TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀዋሳ‼️

የአስተዳደሩ የፀጥታ አማካሪ ም/ቤት የከተማዋን ጸጥታና #ሰላም_ለማረጋገጥ ያቀረበውን ዕቅድ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያመለከተ ውይይት አካሄደ፡፡

በዚህ ከተማ አቀፍ በሆነ የፀጥታ እና የሠላም የጋራ የምክክር መድረክ ላይ የሀዋሳ ከተማ ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ዕቅድ በፀጥታ ም/ቤቱ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በቀረበው እቅድ ላይ ከመድረክ ማመላከት እንደተቻለው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የከተማዋን ገጽታና ሁለተናዊ ሰላም የማይገልጹ አለመረጋጋቶች እና ሁከቶች መስተዋላቸው ይገኝበታል፡፡

ለዚህ አለመረጋጋት በዋናነት የጎዳና ላይ ንግድን መሰረት ባደረገ መልኩ እና #የጎዳና_ልጆችን በመጠቀም የሚፈጠሩ ክስተቶች ስለመሆናቸውም በም/ቤቱ የቀረበው ዕቅድ በዋናነት የጠቀሳቸውም ናቸው፡፡

በእኚህ አካላት የሚፈጠሩ ግርግሮች እና ሁከቶች #ለሽብር ተግባሩ ተልዕኮ አራማጆች በር የሚከፍት በመሆን ጭምር ስለመስተዋሉም እቅዱ አያይዞ አመልክቷል፡፡

አንዳንድ ጊዜም የእግር ኳስ ጨዋታዎች በከተማዋ በሚካሄዱበት ወቅትም መሰል #የረብሽ_ትንኮሳዎችን ተከትሎ ገጽታን የማበላሸት ተግባር በተወሰኑ አካላት #ጠንሳሽንት ተስተውሏልም የጸጥታ ም/ቤቱ ያቀረበው ዕቅድ ያመለከተው፡፡

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር #መስፍን_ዶቢሳ በበኩላቸው የከተማዋን ሁለንተናዊ ተመራጭነት ጋር ተያይዞ ታላላቅ በዓላትና ዝግጅቶች ከተማዋ በተደጋጋሚ ማስተናገድዋን አውስተው እነዚህን ክብረ በዓላትን በማዋክ የከተማዋን ገጽታ ለማበላሸት የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የእኩይ ሥነ-ምግባር ባለቤቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ስለሆነም ፖሊስ ብቻውን ለከተማዋ ሠላም ወንጀለኞችን የመቆጣጠር ተልዕኮን መወጣት ስለማይችል የጠቆሙት እነዚህን ሸብር ፈጣሪ
ህብረተሰቡ አጋልጦ ለፍርድ በማቅረብ የበኩሉን እገዛ ሊያበረክት እንደሚገባ ኮማንደር መስፍን አሳስበዋል፡፡

የመምሪያው ኃላፊ ኃይለየሱስ ነጌሶ በበኩላቸው በከተማዋ የሚከናወኑ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ለገቢ አቅም የሚሆኑ ከመሆናቸው በላይ ገጽታን የሚያጎለብቱ ናቸው ብለዋል፡፡

ሆኖም እኚህን እና መሰል ከተማዋ የምታስተናግዳቸው ሁነቶችን በመጠቀም #ሁከት የሚፈጥሩ ሃይሎች በንብረት ላይ የሚያደርሱትን የከፋ አደጋ ለመቋቋም የህግ የበላይነትን ማስከበር ወሣኝ እንደሆነ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

የአስተዳደሩ የጸጥታ መምሪያ ኃላፊ ኃይለዮሐን ነጌሶ እንደገለጹት ለወንጀል እና ወንጀለኞች መበራከት የሺሻ፣ የጫትና የኮንትሮባንድ ንግድ ተግባራት ተጠቃሽ እንደሆኑ ገልጸው ይህም የተቀናጀ የክትትልና ቁጥር ተግባርን የሚጠይቅ እንደሆነ በማስረዳት ነው፡፡

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ሱኳሬ ሹዳ በበኩላቸው ከምንም በላይ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ተልዐኮውን እንደሚወጣ በመጠቆም ለዚህም ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

ም/ከንቲባው አያይዘውም በአንዳንድ የሃይማኖት ተቋማት የሚስተዋሉ የድምጽ ብክለቶችን ጨምሮ ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው የምሽት ጭፈራ ቤት ያሏቸው አካላት ሣይቀሩ ለከተማዋ ሠላም መደፍረስ ምክንያት በመሆናቸው የፀጥታ ሃይሉ እና ህብረተሰቡ በተቀናጀ መልኩ የሚያደርገው ጥረት ወሣኝ ስለመሆኑ በማስረዳት ነው፡፡

ምንጭ፦ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
6400 ላይ 'A' ብለው በመላክ #የጎዳና ልጆችን መልሶ ለማቋቋም የድርሻዎትን ይወጡ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia