳል።

ይኸው የጦር መሳሪያ ምዝገባ ለአራት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በክልሉ ከዚህ በፊት ያልተመዘገበ መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በአካባቢው ባሉ የምዝገባ ማዕከላት መሳሪያውን ማስመዝገብ እንዳለበት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምዝገባው የአማራን ህዝብ ደህንነት ለማስጠበቅ አጋዥ ኃይል ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ አመልክቷል።

@tikvahethiopia
#AmharaRegion

የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ፤ በክልሉ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቋል።

ቢሮው ዛሬ ግንቦት 15/2014 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከሰሞኑን መንግሥት ያካሄደውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ መሆኑን አመልክቷል።

የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳሳለኝ ጣሰው የአማራ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ ሥራውን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ከ4 ሺ በላይ ሰዎች መካከል 40 የሚሆኑት ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለው ፍርድ የተላለፈባቸው መሆናቸው የተጠቀሰ ሲሆን 210 የሚሆኑት ደግሞ በነፍስ ግድያ የተጠረጠሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አቶ ዳሳለኝ ጣሰው በአሁኑ ወቅት መንግሥት ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ከሚደረግ ሥራ ውጭ ክልሉ አስተማማኝ ሰላም ላይ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

" ትክክለኛውን የፋኖ ስም የማይወክሉ፣ በፋኖ ስም ተደራጅተው በሕዝብ ላይ የተለያዩ ሕገ ወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ ቡድኖችን መንግሥት አይታገስም " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
#AmharaRegion

በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና በ10 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚገኙ 31 ማዕከላት ይሰጣል፡፡

ፈተናው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ እየሠራ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በክልሉ ሁሉም የመፈተኛ ተቋማት እና ማዕከላት በቂ የጸጥታ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ምክትል ኮሚሽነር እንየው ዘውዴ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ወረዳን ማዕከል አድርጎ ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተቀመጠው ጊዜ ለማድረስ በቂ የትራንስፖርት አገልግሎት ዝግጅት ማድረጉን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ውቤ አጥናፉ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች የወረዳ ትራንስፖርት ቢሮ በሚያወጣው መርሃ ግብር መሰረት በጊዜ እየተገኙ እንዲስተናገዱ ጠይቀዋል፡፡

ሀገራዊ ግዴታቸውን በአግባቡና በሀላፊነት የማይወጡ የትራንስፖርት ማህበራትና ባለሀብቶች በትራንስፖርት መመሪያ እና በሕግ ይጠየቃሉ ብለዋል፡፡

ተማሪዎች በሚጓጓዙባቸው ቀናት መደበኛ ትራንስፖርት ስለማይኖር ሕዝቡ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እንዲተባበር ጥሪ አድርገዋል፡፡

ምንጭ፦ አሚኮ

More : @tikvahuniversity
#AmharaRegion

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተማሪዎች በራሳቸው አቅም ብቻ ተማምነው ወደፈተና ማዕከላት እንዲመጡ ጠየቀ።

በራሱ በመተማመን መፈተን ያልፈለገ ተማሪ ወደ ማእከላት ባይመጣ ይመረጣል ብሏል ቢሮው።

ከሰሞኑ በጥቂት ማእከላት የተፈጠረው ክስተት የአማራ ክልልን ህዝብና ተማሪዎችን የማይመጥን ድርጊት ነው ሲልም ገልጿል።

በቀጣይ ሳምንት ፈተና የሚወስዱት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከተጠናቀቀው የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ሂደት በመማር ፍጹም ለአሉባልታና ለወሬ ሳይበገሩ ፈተናቸውን በሰላም እንዲወስዱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጥሪ አቅርቧል።

ለቀጣዩ ፈተና ከወረዳ ጀምሮ ያሉ አካላት ሰፊ ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገልጿል።

የአማራ ክልል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም በበኩሉ ፤ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ በጥቂት ማእከላት የተፈጠረው ችግር የወላጆችን ፣የመምህራንን እና አጠቃላይ የማህበረሰቡን ልፋት መና ያስቀረ ፤ በቀጣይ በፍጹም መደገም የሌለበት ስህተት ነው ብሏል።

ተማሪዎች ዩንቨርስቲ የሚመጡት ፈተና ለመፈተን እንጂ ለሌላ ተልእኮ አለመሆኑን በመገንዘብ የተቀመጡትን ህግና ደንቦች አክብረው እንዲፈተኑ ጠይቋል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የፈተና መርሐግብር ከጥቅምት 08 እስከ 11/ 2015 ዓ. ም የሚሰጥ ሲሆን በአማራ ክልል ብቻ ከ119,000 በላይ ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ።

በዚሁ አጋጣሚ ፦

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ከባለፈው የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ጋር በተያያዘ በተለያዩ ተቋማት የተፈተኑ ተማሪዎች አስተያየት፣ የወላጆችን መልዕክት ስንቀበል ውለናል አሁንም እየተቀበለን ሲሆን ተማሪዎች መረጃ ስትልኩ " ሰማሁ " ፣ " እየተባለ ነው "  እያላችሁ ሳይሆን በትክክል የምታውቁትን እና ያረጋገጣችሁትን ብቻ እንድትልኩ እንጠይቃለን።

@tikvahethiopia
#AmharaRegion

ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ከተማ የሚወስደው መንገድ ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ ደጀን ከተማ ላይ ተዘግቷል።

በዚህ ምክንያት የሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጣል።

በዛሬው ዕለት ደግሞ የንግድ እንቅስቃሴ መቆሙ እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መዘጋታቸው ተገልጿል።

ጉዳዩን በተመለከተ የከተማው የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ዘውዱ ተከታዩን ቃል ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ ሰጥተዋል ፦

" ደጀን ከተማ የሚያስገባው መንገድ የተዘጋው ፤ የክልሉ ልዩ ኃይል መበተንን በሚቃወሙ ነዋሪዎች ነው።

ወጣቶች ተቃውሟቸውን ማሰማት የጀመሩት ከትላንት አርብ ከሰዓት ጀምሮ ነው።

ከቀኑ አስር ሰዓት ገደማ ላይ ተቃውሞ የሚያሰሙ ነዋሪዎች፤ ወደ ከተማዋ የሚያስገባው መንገድ ላይ ድንጋይ በማስቀመጥ የተሽከርካሪዎች ፍሰት እንዲቆም አድርገዋል።

በትላንቱ ተቃውሞ የፌደራል ፖሊስ ንብረት የሆነ አንድ ‘ፒክ አፕ’ ተሸከርካሪ ተቃጥሏል የሚል መረጃ እደርሶናል።

ድርጊቱን የፈጸመው አካል ማንነት ግን ገና አልተረጋገጠም። የትኛው ነው ያቃጠለው? ‘ወጣቱ ነው ወይስ ለመንግስትም ለህዝብም አልመች ያለ ጠላት ነው?’ የሚለውን ነገር አልደረስንበትም።

የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ተሰሚነት አላቸው በተባሉ ወጣቶች አማካኝነት፤  የነዋሪዎችን ተቃውሞ ለማረጋጋት ጥረት እየተደረገ ነው።

የሚደረገው ንግግር፤ በከተማይቱ በተነሳው ተቃውሞ ሰዎች እንዳይጎዱ የማድረግ ዓላማ ያለው ነው። "

የከተማዋ ኮሚዩኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ ሞኙ ሆዴ አሳየ በበኩላቸው ተከታዩን ብለዋል ፦

" ከደጀን ከተማ መግቢያ በተጨማሪ በከተማው የሚያልፈው መንገድ ተዘግቷል።

በደጀን በየሳምንቱ ይካሄድ የነበረው የቅዳሜ ገበያ በዛሬው ዕለት ሳይከናወን ቀርቷል።

ገበያ የመጣውም ህዝብ እንዲመለስ ተደርጓል። ሱቅም ተዘግቷል። የሰው እንቅስቃሴ አለ፤ ወጣቱ ላይ ታች ይላል። የንግድ እንቅስቃሴ ግን የለም።

ቅዳሜ በርካታ ህዝብ ገበያውን የሚያሳልጥበት ቀን ነው። ግን ዛሬ አንድም የለም። "

በደጀን ከትላንት አንስቶ በተነሳው ተቃውሞ ምክንያት ዛሬ ቅዳሜ ወደ ከተማዋ የመጣ ሀገር አቋራጭ ተሽከርካሪ አለመኖሩ ተነግሯል።

ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችም መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት ዛሩ ወደ ባህር ዳር አውቶብሶችን አለማሰማራታቸውን አስታውቀዋል።

Credit : Ethiopia Insider

@tikvahethiopia