አሳዛኝ ዜና‼️
በዲላ ከተማ ልዩ ቦታው ሞላ ጎልጃ ወረድ ብሎ የድሮው ቱቱፈላ ፔንሲዮን አካባቢ የተሰጣ ልብስ በማስገባት ላይ በነበሩ የቤተሰብ አባላት ላይ በደረሰ የኤሌክትሪክ አደጋ፣ አንድ እናት ከሶስት ልጆቿ ጋር #መሞቷ ተሰምቷል። አምስተኛ የቤተሰብ አባል በደረሰበት ከከፍተኛ ቃጠሎ በዲላ ሆስፒታል የህክምና #እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል።
🔹ከሟቾቹ አንዷ በነገው ዕለት ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ልታቀና የተዘጋጀች ነበረች።
©ማስተዋል
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#UpdateSport ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን 5 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸነፈ። በጫወታው ሱዋሬዝ 3 ግቦችን አስቆጥሯል። ቪዳል እና ኩቲኒሆ የቀሩትን የባርሴሎና ግቦች ሲያስቆጥሩ ለሪያል ማድሪድ ብቸኛውን ግብ ማርሴሎ አስቆጥሯል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ታላቁ ቤተ መንግስት⬆️
በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤትና #መኖሪያ የሚገኝበትን በአራት ኪሎ አካባቢ የሚገኘው የአፄ ምኒልክ ቤተ መንግሥት በዘመናዊ መንገድ በማደስና በማልማት ወደ #ሙዚየምነት ለመቀየር፣ የፈረንሣይ መንግሥት #ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱ ታወቀ።
የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት ታላቁን የምኒልክ ቤተ መንግሥት በማደስና ተጨማሪ ልማቶችን በማከናወን፣ ለሕዝብና ለጎብኝዎች ክፍት የሚሆን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ዕቅድ ተይዟል፡፡ ይህንንም በፍጥነት በተግባር ለመቀየር የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርትሚኒስቴር ኃላፊነት ተሰጥቶታል።
ይሁን እንጂ ፕሮጀክቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው በበላይነት እየተከታተሉት እንደሚገኝ ታውቋል። በዚህም መሠረት የተለያዩ አገሮች ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኝነታቸውን እንዳሳዩ፣ በዋናነት ግን የፈረንሣይ መንግሥት አስፈላጊውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱን ምንጮች ጠቁመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ሳምንት የሚያደርጉትን የአውሮፓ ጉብኝት በፈረንሣይ የሚጀምሩ ሲሆን፣ በፈረንሣይ በሚኖራቸው የአንድ ቀን ቆይታ ቤተ መንግሥቱን ወደ ቱሪዝም መዳረሻ ለመቀየር ለተቀረፀው ፕሮጀክት የሚፈለገውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ የተመለከተ ስምምነት ተፈራርመው ይመለሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግንቦት ወር 2010 ዓ.ም. በውጤታማ ሥራ አፈጻጸም ላይ በወቅቱ ለነበሩ የካቢኔ ሚኒስትሮች ባደረጉት ገለጻ፣ የአፄ ምኒልክ ቤተ መንግሥትን የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ እንደሚገባ መግለጻቸው ይታወሳል።
ቤተ መንግሥቱ ኢትዮጵያ ምን እንደምትመስልና ጥንታዊ ገናናነቷ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ መሆን በወቅቱ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ያለፋት የኢትዮጵያ መንግሥታት እያንዳንዳቸው በቅጥር ግቢው ትተው ያለፋትን አሻራ ለማሳየት፣ ለዓመታት የተዘጉ ቤቶችን በማስከፈት የካቢኔ አባሎቻቸውን እያዞሩ ማስጎብኘታቸው አይዘነጋም።
ምንጭ፦ ሪፖርተር

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቅሬታ‼️
በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች ተቋማቸው የተሟላ ዝግጅት ሳያደርግ እንደጠራቸው ለTIKVAH-ETH በላኩት መልዕክት ገልፀዋል። ቅሬታቸውን ካሰሙት መካከል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እና የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይገኙበታል።
መልዕክታቸው ለTIKVAH-ETH የላኩ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው በመኝታ ክፍሎች እና በእቃ ማስቀመጫ ሎከሮች ጉድለቶች እንዳሉበት ተናግረዋል። በአንድ የመኝታ ክፍል ውስጥም ከ6 በላይ ተማሪዎች እንዲያድሩ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል። በፀጥታው ረደግ አስተማማኝ የሆነ ሰላም እንዳለ የሚናገሩት ተማሪዎቹ የዩኒቨርሲቲው እና የአካባቢው ማህበረሰብ ላደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል። ያሉ ችግሮች እና ጉድለቶችም በፍጥነት እንዲስተካከሉ ጠይቀዋል።
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የጤና ተማሪዎች በበኩላቸው በቂ የሆነ የዕቃ ማስቀመጫ ማግኘት እንዳልቻሉ ገልፀዋል። ያለ ሎከር እቃቸው ሜዳ ላይ በመሆኑ ለንብረታቸው መሰረቅ እንደሚያሰጋቸው ተናግረው ተቋሙ ችግሩን እንዲቀርፍ ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል...
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በግቢው ያለው ጥበቃ እንዲጠናከር ጠይቀዋል። ከሰሞኑን መስኮት እየተሰበረ ንብረት ዝርፊያ እየተፈፀመ እንደሆነ አንስተው ተቋሙ በቂ እና አስተማማኝ ጥበቃ እንዲያደርግላቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
🔹ከዩኒቨርሲቲዎቹ በኩል ምላሽ ካገኘው በቀጣይ የማቀርብ ይሆናል።

#update በቅርቡ አራተኛ ዓመት የሥራ ዘመኑን ለጀመረው አምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ስብሰባ #ለማድረስ የመሰብሰቢያ አዳራሹን ጨምሮ ለተለያዩ የሕንፃ ክፍሎች ዕድሳት ጥገና፣ ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ታውቋል፡፡
ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድሬዳዋ ከተማ የሰው ህይወት አለፈ‼️
ትላንት ቅዳሜ ምሽት በድሬዳዋ ከተማ በተለምዶ ገንደ ቦዬ ተብሎ በሚጠራው መንደር በተቀሰቀሰው #ግጭት የአንድ ወጣት ህይወት ማለፉ ተሰምቷል። ምሽቱ በጥይት እሩምታና በአስለቃሽ ጭስ ተኩስ ነዋሪዎችን ጭንቀት ውስጥ ከቶ ያለፈ ነበር።
በምሽቱ ግጭት ህይወቱን ያጣው ወጣት #አብዱረዛቅ_ሪቫቶ ከፀጥታ ሀይሎች በተተኮሰበት ጥይት ለአካል መቁሰል ተዳርጎ ወደ ድል ጮራ ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱን ለማትረፍ አልተቻለም።
ፍፁም መከሰት የሌለበትና በቀላሉ ሊፈታ የሚገባው ችግር ማመዛዘን በጎደለውና በቸኮለ እርምጃ የሰው ህይወት በድሬዳዋ ተቀጥፏል ብሏል ዜናውን ያሰራጨው ድሬ ትዩብ።
ጨምሮም የህግ አስከባሪዎች ለሚወስዱት ማንኛውም እርምጃ ሞያዊ ክህሎት የተላበሰና ማስተዋል የተጨመረበት መሆን አለበት፤ ኮሽ ባለ ቁጥር አፈ ሙዝ የሚደቅን የፀጥታ ሀይል አላግባብ በሆነ መልኩ ህይወትን ያሳጣል ብሏል።
በድሬዳዋ ገንደ ቦዬ መንደር በመሬት ጉዳይ የተነሳው ውዝግብን ለመፍታት የፀጥታ ህይሎች ችግሩ ሳይፈጠር መፍታትና #መቆጣጠር ሲችሉ የረፈደ እርምጃቸው ውዱን የሰው ህይወት አላግባብ እንዲመክን ምክንያት ሆኗል ሲል ድሬ ትዮብ ጨምሮ አስነብቦናል። በወጣቱ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልፆ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን ተመኝቷል።
ምንጭ፦ ድሬ ትዩብ

#update የሌስተር ሲቲው ባለቤት ቪቻይ በተከሰከሰው ሂሊኮፍተር ውስጥ ከነበሩ 5 ሰዎች መካከል እንደሚገኙ ለመስማት ተችሏል። በርካቶች #በተከሰተው ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች የተሰማቸውን ሃዘን እየገለፁ ይገኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር ዐብይ ወደ አውሮፓ🛫ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት እና የጀርመኗ መራሂተ መንግስት ባደረጉላቸው ጥሪ መስረት ዛሬ ጠዋት ላይ ወደ አውሮፖ አቀኑ። ከፓሪስና በርሊን በተጨማሪ በፍራንክፈርትም ተገኝተው በአውሮፖ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በቤንሻንጉል ካማሺ ዞን #መረጋጋት እየተፈጠረ ይገኛል ተባለ። በዚህም ድጋፍ ለሚሰፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ነው የተሰማው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#upate የመንግስተ አብ ኢንዱስትሪያልና ኮሜርሻል ድርጅት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሠራተኞች የቅጥር ውላቸውን ባላገናዘበ ሁኔታ ከስራ #በመሰናበታቸው ለችግር መጋለጣቸውን ገለፁ፡፡ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲህ ዓይነት በደል የሚፈፀምባቸው ዜጐች ትክክለኛ መረጃ ካቀረቡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሊያግዛቸው ዝግጁ ነው ብሏል፡፡
ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ‼️
በኢንዶኔዢያ #ጃካርታ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን ለበረራ ከተነሳ ከደቂቃዎች በኋላ ባህር ውስጥ #መከስከሱ ተነግሯል።
የላየን አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737 አውሮፕላን 188 ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ እያለ ነበር በጃካርታ ባህር ወስጥ የተከሰከሰው።
ከአደጋው እስካሁን በህይወት የተረፈ ሰው ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም ብለዋል የአካባቢው ባለስልጣናት።
ምንጭ ፦ ቢቢሲ

ኮ/ል ጎሹ ወልዴ አዲስ አበባ ገቡ‼️
በደርግ ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ኮ/ል #ጎሹ_ወልዴ ዛሬ አዲሰ አበባ ገብተዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመንና እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ ጉዳዮች ዳ/ጀነራል አቶ ነብያት ጌታቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርግውላቸዋል።
የቀድሞው ሚኒስትር በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የደርግን አገዛዝ በመቃወም ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ከለቀቁና ኑሯቸውን በአሜሪካ ካደረጉ ጀምሮ ላለፉት 32 አመታት የአገራቸውን መሬት ሲረግጡ የመጀመሪያቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ኮ/ል ጎሹ ወልዴ አመጣጣቸው የአገሪቱን አጠቃላይ የለውጥ ሂደት ለማየት፣ ለረጅም ጊዜ የናፈቋቸውን ዘመድ ወዳጆች ለማግኘትና የተጀመረውን የሰላም፣ የፍቅርና የመደመር ሂደት በሚችሉት መጠን ለመደገፍ መሆኑን ገልጸዋል።
ምንም አይነት ፖለቲካዊ ውድድር የማድረግም ሆነ ስልጣን የማግኘት ፍላጎት የለኝም ያሉት ኮ/ል ጎሹ፣ በአሁኑ ወቅት በአገራችን የተጀመረው የሰላም፣ የእርቅና የመደመር እንቅሴቃሴ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ በመሆኑ እርሳቸውን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊደግፈው እንደሚገባ በማመን መምጣታቸውን ጠቁመው ለዚህም ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ወጣቱ የሰላምን አስፈላጊነት በሚገባ ተገንዝቦ ለግጭት ከሚዳርጉ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ማንኛውንም ጥያቄዎች
በሰላማዊ መንገድ በማቅረብ መፍትሄ ማግኘት የሚያስችል ሁኔታ ተፈጥሯል የሚል እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል።
ለዚህም ያላቸውን ልምድና ተሞክሮ ለማጋራትና ለሰላማዊ ሂደቱ መጎልበት የተቻላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ቃል ገብተዋል።
ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

#update በምርጫ ቦርድ በሕጋዊነት #ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝርዝር፦
🔹አገር ዓቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች
1. የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት
2. የኢትዮጵያ ሰላማዊ የዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
3. የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር
4. የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
5. የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት
6. ገዳ ሥርዓት አራማጅ ፓርቲ
7. የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ኅብረት
8. መላው ኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
9. የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ
10. የመላው ኢትዮጵያዊያን ብሔራዊ ንቅናቄ
11. ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ
12. የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ንቅናቄ
13. የወለኔ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
14. የመላው ኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራቲክ ፓርቲ
15. የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ
16. የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ
17. ሰማያዊ ፓርቲ
18. የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ
19. አዲስ ትውልድ ፓርቲ
20. የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ
21. አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ
22. የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ኮንግረስ
🔹ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች
1. ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ
2. የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
3. ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
4. የምዕራብ ሶማሌ ዲሞክራቲክ ፓርቲ
5. የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ
6. የኦሮሞ አቦ ነጻነት ግንባር
7. የደንጣ፣ ዱባሞ ክችንችላ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
8. የከምባታ ሕዝቦች ኮንግረስ
9. የትግሪ ወርጂ ብሔረሰብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት
10. የኦሮሞ ነጻነት አንድነት ግንባር
11. የዶንጋ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
12. የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ
13. የኢትዮጵያዊያን አንድነት ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
14. የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
15. የሐድያ ብሔር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
16. የጌዴኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት
17. የየም ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
18. የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
19. የኦሮሚያ ነጻነት ብሔራዊ ፓርቲ
20. የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት
21. የሲዳማ አርነት ንቅናቄ
22. የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር
23. የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
24. ዱቤና ደገኒ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
25. የዲል ወቢ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
26. የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር
27. የሲዳማ ሀዲቾ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት
28. የቤንች ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት
29. የሸኮና አካባቢው ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት
30. ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲ ሉዓላዊነት
31. የአርጎባ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት
32. የሐረሪ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት
33. የጋምቤላ ሕዝቦች አንድነት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ
34. የአርጐባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
35. የቤንሻንጉልና ጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
36. የአገው ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
37. የጉምዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ን ቅናቄ
38. የቤንሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ለሠላምና ለዴሞክራሲ ድርጅት
39. የስልጤ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
40. የደቡብ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኮንግረስ
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ
@tsegabwolde @tikvahehiopia