TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጋምቤላ ክልል‼️

በጋምቤላ ክልል በማጅንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ እና አካባቢው በ126 ሰዎች ግድያ፣ 36 ከባድ የአካል ጉዳት፣ ከ 7 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን በማፈናቀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ፍርድ ቤት #ጥፋተኛ ብሏል።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው በጋምቤላ ክልል #በማጅንግ_ዞን ጉደሬ ወረዳ እና አካባቢው ከ2006 እስከ 2007 ዓ.ም ከሌላ ቦታ የመጡ ነዋሪዎች ላይ ከላይ የተጠቀሱትን ድርጊት በመፈጸም ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው ክስ ተመስርቶባቸው ከ4 አመት በላይ በፍርድ ቤት ክርክር ላይ የነበሩ ከ15 በላይ ተከሳሾች ላይ ነው የጥፋተኝነት ውሳኔውን ያሳለፈው።

ተጠርጣሪዎቹ ከሌላ አካባቢ መጡ ያሏቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችን ሚዚያ 29 በተባለው የመሰብሰቢያ አደራሽ በመሰብሰብ የቡናም ሆነ የሌሎች ምርት ውጤቶችን ለማጅንግ ብሄረሰብ ማከፈል አለባችሁ በማለት ሲዝቱባቸው የነበረ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም የዞን እና የወረዳ ሚሊሻዎችን በማነሳሳት ያልታጠቁትን በማስታጠቅ በአካባቢው ግጭት በመፍጠር የ126 ዜጎች ህይወት እንዲጠፋ፣ 36 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እንዲደረስ እና 7 ሺህ 422 ነዋሪዎች ማፈናቀላቸውን አቃቤ ህግ በክሱ አስረድቷል።

በ2007 ዓ.ም በቁጥጥር ስር በዋሉት ተጠርጣሪዎቹ ላይ አቃቤ ህግ ያስረዳልኛል ያላቸውን የሰነድ እና የሰው ማስረጃ አሰባብሰቦ አሰምቷል።

ተካሳሾቹ የአቃቤ ህግን የሰነድ እና የሰው ማስረጃዎች መከላከል ባለመቻላቸው ጉዳዩን የተከታተለው ፍረድ ቤቱ ጥፋተኛ ብሏቸዋል።

በዚህ መዝገብ በ39ኛ ላይ ክስ ቀርቦበት የነበረው አቶ ጸጋየ ገሊቶ የቀረበበትን የአቃቤ ህግ የሰነድ እና የሰው ማስረጃ በአግባቡ መካከሉን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በነጻ አሰናብቶታል።

በሌሎቹ ተከሳሾች ላይ ግን የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ ሀሳቦች ለማቀበል ፍርድ ቤቱ ለታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia