#update ወጣቶቹ ከጦላይ ተለቀቁ⬇️
በአዲስ አበባ ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውለው በጦላይ ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ 1 ሺህ 174 ወጣቶች ዛሬ ከእስር ተለቀዋል።
ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩት 1 ሺህ 174 ወጣቶች ዛሬ ረፋድ ላይ ከእስር መለቀቃቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር #ፋሲካ_ፋንታ ለfbc ተናግረዋል።
የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው፥ ዛሬ ማለዳ ላይ የጋራ ውይይት ከተደረገ በኋላ ተጠርጠጣሪዎቹን ወደ አዲስ አበባ የሚመልሱ ተሽከርካሪዎችን በማቀረብ እንዲለቀቁ ተደርጓል ብለዋል።
ወጣቶቹ ከመስከረም 2 እስከ መስከረም 8 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆኑ፥ በቆይታቸውም የተለያዩዩ ስልጠናዎችን ሲወስዱ መቆየታቸው ተመልክቷል።
በዚህም መሰረት ወጣቶቹ በጦላይ ለአንድ ወር እራስን ከወንጀል ስለማራቅ እና ተያያዠ ስልጠናዎችን ለመስጠት የተያዘውን የጊዜ ሰሌዳ በማጠናቀቃቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ የማጓጓዝ ስራ ተጀምሯል ብለዋል።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia