TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#AlertEthiopia😷 ባለፉት 24 ሰዓት 23 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። በተመሳሳይ ከተደረገው 7,423 የላብራቶሪ ምርመራ 1,949 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ትላንት 530 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። በአጠቃላይ 194,524 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,741 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 151,172 ሰዎች አገግመዋል። በአሁን…
#እጅግ_በጣም_አሳሳቢ

26% ሀገርአቀፍ በበሽታ የመያዝ ምጣኔ።

ዛሬ ከተመረመሩት ዉስጥ 5 ክልሎች ከፍተኛ (ከ20% በላይ) የበሽታ ስርጭት የታየባቸው ፦

• ሲዳማ-37%
• ድሬዳዋ-26%
• አዲስ አበባ-29%
• ቤንሻንጉል ጉሙዝ - 27%
• ሐረር - 25%

በፀና የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ በመጨመሩ በአዲስ አበባ እንዲሁም በተወሰኑ የክልል ከተሞች ገጥሞ የነበረውን የኦክስጅን እጥረት በተለያዩ አማራጮች ለመፍታት እየተሞከረ እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር የህክምና አገልግሎት ዳይሬክተር ያዕቆብ ሰማን አስታውቀዋል።

አቶ ያዕቆብ ፥ ከጥቂት ቀናት በኃላ የኦክስጅን እጥረቱ ችግር ሙሉ በሙሉ ይፈታል ተብሎ እንደሚታመን ገልፀዋል።

እየተመዘገቡ ያኑት ቁጥሮች "የከፋ ጊዜ" ሊመጣ እንደሚችል የሚያሳዩ ስለሆነ ሁሉም ለራሱ እና ለቤተሰቦቹ ሲል ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል።

#መኖር_እየቻልን_አንሙት

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia