#update አቶ አህመድ ሽዴ⬇️
በአዲስ አበባ ከተማ ሰዎች ታፍሰው ተወሰዱ ተብሎ የሚሰራጨው ወሬ የተሳሳተ መሆኑንና ህብረተሰቡን ለማደናገር የሚሰራ ስራ እንደሆነ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚንስትሩ አቶ #አህመድ_ሽዴ
አስታወቁ።
ሚኒስትሩ በወቅታዊ ጉዳይ በሰጡት መግለጫ፥ በተለያዩ አካባቢዎች ህይወት እንዲጠፋና ንብረት እንዲወድም በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎች በህጋዊ መንገድ በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።
መንግስት በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የፓለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ከመስከረም 2 ጀምሮ የፖለቲካ ኃይሎችን ለመቀበል በደጋፊዎቹ መካከል በተፈጠረው ያልተገባ #ፉክክር ግጭቶች መፈጠራቸውን አስታውሰዋል።
እየሰፋ ቤደው ግጭትም በቡራዩ 27 ሰዎች በአዲስ አበባ 28 በጥቅሉ 55 ሰዎች #ህይወታቸው እንዳለፈ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም በቡራዩ ከተማ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት እንዳጋጠመና 3 ሺህ 50 ሰዎችም መፈናቀላቸውን ገልፀዋል።
እነዚህን ግጭቶች የብሄር ማስመሰልና በማህበራዊና በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የተዛቡ መረጃዎችን በማቅረብ ግጭቱን ለማባባስ እንቅስቃሴ ተደርጓል ብለዋል።
በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ከተማ ከግጭቱ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው 170 ሰዎችና በቡራዩ ከተማ ደግሞ 390 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተናግረዋል።
እንዲሁም በአዲስ አበባ ሁከቱና ብጥብጡን ለማማባባስ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ 1200 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
ችግሩን ለመቆጣጠር የፍትህና የፀጥታ አካላት ባደረጉት ርብርብ ችግሩ በቁጥጥር ስር እንደዋለ አስታውቀዋል።
#መንግስት በደረሰው የህይወት መጥፋት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት የተሰማውን #ሀዘን ሚኒስትሩ ገለፀዋል።
©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#Update ቡኖ በደሌ⬆️
ከኦሮሚያ የተፈናቀሉ ዜጎች ሽኝት ተደረገላቸው። ባለፈው ዓመት ከኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን ቦረቻ ወረዳ ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች አካባቢው ሰላም በመሆኑ ወደ መጡበት እንዲመለሱ #ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ #አማረ_ክንዴ አንደተናገሩት ተፈናቃዮች እንዲመለሱ ከዞኑ አስተዳደር ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በጉዞ ላይ እና ከደረሱም በኋላ የሚጠቀሙባቸው አልሚ ምግብ እና ዱቄት መዘጋጀቱንም ኃላፊው ተናግረዋል።
አቶ አህመድ ኑር ከተፈናቃዮች መካከል አንዱ ሲሆኑ የክልሉ መንግሥት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
መንግሥት የዜጎችን ተዘዋውሮ የመሥራት ሕገ-መንግሥታዊ መብት ማስጠበቅ አንዳለበትም አቶ #አህመድ አሳስበዋል።
ምንጭ ፦ አ.ብ.መ.ድ.

#update አንዋር መስጊድ⬇️
አንዋር መስጊድ ቅጥር ግቢ ታህሳስ 1 ቀን 2008 ዓ.ም በግምት ቦንብ በመወርወር የሽብር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ11 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።
ተከሳሽ #አህመድ_ሙስጠፋ_አብዶሽ የራሳቸውን ሃይማኖታዊ ዓላማን ለማራመድ በማሰብ፣ በመንግስት ላይ ተፅእኖ ለማሳደርና ህብረተሰቡን ለማሸበር እንዲሁም በኢፌዲሪ ህገ-መንግስት የተረጋገጠውን የሃይማኖት ነጻነት በመቃረን ከራሳቸን አስተሳሰብና አስተምህሮት እምነት ውጪ ሌላ አስተምህሮት መኖር የለበትም የሚል ዓላማ በመከተል ቀኑና ወሩ ባልታወቀ
በ2007 ዓመተ ምህረት ተከሻሽ በሚጠቀምበት የሞባይል ስልክ ቁጥር በማህበራዊ ድረ-ገጽ ላይ የተዋወቀውንና ያልተያዘውን ግብረ-አበሩን ሼክ አሊ ሀይደር ጋር በመነጋገር ሀበሽ እስላም አይደለም ይህን ተግባር ካሳካህልኝ 100 ሺህ አሰጥሃለሁ በማለት ተከሳሽ ከሚኖርበት ሶማሌ ክልል ልዩ ቦታው ኤረር ጎታ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በመነሳት አዲስ አበባ ሂዶ በአንዋር መስጊድ ላይ ቦንብ እንዲያፈነዳ በግብረ አበሩ በኩል ተልዕኮ እንደተሰጠው የወንጀል ዝርዝሩ ያስረዳል፡፡
ተከሳሽም ተልዕኮውን ለመፈጸም አዲስ አበባ በመግባት የአንዋር መስጊድን ሁኔታ አጥንቶ ለግብረ አበሩ ማህበራዊ ድረ-ገጽ መልዕክት የላከለት ሲሆን ፥ ታህሳስ 1 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት በአንዋር መስጊድ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመግባት በመስጊዱ ውስጥ ተሰብስበው በዝየራ ላይ በነበሩት ሰዎች ላይ ቦንቡን በመወርወር በ24 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት በማድረሱ በሽብርተኝነት ወንጀል ድርጊት በመፈጸም ክስ ተመስርቶበት ቆይቷል።
የፌደራል ዐቃቤ ህግም በጉዳዩ ላይ 30 ሰዎችን የምስክርነት ቃልና የተጎጂዎችን የህክምና ማስረጃ እንዲሁም የተከሳሽን የእምነት ቃል ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት የ11 ዓመት ፅኑ እስራት እንደበየነበት የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ

#Update በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ #ናፍታ_በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። በገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የህግ ተገዢነት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ #አህመድ_መሀመድ እንዳስታወቁት፥ በህገ ወጥ መንገድ ናፍታ ጭነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ተሽከርካሪዎች በሱማሌ ክልል ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት። ነዳጅ ጭነው ሲጓዙ የነበሩ መኪናዎች አሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አቶ አህመድ አስታውቀዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የነዳጅ ፍላጎትና አቅርቦት ካለመመጣጠን ጋር በተያያዘ በየነዳጅ ማደያዎች ረጃጅም ሰልፎችን መመልከት እየተለመደ መጥቷል። ለዚህም በምክንያትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ህገ ወጥ የነዳጅ ንግድ አንዱ ሲሆን፥ ተገቢ ያልሆነ ውድድር እና የሎጅስቲክስ አቅርቦቱ ምቹ አለመሆን የዘርፉ ችግሮች በመሆን ይጠቀሳሉ።
ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️
የሱማሌ ክልል መሪ--አቶ #ሙስጠፋ_ኡመር-የፌዴራል ገንዘብ ሚኒስትሩን አቶ #አህመድ_ሺዴን-በይፋ በክልሉ መንግስት ላይ "ዓመፃ-ክህደት በመፈፀም" እጅግ ከባድ ወንጀል #ከሰሱ። ም/ፕሬዚደንት ሙስጠፋ ኡመር የሶማሌ ህዝብ ዲምክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ላይ የደረሱበትን ማስረጃ ለሚዲያ ለመግለፅ የማይቻልና ጠ/ሚኒስትሩን ጨምሮ ለፌዴራል ባለስልጣኖች በሚሰጡት ማብራሪያ ላይ የሚገለፅ መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል። ሙስጠፋ 11 የካቢኔ አባላትን መርተው ዛሬ ከሰዓት #አዲስ_አበባ መግባታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።
.
.
https://telegra.ph/BREAKING-01-25

Telegraph
BREAKING
Addis Abeba, January 25/2019 – Mustafa Omer, Vice President of the Somali regional state, told Addis Standard that the regional government has “foiled a highly dangerous, sophisticated, and well planned attempt to plunge the region into chaos and collapse.”…
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 17/2011 ዓ.ም.
ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚከበረው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቀን በአየር ኃይልና በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ትብብር #በአዳማ ከተማ እንደሚከበር፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡ በዓሉም የካቲት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
.
.
ዛሬ ማለዳ በተካሄደው የዱባይ ማራቶን ጌታነህ ሞላ የቦታውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል። በሴቶች ኬንያውያን እኤአ ከ2006 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፈዋል፡፡
.
.
አቶ #በረከት_ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ በተጠረጠሩበት የጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት ጉዳይ ዛሬ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
.
.
#የአገር_መከላከያ_ሰራዊት አባላት እና የሶማሌ ክልል #ልዩ_ሀይል አባላት ዛሬ #በጅግጅጋ_ከተማ የፅዳት ስራ አከናውነዋል።
.
.
በነጭ ሣር ፓርክ ላይ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት እሳት ተነስቶ 1 ሺ ሄክታር የሚሆን የፓርኩ ክፍል ወድሟል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ #የተቀሰቀሰው_ተቃውሞ ዛሬ ጥር 17/2011 ዓ.ም. ቀጥሎ ውሏል። የኢንተርኔት አገልግሎት ተዘግቷል።
.
.
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2 ዙር በተካሄደ ነፃ የስራ ዘመቻ 3.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ስራ መሰራቱን ተናግሯል።
.
.
የኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የ100 ቀናት እቅዱን በአርባምንጭ ከተማ ገምግሟል።
.
.
በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት እጃቸውን በማስገባት ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር #በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታውቋል።
.
.
በሳኡዲ አረቢያ በተለያየ ምክንያት ታስረው የነበሩ 368 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ አገራቸው ገብተዋል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የሕዝቡን አብሮነት እና ተቻችሎ የመኖር እሴት የሚሸረሽር በመሆኑ ሰላምን በማወክ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል።
.
.
በኢትዮጵያ #የመጀመሪያ የሆነ የሚዲያ ኤክስፖ በኤግዚብሽን ማዕከል ዛሬ ተከፍቷል።
.
.
የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ አቶ #ጌታቸው_አሰፋን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከክልሉ መንግሥት ጋር እየሰራ እንደሆነ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።
.
.
በጉጂ ዞን ይንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/አባላት ከጫካ ወጥተው #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰናቸውን ገልፀዋል።
.
.
የሱማሌ ክልል መሪ--አቶ #ሙስጠፋ_ኡመር-የፌዴራል ገንዘብ ሚኒስትሩን አቶ #አህመድ_ሺዴን-በይፋ በክልሉ መንግስት ላይ "ዓመፃ-ክህደት በመፈፀም" እጅግ ከባድ ወንጀል #ከሰዋል።
ምንጭ፦ አዲስ ስታንዳርድ፣ fbc፣ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ elu፣ ቢቢሲ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
አመሰግናለሁ! ሰላም እደሩ!!
ሀገራችን ቸር ትደር!!
ጥር 17/2011 ዓ.ም.

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፋ_ዑመር እና የሶማሌ ክልል ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር #አህመድ_ሽዴ ጋር በክልሉ ልማትና ፀጥታ ጉዳይ ላይ ተወያዩ።
Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜቴክ ይቅርታ መጠየቅና እርቅ ማውረድ እንደሚፈልግ አስታወቀ‼️
.
.
"ይቅርታ መጠየቅና #እርቅ ማውረድ ካለበት አካል ጋር ሁሉ ይህንን ያደርጋል"
"መልዐክ ሆኖ ቢመጣ ሰው #ሰይጣን በሚል እንደሚያነበው አውቆ ስሙን ይቀይራል"
.
.
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፓሬሽን/ሜቴክ/ይቅርታ መጠየቅና #እርቅ ማውረድ ካለበት አካል ጋር ሁሉ እንደሚያደርግ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል #አህመድ_ሀምዛ አስታወቁ፡፡
ብርጋዴር ጀነራል አህመድ ሀምዛ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንገለጹት፤ ሜቴክ ከሥራ አጋሮቹ ጋር የነበረው ግንኙነት የተበላሸና በጸብ የተሞላ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት ይቅርታ መጠየቅና እርቅ ማውረድ ካለበት አካል ጋር ሁሉ ይህንን ይፈጽማል፤ ተቋሙም የህዝብ እንደመሆኑ ከዚህ በኋላ ሚስጢር አይኖረውም፤ እቅዶች ድረ ገጾች ላይ ይቀመጣሉ፤ ለመገናኛ ብዙኃንም ክፍት ይሆናል ብለዋል።
ተቋሙ አብረውት ከሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችን እያደረገ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ‹‹አገልግሎት ሰጪ እስከ ሆንን ድረስ ከአገልግሎት ፈላጊው ዝቅ ብሎ ነው መታየት ያለብን›› ብለዋል፡፡ ደንበኞች ለከፈሉት ገንዘብ እንኳን አገልግሎት ሲጠይቁ ይሰጣቸው የነበረውምላሽ በጣም አደገኛና በጸብ የተሞላ እንደነበር በማስታወስ ይህንን ሁኔታ ለመቀየርም እንደሚሰራ አብራርተዋል።
ስኳር ኮርፖሬሽንን ለአብነት በመጥቀስም ከኮርፓሬሽኑ ጋር የነበረው ግንኙነት ጥሩ እንዳልነበረ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ኮርፖሬሽኑ በጣም ከፍተኛ ገንዘብ ከፍሏል፤ ተቋሙ ግን ጨርሶ ያስረከበው አንድም ፕሮጀክት የለም፡፡ ፕሮጀክቶቹን ካለማጠናቀቅም በላይ አንዳንዶቹን ወገብ ወገባቸው ላይ እያደረሰ ነው በሀይል እንዲረከቡ ያደረገው›› ሲሉ ያብራራሉ።
በሌላ በኩል መልካም ስምን ከመገንባት አንጻር አደረጃጀቱን መቀየር ያስፈልጋል ያሉት ብርጋዲዬር ጀነራል አህመድ ፣ ‹‹ሜቴክ ከአሁን በኋላ መልዐክ ሆኖ ቢመጣ እንኳ ሰው ሰይጣን ብሎ ስለሚያነበው ስሙን መቀየር አስፈልጓል››ብለዋል፡፡ ይህንን ለማከናወንም መረጃዎችን የማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
መረጃ የማሰባሰብ ስራው ከተጠናቀቀ በኋላም በጥቂት ጊዜ ውስጥ አደረጃጀቱንና ስሙን በመቀየር በአዲሱ ስሙም አዲስ ሆኖ እንደሚቀርብና እንደ ማንኛውም የልማት ድርጅት ህግን ተከትሎ መስራት እንደሚጀምር አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት በስድስት ወራት ውስጥ ተሰርቶ የሚጠናቀቅ የሪፎርም እቅድ መዘጋጀቱን ገልጸው፣ ይህ እቅድ ሲዘጋጅ ይሳካሉ ተብለው ከተቀመጡ ግቦች መካከል ዋናው የተቋሙን የጠፋ ስም መመለስ፣ በህግና ስርዓት ብቻ ተከትሎ እንዲሰራ ማድረግ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ምንጭ፦ አዲስ ዘመን

TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 21/2011 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ መንግስት “የጤፍ ባለቤት ነኝ” ያለውን የሆላንድ ድርጀት በዓለም አቀፉ የግልግል ፍርድ ቤት ሊከስ ነው።
.
.
በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ሁለት አርሶ አደሮች በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር "ኦነግ ታጣቂዎች" መገደላቸውንና አንድ አርሶ አደር መቁሰሉን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
.
.
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የሴፍቲና ሲኬዩሪቲ ዲፓርትመንት ባለሙያዎች በባቡሩ ላይ #ድንገተኛ የእሳት አደጋ ቢከሰት እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል የሚያሳይ ልምምድ አካሂደዋል።
.
.
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት የቀጠለውን የሚኒስትርና ተጠሪ መስሪያ ቤቶችን የ100 ቀን እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መርተዋል።
.
.
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፓሬሽን/ሜቴክ/ይቅርታ መጠየቅና #እርቅ ማውረድ ካለበት አካል ጋር ሁሉ እንደሚያደርግ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል #አህመድ_ሀምዛ አስታውቀዋል።
.
.
በሰቆጣ ከተማ ሦስት #ፓኪስታናውያን በሕገ ወጥ የሞባይል ሽያጭ ተሰማርተው እጅ ከፈንጅ ተይዘዋል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ሰርተፍኬት፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ፣ የልደትና ሞት ሰርተፍኬት እንዲሁም የጋብቻ እና ፍቺ ሰርተፍኬቶች በዲጂታል ሰርተፍኬት ሊቀየሩ ነው ተብሏል።
.
.
ኢ/ር #ታከለ_ኡማ ቦሌ አራብሳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የፈረሰውን መስጂድ በመጎብኘት የአከባቢውን የሙስሊም ማህበረሰብም አነጋግረዋል፡፡
.
.
#የፌዴራል_መንግሥት አመራሮች የድሬዳዋ ነዋሪዎችን በከተማዋ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አወያይተዋል፡፡
.
.
በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና በማህበራዊ ፍትህ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያውን አረንጓዴ የፖለቲካ ፓርቲ (Green Party) ለማቋቋም ጊዜያዊ አስተባባሪ ፓርቲ መሰየሙን ዋዜማ ራድዮ ዘግቧል።
.
.
ከሳውዲ አረቢያ ጋር በተደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በህጋዊ መንገድ ለሚሄዱ ሰራተኞች የቪዛ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።
.
.
ግምታዊ ዋጋው 400 ሺህ ብር የሚያወጣ የባህርዛፍ አጠና ያለምንም ህጋዊ ሰነድ ከአገር ሊወጣ ሲል #በጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
ከጥር 19 እስከ 21 ለተከታታይ ሦስት ቀናት #በሀዋሳ_ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበሩን በመምረጥ ተጠናቋል።
.
.
ከጭናግሰን ከተማ የማርያምን ክብረ በዐል አክብረው ይመለሱ በነበሩ ምዕመናን ላይ ወጣቶች መንገድ መዝጋታቸውን ተከትሎ #በጅግጅጋ_ከተማ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መረጋጋቱ ታውቋል። በግጭቱ የ2 ሰው ህይወት አልፏል።
.
.
ቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለተከታተሉበት የጎንደሩ ጻዲቁ ዮሐንስ 1ኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት የኮምፒዩተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
.
.
#በድሬዳዋ_ከተማ የትራንስፖርትና የግብይት #አድማ ለማድረግ ያቀዱ ነዋሪዎች ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ዘንድ #የምስራቅ_ዕዝ_ጠቅላይ_መምሪያ አስጠነቅቋል።
.
.
አቃቤ ሕግ የቀድሞ #የሜቴክ የስራ #ሀላፊዎች በነበሩት ሻለቃ #ክንደያ_ግርማይና ሌተናል ኮሎኔል #አሰፋ_ዮሐንስ ላይ ክስ መስርቷል።
.
.
የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) በዚህ ሳምንት ሐሙስ በይፋ ትጥቅ ይፈታል።
.
.
በቅርቡ በመንግስት እና ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መካከል በአምቦ በተደረገው ስምምነት መሠረት እርቁን ተግባራዊ ለማድረግ የተመረጠው የቴክኒክ ኮሚቴ ሥራውን በተግባር መጀመሩን የቴክኒክ ኮሚቴው አባል አቶ #ጀዋር_መሀመድ አስታውቀዋል።
.
.
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ #ዝናሽ_ታያቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምናና የኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና ለሁለት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አድርገዋል።
.
.
#የኢፌዲሪ_አየር_ሃይል በሶማሊያ ከባይደዋ በስተምስራቅ 75 ኪሎ ሜትር ላይ ቡርሃይቤ በተባለ የአልሻባብ ይዞታ ላይ ጥር 16 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም ድብደባ በመፈፀም ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ የተከሰተዉን #አለመረጋጋት ተከትሎ የከተማዉ ፖሊስ ኮሚሽን 308 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያካሄደ ነዉ፡፡
ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ፣ etv፣ fbc፣ VOA፣ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት፣ የጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ አብመድ
.
.
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

ተጨማሪ፦
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ስለተከሰከሰው ቦይንግ 737 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ለጋዜጠኞች መግለጫ መስጠታቸው ይታወቃል፡፡
በመግለጫው አውሮፕላኑን ሲያበር የነበረው ከ8 ሺህ ሰአታት በላይ የማብረር ልምድ ያለውና ጥሩ የበረራ ሪከርድ የነበረው ካፒቴን #ያሬድ_ጌታቸው ሲሆን ግማሽ ኢትዮጵያዊና በግማሽ ኬኒያዊ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ረዳት አብራሪው #አህመድ_ኑር_መሀመድ ኑር የሚባል ከ200 ሰአት በላይ የበረራ ልምድ ያለው አብራሪ ነበር፡፡
እንደ ዋና ስራ አስፈፃሚው ገለፃ አውሮፕላኑ ከተገዛ ገና 4 ወራትን ያስቆጠረና ምንም አይነች ችግር ያልነበረው ንፁህ አውሮፕላን ነበር፡፡
በተከሰከሰው አውሮፕላን ላይ የነበሩ 149 መንገደኞች እና 8 የበረራ አስተናባሪዎች ዜግነታቸው ተለይቷል፡፡
በአውሮፕላኑ ላይ 32 ኬኒያውያን፣18 ካናዳዊያን፣ 9 ኢትዮጵያውያን፣ 8 ጣልያውያን፣ 8 ቻይናዊያን፣ 8 አሜሪካውያን፣ 7 እንግሊዛውያን፣ 7 ፈረንሳውያን፣ 6 ግብፃውያን፣ 5 ጀርመናውያን ሲሆኑ ከ5 የኔዘርላንዳውያን ውስጥ 4ቱ የተባበሩት መንግስታት ፓስፖት የያዙ መንገደኞች መሆናቸው ታውቋል፡፡
4 ህንዳውያን፣ 4 የስሎቫኪያ ዜጎች፣ 3 የኦስትሪያ ዜጎች፣ 3 ስዊድናውያን፣ 3 የራሻውያን፣ 2 የሞሮኮ ዜጎች፣ 2 የስፔናውያን፣ 2 ፖላንዳውያን፣ 2 እስራኤላውያን፣ 1 የቤልጄማዊ፣ 1 ኢንዶነዌዥያዊ፣ 1 ኡጋንዳዊ፣ 1 የመናዊ፣ 1 ሱዳናዊ፣ 1 ሰርቢያዊ፣ 1 ቶጓዊ፣ 1 ኔፓል፣ 1 ናይጄሪያዊ፣ 1 ሞዛንቢካዊ ዜጋ፣ 1 ሩዋንዳዊ፣ 1 ሶማሊያዊ፣ 1 ኖርዌያዊ፣ 1 የጅቡቲ ዜጋ፣ 1 አየርላንዳዊ እና 1 የሳኡዲ ዜጋ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡
Via ETV

መቶ በመቶ ፈተነዋል...
"የሃሳብ ልዩነት አልነበረንም አንልም። ይህ ደግሞ በተፈጥሮ፣ በግለሰብ ሌላው ቀርቶ በአንድ ቤተሰብ አባላት መካከል እንኳን በቴሌቭዥን ቻናል ምርጫ ልዩነት ላይ ይገጥማል። …በመካከላችን ያጋጠመው የሀሳብ ልዩነት ነበር። ይህን ደግሞ በመርህ ደረጃ እና በውይይት መቶ በመቶ ፈትተነዋል።" የሶማሌ ክልል ም/ ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፌ_ሙህመድ እና የሶ.ህ.ዴ.ፓ ሊቀመንበር አቶ #አህመድ_ሽዴ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 10ኛው የሶ.ህ.ዴ.ፓ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከተናገሩት።