TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ኤርትራን ፕረስ" በሚል ስም የሚታወቀው የፌስቡክ ገፅ በትላንትናው ዕለት እንደገለፀው ከዚህ በሁዋላ በአስመራ ላለው የፕሬዝደንት #ኢሳያስ_አፈወርቂ መንግስት የሚያደርገውን #ድጋፍ አቁሟል። ምክንያቱ ደግሞ ፕሬዝደንቱ ልጃቸውን #አብርሀም_ኢሳያስን ፅህፈት ቤታቸው ውስጥ አማካሪ አድርገው ወደ ስልጣን ጠጋ ጠጋ እያረጉ ነው በማለት ነው። ገፁ ፕሬዝዳንቱን "አምባገነን" ያላቸው ሲሆን "ሰማእታት ህይወታቸውን የሰጡት የኢሳያስ ስርወ-መንግስት ለመመስረት አይደለም" ሲል አክሎ ገልጿል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት(AP)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቤንሻንጉል ጉምዝ⬇️

በአሶሳ ከተማ የእርዳታ እህል የተጫኑ 9 ከባድ መኪኖች መንቀሳቀስ አልቻሉም ተባለ፡፡ መኪኖቹ ወደ #ካማሺ ዞን የእርዳታ እህል ለማድረስ ታስቦ የተላኩ ነበሩ፡፡

የብሔራዊ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን የአቅርቦትና ሎጅስቲክስ ዳይክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ #ሃይድሮስ_ሀሰን ዛሬ ለሸገር 102.1 እንደተናገሩት፣ 9ኙ ተሽከርካሪዎች 2358 ኩንታል ስንዴ፣ በቆሎና የተለያዩ አልሚ ምግቦችን ተጭነው ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በፀጥታ ችግር ስጋት ከከተማው አልተንቀሳቀሱም ብለዋል፡፡

ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ መከላከል ቢሮ ጋር በመተባበር ዛሬ #በመከላከያና በፖሊስ አባላት መኪኖቹን በማጀብ የእርዳታ እህሉን ወደ ካማሺ ዞን ለማድረስ በዝግጅት ላይ እንደሆነ አቶ ሃይድሮስ ተናግረዋል፡፡

ቀያቸውን ለቀው በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ መጠለያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ግን ያለ እክል #ድጋፍ እየቀረበላቸው እንደሆነ አቶ ሃይድሮስ
ነግረውናል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ ዩኒቨርሲቲ⬆️የጅማ ዩኒቨርሲቲ የጤና ተማሪዎች ከቤንሻንጉል ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች የቀሳቀስ #ድጋፍ አድርገዋል። ተማሪዎች ያሰባሰቧቸው አልባሳት፣ ጫማዎች እንዲሁም ብርድ ልብስ ተፈናቃዮች ወደሚገኙበት ቦታ ትላንት ተልኳል። ተማሪዎች በላኩልኝ መልዕክት እንደገለፁት ይህ ድጋፍ የመጀመሪያ ዙር ሲሆን በቀጣይ መደበኛ ተማሪዎች ሲመለሱ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል። ተማሪዎቹ እግረ መንገዳቸውን ይህን ስራ ላስተባበረው የኢትዮጵያ ህክምና ተማሪዎች ማህበር (ጅማ) ምስጋና አቅርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የእንግሊዝ የልማት ተራድኦ ድርጅት (DFID) የኢትዮጵያ ተወካይ ክርስቲያን ሮግ የሶማሌ ክልልን ጎብኝተዋል። መንግስትቸው ለክልሉ ልዩ ፖሊስ #ድጋፍ አድርጓል መባሉንም #አስተባብለዋል። ከክልሉ ፕሬዝዳንት #ሙስጠፋ_ዑመር ጋርም መልካም ውይይት ማድረጋቸውን ሀላፊው ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ታላቁ ቤተ መንግስት⬆️

በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤትና #መኖሪያ የሚገኝበትን በአራት ኪሎ አካባቢ የሚገኘው የአፄ ምኒልክ ቤተ መንግሥት በዘመናዊ መንገድ በማደስና በማልማት ወደ #ሙዚየምነት ለመቀየር፣ የፈረንሣይ መንግሥት #ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱ ታወቀ።

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት ታላቁን የምኒልክ ቤተ መንግሥት በማደስና ተጨማሪ ልማቶችን በማከናወን፣ ለሕዝብና ለጎብኝዎች ክፍት የሚሆን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ዕቅድ ተይዟል፡፡ ይህንንም በፍጥነት በተግባር ለመቀየር የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርትሚኒስቴር ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

ይሁን እንጂ ፕሮጀክቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው በበላይነት እየተከታተሉት እንደሚገኝ ታውቋል። በዚህም መሠረት የተለያዩ አገሮች ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኝነታቸውን እንዳሳዩ፣ በዋናነት ግን የፈረንሣይ መንግሥት አስፈላጊውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱን ምንጮች ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ሳምንት የሚያደርጉትን የአውሮፓ ጉብኝት በፈረንሣይ የሚጀምሩ ሲሆን፣ በፈረንሣይ በሚኖራቸው የአንድ ቀን ቆይታ ቤተ መንግሥቱን ወደ ቱሪዝም መዳረሻ ለመቀየር ለተቀረፀው ፕሮጀክት የሚፈለገውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ የተመለከተ ስምምነት ተፈራርመው ይመለሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግንቦት ወር 2010 ዓ.ም. በውጤታማ ሥራ አፈጻጸም ላይ በወቅቱ ለነበሩ የካቢኔ ሚኒስትሮች ባደረጉት ገለጻ፣ የአፄ ምኒልክ ቤተ መንግሥትን የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ እንደሚገባ መግለጻቸው ይታወሳል።

 ቤተ መንግሥቱ ኢትዮጵያ ምን እንደምትመስልና ጥንታዊ ገናናነቷ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ መሆን በወቅቱ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ያለፋት የኢትዮጵያ መንግሥታት እያንዳንዳቸው በቅጥር ግቢው ትተው ያለፋትን አሻራ ለማሳየት፣ ለዓመታት የተዘጉ ቤቶችን በማስከፈት የካቢኔ አባሎቻቸውን እያዞሩ ማስጎብኘታቸው አይዘነጋም።

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፈንሳይ-ፓሪስ⬆️ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ሚ/ር #ኢማኑኤል_ማክሮ ጋር ኤሊሴ ፓላስ ተወያዩ።

በውይይታቸውም:-

1) የላሊበላን አብያተ-ክርስቲያናት የጥገና ስራ ፈረንሳይ #እንድትደግፍ:

2) የፈረንሳይ ኢንቨስተሮች ወደ #ኢትዮጵያ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ:

3) ለልማት የሚያግዝ:- ቀጥታ የበጀት ድጋፍ ለማድረግ፣ በፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ፣ በአይ.ኤም.ኤፍ. እና በአለም ባንክ በኩል በቀጥታ እና በቦርድ በኩል #ድጋፍ ለማድርግ:

4) በአፍሪካ ቀንድ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የመጣውን ሰላም በማስቀጠል በኤርትራና በጅቡቲ መካከል ሰላም እንዲጠናከር ለማድረግ:

5) ፕሬዚዳንት ማርኮ ኢትዮጵያን #እንዲጎብኙ: ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከትላንት በስቲያ የላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት ከጥገና እና እንክብካቤ አንጻር የሚገኙበትን ሁኔታ መጎብኝታቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም(አብቁተ) ለጣና እና ለላልይበላ እንክብካቤ የሚውል 4 ሚሊየን ብር #ድጋፍ አድርጓል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አባጅፋር⬆️የአሜሪካ መንግስት በጅማ ለሚገኘው የአባጅፋር ቤተ መንግስት እድሳት #ድጋፍ አድርጓል፡፡ የእድሳት ፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ራይነር እንደተናገሩት ይህ የአሜሪካ ድጋፍ አከባቢውን የባህል መዳረሻ የማድረግ ሰፊ #ራዕይ አካል ነው ብለዋል፡፡ የአሜሪካ መንግስት ለዚህ ተግባር የሚውል $125,000 ድጋፍ አድርጓል፡፡

ፎቶ፦ የአሜሪካ ኤምባሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወላይታ ሶዶ⬇️

በወላይታ ሶዶ ከተማ ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ችግር  ንብረት ለወደመባቸውና #ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች በክልሉ መንግስት ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ #ድጋፍ ተደረገ፡፡

የደቡብ ክልል መንግስት ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ተጎጂዎችም ድጋፉ ተስፋ ከመቁረጥ እንዳዳናቸው ተናግረዋል፡፡

የሶዶ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ #ባታላ_ባራና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ.ም በከተማው ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር የንብረት ጉዳት መድረሱን አስታወሰዋል፡፡

ከተጎጂዎች መካከል አብዛኞቹ በተለያዩ የንግድ ሥራዎች የተሰማሩ ሲሆን በንግድ ተቋማት፣ በመኖሪያ ቤቶችና በተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንም አመልክተዋል፡፡

ባለፉት ጥቂት ወራት የማጣራትና መረጃ የማሰባሰብ ሥራ መሰራቱን ገልጸው በተገኘው መረጃ መሰረት ለ89 ተጎጂ ግለሰቦች ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ተጎጂዎቹ ራሳቸው ባቀረቡትና ከአካባቢው ህብረተሰብ በተሰበሰበ መረጃ እንዲሁም በንግድ ፈቃዳቸው ላይ ያስመዘገቡት ካፒታልና የገቢ ግብር ማህደርን መነሻ በማድረግ የማጣራት ሥራው መከናወኑንም አቶ ባታላ ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሰረት የክልሉ መንግስት ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎ ከ11 ሚሊዮን 478 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀዋል።

የሶዶ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤና የአጣሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ ታልጎሬ ታደሰ በበኩላቸው የተሰበሰበውን መረጃ መሰርት በማድረግ እንደጉዳታቸው መጠን ድጋፉ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

“እስከ 10 ሺህ ብር ጉዳት ያቀረቡ 34 ተጎጂዎች ገንዛባቸው ሙሉ በሙሉ እንዲተካላቸው የተደረገ ሲሆን ቀሪዎቹ 55ቱ የጉዳታቸውን 50 በመቶ እንዲያገኙ ተደርጓል” ብለዋል፡፡

ባለሁለት ጎማ የሞተር ብስክሌት ለተቃጠለባቸው ወገኖች ምትክ እንዲገዛ መወሰኑንና በመኖሪያ ቤታቸው ጉዳት ለደረሰባቸው ደግሞ ጥገና ለማድረግ የሚያስችል ድጋፍ መደረጉን አስረድተዋል፡፡

ድጋፍ ከተደረገላቸው ተጎጂዎች መካከል ወይዘሮ ምህረት መሸሻ በከተማዋ ጤና ጣቢያ ሰፈር የህጻናት አልባሳትና ኮስሞቲክስ ይነግዱ እንደነበረና በዕለቱ በድንገት በተፈጠረው ችግር መዘረፋቸውን ገልጸዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት ወይዘሮ ምህረት ችግሩ ከደረሰ በኋላ ከፍተኛ ጉዳት ውስጥ ቢቆዩም ድጋፉ ሥራቸውን ዳግም ለመጀመር የሚያስችልና ተስፋ ከመቁረጥ እንደታደጋቸው ገልጸዋል፡፡

በሶዶ ከተማ መሃል ከተማ በኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ንግድ ሥራ የተሰማሩት አቶ ኑሪ ባዲ በበኩላቸው ድንገት በተፈጠረው ችግር  በህገ-ወጦች ቢዘረፉም የመንግስት ድጋፍ ዳግም ወደስራቸው ለመመለስ እንዳገዛቸው ተናግረዋል፡፡

ችግሩ ሰላም የማይፈልጉና በሁከት ሰበብ ለዘረፋ የተዘጋጁ ነውጠኞች ያደረጉት መሆኑን ጠቁመው የተዘረፈውን ንብረት ለማስመለስ ነዋሪውና የከተማው ጸጥታ ኃይል ያደረገው ርብርብ የማይረሳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ.ም በከተማዋ ተከስቶ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ምክንያት በንብረታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች መንግስትና የከተማዋ አስተዳደር ከቃል ባለፈ ተጨባጭ ድጋፍ ባለማድረጋቸው ተቸግረናል ሲሉ ያቀረቡትን ቅሬታ ኢዜአ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሞያሌ🔝

ከህዳር 2 እስከ 7 በሞያሌ በደረሰው ጥቃት ቤታቸዉ የተቃጠለባቸዉ የከተማዋ ነዋሪዎች #ድጋፍ አጥተው እየተቸገሩ መሆናቸውን ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ ከመንግሥት አካል መጥተው ያናገራቸው አካል አለመኖሩንም ለአሜርካ ድምፅ ገልፀዋል። የኦሮሚያ አደጋ መከላከል ኮሚሽን ለተጎጂዎቹ በሳምንት ውስጥ #እርዳታ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር🔝የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እምቦጭ አረምን ለመከላከል የሚውል 10 ሚሊዮን ብር #ድጋፍ ሰጠ፡፡ገንዘቡን የሰጡት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ናቸው፡፡ምክትል ከንቲባው ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል፡፡ በወንድማማች ወጣቶች ውይይት ላይም እየተሳተፉ ነው፡፡

ምንጭ: አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በሱማሌ ክልል ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን #ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ የሴቶች፣ የህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር #ከሆራይዘን_ኩባንያ ጋር በመተባበር የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ለክበበ ጸሃይ ህጻናት ድጋፍና ክብካቤ ማዕከል፣ ለቀጨኔ የህጻናት ማሳደጊያ ተቋም እና ለአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር የማረፈያ ማዕከል ከስምንት መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ #ድጋፍ አደረጉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአውሮፓ ህብረት የኤርትራ ወደቦችን ከኢትዮጵያ ድንበር ጋር የሚያገናኙ መንገዶችን መልሶ ለመገንባት የ20 ሚሊዮን ዩሮ #ድጋፍ ማድረጉን የአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የአውሮፓ ህብረት ሁለቱን ሀገራት ለመደገፍ #ቁርጠኛ መሆኑን የህብረቱ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኔቨን ሚምካ ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት በማጠናከርና ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን ለሁለቱ ሀገራት ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያና ኤርትራ ከ20 ዓመታት በኋላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ማደሳቸውን የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia