TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢንጂነር_ታከለ_ኡማ

በአዲስ አበባ ከተማ #በ2012 የተመደበው #በጀት በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚደረግ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 6ተኛ አመት የስራ ዘመን 3ተኛ መደበኛ ማጠቃለያ ጉባኤውን የከተማ አስተዳደሩን የ2012 በጀት በማጽደቅ አጠናቋል፡፡

ምክር ቤቱ በ2012 በጀት አመት ከ48 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት መድቧል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ያሉባትን ችግሮች ለሚቀርፉ ፤ነዋሪዎቿን በተሻለ መንገድ ተጠቃሚ ያደርጋሉ ለተባሉ እንዲሁም አንገብጋቢ ለተባሉ የልማት ጥያቄዎች በቂ ምላሽ መስጠት ለሚችሉ ዘርፎች ልዩ ትኩረት የሰጠ በጀት ምደባ ነው ተብሏል፡፡

በጀት ከመመደብ ባለፈ አጠቃቀሙ ላይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጀቱን አዋጪ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የአስፈፃሚ ተቋማትን አቅምና አደረጃጃት የማስተካከል ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የተመደበው በጀት በአግባቡ ለታለመለት አላማ እንዲውል የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር እንዲያደርጉም አሳስበዋል፡፡

Via #AddisTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በምእራብ ሸዋ ዞን #በ2012_የትምህርት_ዘመን ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕጻናትን ወደ ትምህርት ገበታ ለማምጣት የቤት ለቤት ምዝገባ እየተካሄደ ነው። የዞኑ ትምህርት ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ታምራት ዳባ እንደገለጹት ከነሀሴ 20 ቀን 2011 ጀምሮ ቤት ለቤት በተደረገ አሰሳ ዕድሜያቸው ደርሶ ወደ ትምህርት ቤት ያልመጡ 128 ሺህ ህጻናት ተመዝግበዋል። ከተመዘገቡት ህፃናት መካከል 45 ሺህ 100 ሴቶች ናቸው። የተመዘገቡት ህፃናት  የአንደኛ ክፍል አዲስ ተመዝጋቢዎች እና በቅድመ መደበኛ የትምህርት መርሃ ግብር የሚሳተፉ ናቸው፡፡ “መምህራን፣ የትምህርት ባለሙያዎችና የመስተዳድር አካላት በምዝገባው እየተሳተፉ ነው ” ብለዋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia